RSS

Daily Archives: January 27, 2013

የሃይማኖት መብቶች እንዲከበሩ ለሁሉም መብቶች የመታገያ ግዜው አሁን ነው!

ፍትህ፣ ነጻነት፣ እኩልነትና አንድነት የብዙ ሃይማኖቶች መሰረታዊ መርህ እሴቶች ናቸው። እነዚህ ቲውፊቶች ለአለፉት 20 አመታት በዘረኛው ወያኔ እየተሸረሸሩና እየመነመኑ ዛሬ ከእነ አካቴው በሀገራችን ኢትዮጵያ ስለመሰረታዊ የሰው ልጆች መብት ነጻነት እንዳይወራ፤ ወያኔ የጥይት አፈ ሙዞች በእያንዳንዱ የህዝብ አገልግሎት ተቋማት ላይ በመደቀን የአምልኮ ቦታዎችን ሳይቀር በመዳፈር ህዝበ ምእመናኑ የእኔ የራሴ የሚለው የአምልኮት ቦታ እና ህግ እንዲያጣና እንዳይኖረው እያደረገ ነው።

በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቀን ወደቀን እየተባባሰ የመጣው የእምነት ነጻነት እጦት ሁላችንንም ሊያሳስበን እና ሊያስተሳስረን የሚገባበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። በተለይም በታሪካችን፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በእምነት፣ በዘር፣ በፖለቲካ እስከ ቅርብ ጊዚያት ድረስ ሳይለያይ ተከባብሮና ተሳስቦ የሚኖር ህዝብ እንደሆነ የማይካድ ሃቅ ነው።

ይሁን እንጅ ከቅርብ ግዜ ወዲህ አምባገነኖች በፈጠሩት ህገ- አራዊት በሆነው የከፋፍለህ ግዛ እና የአንድ ዘር የበላይነት ፖሊሲ አማካኝነት የምንወዳት ሀገራችን ኢትዮጵያ፤ አበው ለአንድነቷ፣ ለህልውናዋ የሞቱላት፣ ዘውግ፣ ቋንቋና የሃይማኖት ልዩነት ሳያግዳቸው የገነቧት እማማ ኢትዮጵያ፤ የልጆቿ የኤሎሄ ማሰሚያ ስፍራዎች፣ ተቋማትና የገዳማት አባቶች በህወሃት የጥፋት አለንጋ እየተገረፉ ናቸው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን 4ኛውን ፓትርያርክ ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ ከእምነቱ ቀኖና ህግ ውጭ በሆነ መንገድ ህጋዊውን ፓትርያርክ በማባረር በዘረኛው የወያኔ አስተዳደር ስርአት ውስጥ በማስገባት አባ ጳውሎስ እስከሞቱበት እለት ድረስ እና አሁንም ምእመናኑ በመከፋፈል የተሳካላቸው ወያኔዎች፤ በቅርቡ ሊደረግ የነበረውን የእርቀ ሰላም ሂደት በወያኔ ጀሌዎች እንዲሰናከል የስርአቱ አገልጋይ አባቶች የሆኑትን፤ ልሳናቸውን በመጠቀም የኦርቶዶክስ ተዋህዶን እምነት አሁንም በወያኔ ቁጥጥር ስር ሆና እንድትመራ የተደረገው አሳዛኝ ክስተት አንዱ ነው። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on January 27, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , , ,

ሒትለርና አይሁድ፤ መለስ፤ ስብሀትና አማራ

ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)

ውድ አንባቢያን “ዘራፊ ሚሊየነሮች” ለሚለው ጽሁፍ ካደረሳችሁኝ መልሶች አጠር ያለውን አንዱን እንመልከትና ወደሚቀጥለው ጉዳይ እናመራለን።  ወዳጄ ስለነዚህ እርጉም ሰዎች የጻፍከዉን ከማህደሬ አዉጥቼ ዛሬ አነበብኩት። እግዜር ይስጥህ። ምን እላለሁ። አፍዝ አደንግዝ እንደተደረገብን ሁሉ ዝም ብሎ ማየት ሁኗል ።ጉርሻ በሚሸጥበት አገር ሰዉ በቁንጣን አለቀ ሲሉን ለማመን ይዳዳናል። ምን አይነት እርጉም ወራዳ ትዉልድ እንደሆንን ነዉ የሚያሳየዉ።

የትግሬ እና የሻቢያ ምሁራን ቀጥፈዉ ዋሽተዉ በድፍረት የሌለ ታሪክ ታሪክ አድርገዉ ተከታዮቻቸዉን እያሳመኑ ነዉ። የእኛ ምሁራን ደግሞ ሲሞዳሞዱ ጥቅም አይቅርብን ብለዉ ሲልከሰከሱ ስለኢትዮጵያ ከሞላ ጎደለ የሚጽፈዉ ያዘነልን ነጭ ሁኗል።  ቢያስቡት ቢያስቡት መልስ የሌለዉ ነገር ነዉ። ነገር ግን ትግሬን ምን አደረግነዉ? ትግሬ ከሌሎች ወገኖች በላይ የደረሰበት በደል ምንድነዉ? ኢትዮጵያን ሊያጠፋ የተነሳበት ምክንያት ምንድነዉ? የሚለዉ ነገር ሁልጊዜ ጥያቄ ዉስጥ ይከተኛል።

የሚገርመዉ በኢትዮጵያ አንድነት ከምንም በላይ ተጠቃሚ የነበረዉ ትግሬ እና ጉራጌ ነበር። ምክንያቱም ካካባቢያቸዉ ወደሌላዉ የኢትዮጵያ ክፍል እየተዘዋወሩ ይጠቀሙ ነበር። ታድያ እነዚህ ከተንኮል ድርና ማግ የተሰሩ ዘወትር ቢላ እየሳሉብን እኛ ስንገነባ እነሱ ሲያፈርሱን እዚህ ደርሰናል። በጽሁፍህ ያልተስማመሁበት የትግራይ ህዝብ ከፍተኛ በደል ላይ እንዳለ ጠቁመሀል።፡በዉነቱ ለእነሱ የዚህ አይነት አባባል ከማሳቅ አልፎ ሌላዉን ሽንታም እያሉ ያላግጡበታል። ከእዉነታዉ ጋር ስለማይዛመድላቸዉ አያምኑትም። የትግራይ ህዝብ በጣም ደስተኛ ነዉ። በፖሊሲ ደረጃ አቦይ ስብሀት አላማችን ለሚቀጥለዉ 10 አመት የትግራይን ህዝብ ወደ መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ማሸጋገር ነዉ ብሏል። መቀሌ ዛሬ ደረጃዋ ከአዉሮፓ እኩል ነዉ። ለግንዛቤ እንዲረዳህ ተከታታይ እዛ የሚሰራ የአገር ቤት ትያትር ስላለ እሱን መመልከት ነዉ። የነጻ ትምህርት እድል 100% የሚሰጠዉ ለትግሬ ነዉ ይህም በስዉር አይደለም መለስ ዜናዊ አማራዉ ቀደም ባለዉ ጊዜ ስለተጠቀመ ነዉ ብሎ መልሷል። እዉነትነቱን እንድትመረምር ላንተ ትቸዋለሁ። ወደ አሜሪካ እና አዉሮፓ እየተዘዋወሩ የሚነግዱት ትግሬዎች ናቸዉ። ከትግራይ መጥተዉ ቦታ ተስጥቷቸዉ ሽጠዉ እንዲጠቀሙ የተደረጉት ትግሬዎች ናቸዉ። ብዙ ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል። ትግሬ ተጠቃሚ ነዉ ያለዉንም መንግስት በጣም ይደግፋል። ተበድለናል ካሉም እነሱ እራሳቸዉን ለመከላከል ብቃቱ ስላላቸዉ እነሱዉ ይንገሩን እንጅ እኛ የሌለ በደል ባንፈጥርላቸዉ ጥሩ ነዉ። ያለበለዚያ ምንም አልበደልንም ማለት ነዉ በማለት ልጓሙን ያጠብቁብናል። አንዳንድ የዋሆች አዲስ አበባ ደርሰዉ ሲመለሱ ለማኙ ሁሉ ትግሬ ነዉ ይላሉ። እንዴት ያስቃል ያ በትግርኛ የሚለምነዉ ሰዉ ሚስቱን ተቀምቶ የተባረረ የወልቃይት እና ጠገዴ ህዝብ እንጂ ትግሬ አይደለም። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on January 27, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , , ,