RSS

Monthly Archives: June 2013

ወያኔ ሕወሃት የደደቢቱን አስታውስ!!!

 

ይኸነው ዓለሙ

ሰኔ 25 2013

በሚያስደንቀው የሀገራችን ምርጫና ከዚሁ የምርጫ ሳጥን በሚገኝ የሕዝብ ድምጽ፤ በሰላማዊ መንገድ ወያኔ ሕወሃትን እናሸንፋለን ብለው ቀን ከሌት ከሚደክሙትም ሆነ ሰላማዊው አማራጭ አዋጭ አይደለም በማለት በነፍጥ ወያኔን ለማንበርከክ እየታገሉ ያሉ ኢተዮጵያዊ የፖለቲካ ፓርቲዎችንም ሆነ ድርጅቶችን በሀገር ፍቅር ማጣትም ሆነ ተቆርቋሪነት፣ በሕዝብ ክብር መጉደልም ሆነ ሀላፊነትን መዘንጋት ለመውቀስ የሚያበቃ የሞራል ልዕልና ወያኔ ሕወሃት የለውም። ሌላው ቀርቶ በጫካ ዘመን አስተሳሰቡና ምግባሩ ይቅርና መንግስት ነኝ ካለ በሗላ ባሳያቸውና እያሳያቸው ባሉት ምግባሮቹ እንኳ ቢገመገም በሀገራችን ካሉት ሀገራዊም ሆኑ ክልላዊ ፓርቲዎች እንዲሁም በነፍጥ እየታገሉ ካሉት ድርጅቶችና ንቅናቄዎች ጋር ለመወዳደር የሚያበቃ ተክለ ሰውነት እንዲሁም የሀገርና የሕዝብ ፍቅር አልታየበትም።

እነዚህን ፓርቲዎች ወይም ድርጅቶች አንድ ጊዜ የሀገራችንን ጥቅም አሳልፈው የሸጡና ከአሸባሪ ጋር የወገኑ ሌላ ጊዜ ከሀገራችን ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ያበሩና ሀገር ለማፈራረስ የተዘጋጁ እያለ ለመክሰስ እራሱ ወያኔ ሕወሃት ማነው? እንዴትስ አሁን ላለበት የገዥነት ወንበር በቃ? በነማን እርዳትነት? አሁንስ ስለ ሀገራችንና ሕዝባችን ያለው አመለካከት ምንድን ነው? እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች መመልከት ተገቢ ይሆናል። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on June 25, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , ,

ዓባይና የአሜሪካ ጨዋታ


576561_4702713808339_449625552_n

መስፍን ወልደ ማርያም

ሰኔ 2005

በአሥራ ዘጠነኛው ምዕተ-ዓመት አስተሳሰብ ከዚህ ቀጥሎ የተጠቀሰው ዓላማ ለአውሮፓ ቄሣራውያን ዋና ግባቸው ሆኖ እስከሃያኛው ምዕተ-ዓመት ዘልቆአል፤ አሀን ፈጽሞ በተለየ ዘመን አሜሪካ ይህንን አስተሳሰብ ይዞ የተነሣ ይመስላል።

ኢትዮጵያን የተቆጣጠረ ዓባይን ይቆጣጠራል፤ ዓባይን የተቆጣጠረ ግብጽን ይቆጣጠራል፤ ግብጽን የተቆጣጠረ ኃይል ቀይ ባሕርን ከመግቢያና መውጫው ጋር ይቆጣጠራል፤ ቀይ ባሕርን ከመግቢያና መውጫው ጋር የተቆጣጠረ ኃይል ዓለምን ይቆጣጠራል።

አሜሪካ በግብጽ ላይ የተከለው ጥፍሩ ሲነቃነቅ መነቀሉ አለመቅረቱን ስላወቀው ሌላ የሚተክልበት አገር ይፈልጋል፤ በአካባቢው የግብጽን ነፍስ የሚነካ ከኢትዮጵያ የተሻለ አገር የለም፤ ለአሜሪካ ዓለም-አቀፍ ዓላማ ኢትዮጵያ ስትመረጥ የአሁኑ የመጀመሪያው አይደለም፤ በመሀከለኛው ምሥራቅ የአረቦችን የተባበረ ኃይል ለመቋቋም የተመረጡ ሦስት አረብ ያልሆኑ አገሮች — ቱርክ፣ ኢትዮጵያና ፋርስ (ኢራን) — ነበሩ፤ በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የአሜሪካ ዓለም-አቀፍ ኃይል መሰማት በጀመረበት ጊዜ ኢትዮጵያን ከከበቡአት የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ጋር የነበርዋትን የቆዩ ውዝግቦች ለመቋቋም የአሜሪካ ድጋፍ በጣም አስፈላጊ ነበር፤ አሜሪካን ከአውሮፓ አገሮች ጋር እየመዘኑና እያመዛዘኑ የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስከበር የተደረገው ዲፕሎማሲ (ዓለም-አቀፍ የሰላም ትግል) የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን መንግሥት በእውነት ከሚያኮሩት ተግባሮች አንዱ ነው፤ ይህንን ትግል አምባሳደር ዘውዴ ረታ ምስጋና ይድረሰውና የኤርትራ ጉዳይ በሚለው መጽሐፉ ግሩም አድርጎ አሳይቶናል። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on June 21, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , , , ,

ESAT SPORT SPECIAL WITH DEREJE AND FISSEHA

 
Leave a comment

Posted by on June 21, 2013 in ARTICLE, VIDEO

 

Tags: , , ,

Ethiopian History Discussed on VOA

The pseudo TPLF self appointed historian Gebrekidan Desta trying to transform Ethiopian history based on the failed TPLF ethnic politics. Dr. Shumet Sishagne, Associate Professor of History at the Christopher Newport University explained how fraudulent and biased Gebrekidan’s attempt was.

 
Leave a comment

Posted by on June 21, 2013 in AMHARIC, VIDEO

 

Tags: , , , ,

Subcommittee Hearing: Ethiopia After Meles: The Future of Democracy and Human Rights (video)

See it around 11:30

 

 
Leave a comment

Posted by on June 20, 2013 in ENGLISH, VIDEO

 

Tags: , , , ,

የሽፋን ስእሎች

ይኸነው አንተሁነኝ

ሰኔ 19 2013

እንዲሆንልን የተመኘነው ነገር እኛ በፈለግነው መልኩ ሳይሆን ሲቀር ምኞታችንን ሃሳባችንን የሚገልጽ ስም እንሰይማለን። ይህ አዲስ ስያሜ ታዲያ ስያሜ እንጅ በፊት እኛ የተመኘነው ስላልሆነ ይህን በማድረጋችን ራሳችንን  እንዋሻለን ወይም እንሸነግላለን። ለምሳሌ ሆስፒታሎችን ድልድዮችንና ትምህርት ቤቶችን እያፈራረሰና ባንኮችን እየዘረፈ እዚህ ለደረሰውና አሁንም ሕዝብን እያሸበረና ሰላም እያደፈረሰ ላለው ወያኔ “ተራሮችን ያነቀጠቀጠ” የሚል ሽፋን ስያሜ እንደተሰጠው መሆኑ ነው። ቢያንስ ለኛ ወያኔ ሕወሃትን አሳምረን ለምናውቀው ወያኔ ለራሱ ደቦ ሳይቆርስ ሲመኘው የነበረውን ስም እንዳወጣ እንገነዘባለን። እውነታው ግን ስም ወዲህ ተግባር ወዲያ ነው። መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ ይሏል ይህ ነው።

አንድ ሰው በመስታውት ራሱን ሲመለከት ራሱን እንጅ ሌላ ሊያይ አይችልም። ሌላ ያየ ከመሰለው እንኳ መሰለው እንጅ ራሱ አይደለም። ወያኔ ድልድይ እየደረመሰና ለሕዝብ ጥቅም የተገነባ ተቋም እያፈራረሰ፤ ሕዝብን እያተራመሰና እያሸበረ ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ከመሰለው ይህ መምሰል እንጅ ሃቁንማ እየተሸበረ ያለው ሕዝብ ያውቀዋል። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on June 19, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , ,

የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች-ወያኔ ሕወሃት

 

ይኸነው አንተሁነኝ

ሰኔ 12 2013

ሀገራትም ሆኑ ግለሰቦች እንድን ስራ ለመከወን ይነስም ይብዛ እቅድ ያቅዳሉ። ብዙዎቹ ባለሙያዎች እንደሚስማሙበትም እቅድ አቅምን ያገናዘበና ውጤቱም አርኪ እንዲሆን ለማድረግ ለእቅዳችን የሚያገለግሉ በእጃችን ያሉ ነገሮች ከሌሉት የመለየት መሰረታዊ ፍተሻ መደረግ አለበት። እንዲህ አይነቱ የመለየት ስራ ከአቅማችን ጋር ለመጓዝ ከማገልገሉም በተጨማሪ በእጃችን ያሉና እቅዱን ተፈጻሚ ሊያደርጉ የሚችሉ የገንዘብ፣ የሰው ሃይል፣ የቋሚና አላቂ እቃዎችን ዝርዝር በትክክል ለማወቅ ያገለግለናል። ከተደጋጋሚ ግዥና ያለአገልግሎት የሚቀመጥ የሰው ሃይል እንዳይኖር ከመጥቀሙም በተጨማሪ አግባብ ያልሆነ የእውቀት መደራረብን ያስወግዳል። ትዲያ ይህ ሁሉ ሃብትን የማወቅ ፍተሻ በራሱ ገንዘብ የሚያሰወጣ ከመሆኑ አንጻር ከፍተሻው የተገኘው ውጤት ለእቅዱ ግብአት ሆኖ ጥቅም ላይ መዋሉ የሚያከራክር መሆን የለበትም። ከዚህ አንጻር የልማት ፊታውራሪ ነኝ የሚለው ወያኔ ሕወሃት ምን አድርጓል ምንስ እየከወነ ነው?

ከዚህ በፊት የነበሩት የሀገራችን አገዛዞች በተለያየ ደረጃ የሀገራችንን ሃብት ተገቢ ባልሆነ መልኩ አባክነዋል። በተለይ በዘር ላይ የተመሰረተው የወያኔ ሕወሃት አገዛዝ ከሀገርና ሕዝብ ዘላቂ ጥቅም ይልቅ የተወሰኑ ጉጅሌ ስብስቦችን ፍላጎት ለመፈጸምና ለማስደሰት ያለመ በመሆኑ ብዙ ምስቅልቅሎችን ፈጽሟል። እይዘዋለሁ እደርስበታለሁ ብሎ ያሰበውንና እንደሚጨብጠው ገና ያላረጋገጠውን ነገር ለመጨበት ሲል በእጁ የነበረውን ለአገልግሎት የተዘጋጀ እጅግ በጣም ብዙ የሀገር ሃብት በትኗል። የበቆሎ ቂጣ እያረረበት አንድ ቁና የማትሞላ ነጭ ጤፍ በር ላይ በማስጣት ለጎረቤት ነጭ ቴፍ እየበላን ነው የሚል መልእክት ለማስተላለፍ እንደሚዳዳው አላዋቂ፤ ወያኔ ሕወሃትም የምእራባዊያንን ዓይን ለመጋረድ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ባለፈ ሲምንቶ የተገነቡና ጥራታቸው አስተማማኝ ያልሆኑ ጥቂት ሕንጻዎችን በማቆምና ልማት ላይ ያለ በማስመሰል የሕዝባችንን ችግር የደበቀ ይመስለዋል ከዚያም ሲያልፍ በኔ ያገዛዝ ዘመን አገሩ ሁሉ ድሎት በድሎት ሆኗል ሊለን ይሞክራል ። የአንዲት ሀገር ቁጥር አንድ ሀብት የሆነውን የሰው ሃይል ግንባታ ከመቼውም ጊዜ በከፋ መልኩ የትምህርትን ጥራት በመግደል ከመሰረቱ በማጥፋት ላይ ይገኛል። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on June 12, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , ,

የዛሬውን ችግር ለመወጣት ከአለፈው ስሕተት መማር ነው

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

ከጥቂት ቀናት በፊት አንዳንድ ሰዎች በዓባይ ጉዳይ ቀረርቶና ሽለላ ማሰማት ሲጀምሩ ከባድ የሆነ የመረጃ እጥረት መኖሩን ስለተገነዘብሁ ስለግብጽ የኃይል ሚዛን ደረቅ መረጃ የጦርነትን መጥፎ መልክ ከሚገልጽ አስተያየት ጋር አቀረብሁ፤ የወያኔ ሎሌዎች ወዲያው በእኔ ላይ የተቀናጀ ዘመቻ ከፈቱ፤ ድንቁርናው ከዚህ ይጀምራል፤ ማሪዮ ፊልሞና ብሩኖ ‹‹በአፍራሽ አስተሳሰባቸው የሚታወቁት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ዛሬም የግብጽን ጦር ገና ከሩቁ እንድንገብርለት ጉትጎታ ይዘዋል፡፡›› በማለት ውርጅብኙን ይጀምራል፤ አንድም ቦታ እኔ ያቀረብሁትን መረጃም ሆነ አስተያየት አንሥቶ ጉድለትን አላሳየም፤ ዓላማው መረጃው ወይም አስተያየቱ አይደለም፤ ለረጅም ጽሑፉ ዓላማው እኔ ነኝ፤ የአሉላ ሰሎሞን ጆቫኒ የግጥም ዓይነት መልክ ከመያዙ በቀር ያው ነው፡፡Prof. Mesfin Woldemariam

ለእነዚህ ሰዎች መልስ የሚያስፈልጋቸው በእኔ ላይ የሰነዘሩትን ለማረም አይደለም፤ አንዳንድ ሰዎች መልስ አይገባቸውም ይሉኛል፤ እውነት ነው፤ እኔ በሥራዬ እቆማለሁ፤ ወይም በሥራዬ እወድቃለሁ፤ ነገር ግን ንጹሐን ወጣቶችን አዋቂዎች መስለው እንዳይበክሉ መከላከል ግዴታ ነው ብዬ አምናለሁ፤ ድንቁርና እንደተላላፊ በሽታ ነው፤ ይጋባል፡፡ Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on June 9, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , , ,

የፍርሃቱ ኢያሪኮ ተደረመሰ

ይኸነው አንተሁነኝ

ሰኔ 5 2013

የሚሆን የማይመስለው ሆነ፤ ልቦች በአንድነት ዘመሩ፤ የደስታ እንባ ፈሰሰ፤ አእዋፍ በደስታ አብረው እስኪቀዝፉ ድረስ የነጻነት ድምጽ የነጻነት ጩኸት አየሩን ሞላው፤ የሕዝብ አሸናፊነት በግልጽ ገኖ ታየ፤ የታፈነው የድምጽ ማእበል ግድቡን ትሶ ወጣ፤ የምን እንደረግ ይሆን ጭንቀት እትትም ተደረመሰ፤ ምድር የጠበበች እስኪመስል ሽዎች በነጻነት ፈሰሱባት፤ በእውነት 1997ን በ2005 አየነው። ገዥዎቻችን የሕዝባችን የአልገዛም ባይነት ወኔ ባልተቋረጠው አፈናቸው ተዳፈነ እንጅ ፈጽሞ እንዳልሞተ በእርግጥ ባይኖቻቸው አዩ። ልዩነትን የሰበኩት ሲሳቀቁ ፀንቶ የነበረው የፍርሃት ግንብ ኢያሪኮ በሰላም በፍቅር በአንድነት መዝሙር ተደረመሰ እሁድ ግንቦት 25 2005 ዓ/ም።

በ1997 ዓ/ም ቅንጅት ካዘጋጀውና እስካሁንም ድረስ ትዝታው ከሕዝብ ህሊና ካልጠፋው ሰላማዊ ሰልፍ ወዲህ የመጀመሪያ የሆነው የግንቦት 25ቱ ሰልፍ መፈቀድን በተመለከተ አንዳንዶች ወያኔ ህዝብን ለመያዝ፣ ከሕዝብ ለመታረቅ ያደረገው ዘዴ ነው ይላሉ። ሲያስረዱም በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሶ የነበረውን የአማሮችን ከቤኒሻንጉል መፈናቀል ቀልብሶ ተፈናቃይ አርሶ አደሮችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ መሞከሩ፣ ጥቂት ቢሆኑም በሙስና ተዘፍቀዋል በሚል የራሱን የወያኔን ባለስልጣናት ዘብጥያ ማውረዱን ይጠቅሱና አሁን ደግሞ በሰማያዊ ፓርቲ የተጠየቀውን የሰላማዊ ሰልፍ እናድርግ ጥያቄ መፍቀዱ ወያኔ አንድም በአባይ ግድብ ምክንያት በተለይ ከግብጽ ጋር የገባበት እሰጥ አገባ ስላሳሰበው ሕዝባችንን ባንድነት ለማቆም ከማሰብ የተደረገ ነው ሲሉ በሌላ በኩል ደግሞ በሰባዊ መብት ረገጣ አይሆኑ እየሆነ ያለው ወያኔ የእርዳታ ሰጭ ሀገሮችንና ድርጅቶችን ቀልብ ለመግዛትና የውጭውን ማሕበረሰብ አይን ለመሳብ ያደረገው ነው በማለት የተቻሉ። ተችዎች ይህን ይበሉ እንጅ ከሰልፉ ትቂት ቀናት ቀደም ብሎና ከሰልፉም በሗላ በወያኔ መንደር እየሆነ የነበረውና ያለው ግን ይህን አያረጋግጥም ነበር። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on June 4, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , ,