RSS

Category Archives: POEM

ጀግንነትህ የገባኝ ዛሬ ነው

 

ስምን መላክ ያወጣዋል አሉ!!! ”አንዳርጋቸው” አሉህ እውነትም አንዳርጋቸው። የዚያን ትውልድ ዓላማ፣ ቁርጠኛነትና ፍቅር፤ ተስፋ አይቆርጤነት፣ ጥንካሬና የአመራር ብቃት ያየንብህ ታላቅ ሰው፤ በራስህ ትውልድ የጀመርከውን የነፃነት ጉዞ ለመቋጨት ከጓዶችህ እጅግ ወርደህ ይህን ትውልድ ስለ ሀገር አንድነትና ሉአላዊነት፣ ስለ ሰው ልጅ ክብርና እኩልነት፤ ስለ ነፃነት አስፈላጊነት በተለይም በዘመንህ አሳምረህ የምታውቃቸው ጠባቦቹ ወያኔዎች በሀገራችንና በወገናችን ላይ እያደረሱት ያለውን ዘመን አይሽሬ ጭካኔና ክህደት ለማስተማር ለማሳወቅና ለማሰልጠን ብሎም በትግል ነፃ መውጣትን በተግባር ለማሳየት ከአውሮፓ ዉብ ከተማ በርሃ ድረስ የወረድክ ምሳሌ የማይገኝልህ ንዑድ ኢትዮጵያዊ ነህ።

”አንበሳው በጅቦች ተከቦ አየሁት” አለ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ እውነት ነው ከምንም በላይ ገዝፈህ ”ልብ ካላችሁ ኑና ግጠሙን” ሲል የነበረውን ወያኔ በፈለገው ቋንቋ ለማናገርና የፈለገውን ለማሳየት ባደረከው ውጠታማ ጉዞ ገና በሩቁ ውሃ ያስጠማህ ያንበሶች አንበሳ ነህ አንዳርጋቸው። ላለፉት ከ 40 ዓመታት በላይ በሚያስደንቅ ጥንካሬ፣ ሀቀኝነትና ታማኝነት ጎልተህ የምትታይ በሳል ፖለቲከኛ፤ የእኩልነትና የመፈቃቀር ተምሳሌት ነበርክ ነህም። እናም በአንክሮ ከማስተዋልህ ጀርባ፣ እናም ከእርጋታህና ከትግስትህ ጀርባ፣ እናም ከምክርህና ከአርቆ አስተዋይነትህ ጀርባ ያለው ማንነትህ፣ ያለው ጀግንነትህ የገባኝ ዛሬ ነው። አወ ጀግንነትህ የገባኝ ዛሬ ነው።

ጀግንነትህ የገባኝ ዛሬ ነው 

አብረን እንደግ እንጅ በመለያየት አንጥፋ

እንደጋገፍ እንጅ አንዳችን ላንዳችን አንክፋ

ሁላችን አንድ አይነት ሰው ነን

ጌታና ሎሌ የሌለን

ስለዚህ እኛው ለእኛ እንወግን Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on July 10, 2014 in AMHARIC, ARTICLE, POEM, VIDEO

 

Tags: , , ,

ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለዳ አይቀበለውም

ከይኸነው አንተሁነኝ

ህዳር 5 2013

ሁሉም ሰው ሰው በመሆኑ ባቻ የሚያገኛቸው ሰብአዊ መብቶች እንዳሉት ሁሉ፤ በዜግነቱ ደግሞ ከሀገሩ የሚጠብቃቸው መንግስታዊ እገዛዎችና ከለላዎች እንደሚኖሩ እሙን ነው። በሕዝብ የተመረጠው ወይም ተመርጫለሁ የሚለው መንግስትም መርጦኛል የሚለውን ማሕበረሰብ ፍላጎት ለማሟላት መጣሩ የሚጠበቅ ከመሆኑም በላይ ከዜጎቹ አንዱ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ አደጋ ቢያጋጥመው አግባብነት ያለው ፍትህ እንዲያገኝ መሟገቱና ፍትህ እንዲያገኝ መጣሩ ከመንግስታዊ ግዴታዎቹ ውስጥ እንዱና ዋነኛው ነው። ይህ እንግዲህ እንደመንግስት መንግስታዊ ግዴታዎችን ለሚያስተዳድረው ማሕበረሰብ እያበረከተ ላለ መንግስታዊ አካል የሚሰጥ ሃላፊነት ነው። መንግስትነትን መስም ብቻ ተጎናጽፈው እንደሚገኙት ፋሽስት ወያኔ አይነቶቹ ግን ሁሉም ነገር ነግድ ነው። የዜጎች ሰላምና ጤንነት እንዲሁም የሀገር ድንበር መከበርና ሉአላዊነትም እንኳ ቢሆን ከወያኔ ባለስልጣናት ጥቅም አኳያ የተቃኘ ነው። በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያለው የዜጎች ሁለንተናዊ ሰላም ከወያኔ ፖለቲካና የስልጣን ዘለቂነት አንጻር የተለካ ነው። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on December 5, 2013 in AMHARIC, ARTICLE, POEM

 

Tags: , , , , ,

የሳውዲ መንግስት የማሰርና የማሳደድ፤ የመግረፍና የመግደል ሉአላዊ መብት አለው፡- ሽመልስ ከማል

ከይኸነው አንተሁነኝ

ታህሳስ 5 2013

ሀገሮች ሕዝባቸውን የሚያስተዳድሩበት የውስጥ ህግ እንዳላቸው ሁሉ በሌላኛው ሀገር የሚገኝ ዜጋቸውን ሰላም ከማስጠበቅ አንጻር ወይም ደግሞ  ንግድና መዋዕለ ንዋይ ፍሰትን የመሳሰሉ የሁለትዮሽ ግንኙነት የሚፈልጉ ጉዳዮችን በተረጋጋና የራሳቸውን ዜጋ በማይጎዳ መልኩ ለመከወን ይመቻቸው ዘንድ የጋራ ስምምነት ሊያደርጉ ይችላሉ። ይሁን እንጅ ማንኛውም የሀገር ውስጥም ሆነ የሁለትዮሽ ስምምነት ዜጎችን ለችግር የማያጋልጥ መሆን የሚጠበቅበት ከመሆኑም በላይ በዓለም አቀፍ ህግጋት መርህ የተቃኘ ሊሆን ይገባዋል። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on December 5, 2013 in AMHARIC, ARTICLE, POEM

 

Tags: , , , , ,

የባንዲራ ታሪክና ክብር- በኑረዲን ኢሳ

 
Leave a comment

Posted by on September 21, 2013 in AMHARIC, POEM, VIDEO

 

Tags: , , , , ,

እዩና ፍረዱ… (video)

እዩና ፍረዱ ሰዎች  ተዋርዷል ዛሬ አማራው

ሀገሬን ሕዝቤን ስላለ የሚደራረብ መከራው

ባንዲራ ይክበር ስላለ እንደ ጉድ ፍጠረት የታየው

እኒህ በዘፈቀደ በጎጥ ድሪቶ ተሸፍነው

እንዲህም እንዲያ ነበረ እያሉ ቢዘላብዱ

ከባዶ ህሊና ከርሳቸው የራቀ ሌላ ነው የሃቅ መንገዱ Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on April 13, 2013 in AMHARIC, POEM, VIDEO

 

Tags: , , , , ,

ለዱላ አንበገር

ከይኸነው አንተሁነኝ፣ ጥቅምት 16 2012

ዓላማውን ስቶ እጅ ሰጥቶ የረታ

ወድቆ ተንደባሎ ወያኔን የገታ

አጎንብሶ ሰግዶ ችግሩን የፈታ

ከወያኔ አብሮ ሀገሩን የረዳ ህዝቡን ያበረታ

ስለማያውቅ ታይቶ  ወገን ድል የመታ፤ Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on October 16, 2012 in AMHARIC, POEM

 

Tags: