RSS

Monthly Archives: December 2013

የአኖሌ ሐውልት ጉዳይ … «አሣ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል» እንዳይሆን – (ሞረሽ ወገኔ)

በቅርቡ የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ በሚቆጣጠረው የቴሌቪዥን ጣቢያ አንድ ዝግጅት ቀርቦ ነበር
ምንጭ:-

የዝግጅቱ ትኩረትም «የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ሠራዊት በአርሲ እናቶች ላይ በፈፀመው የጡት መቁረጥ ግፍ» መታሠቢያ የሆነ ሐውልት ስለመቆሙ ነበር። «ነገርን ከሥሩ ፣ ውኃን ከጥሩ» ይባላልና ለመሆኑ የዚህ አዲስ ሐውልት ባለቤቶች እነማን ናቸው? በሐውልቱስ መቆም ማን ምን ፋይዳ ያገኝበታል? ብሎ መጠየቁ ተገቢ ይሆናል። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on December 29, 2013 in AMHARIC, ARTICLE, VIDEO

 

Tags: , , , , , , ,

ወያኔዎችና ጨፍን ደጋፊዎች የንስሃ ቀናችሁ ገና አልመሸም

ሀገራችን ብዙ ጀግኖች የሀገር ኩራት የሆኑ የቁርጥ ቀን ልጆች የማፍራቷን አክል ስራቸው ሲታወስ ”ውሾን ያነሳ ውሾ” ተብለው የሚዘለሉ ብዙ ወራዶች አሳፋሪዎች ልጆችም ነበሯት። አሁንም አሏት። የሀገራችን የታሪክ ድርሳናት ወደ ሗላ ሲተረተሩ ሁለት ሶስቴ ቢወለዱ የሚባሉ ወገኖች እንዳሉን ሁሉ ምነው ባልተወለዱ የሚባሉም ሞልተዋል። በተለይ ሳያውቁ በስህተት ከተሰሩት ግድፈቶች ይልቅ እያወቁ በድፍረት፣ በማንአለብኝነትና በንቀት የተሰሩት ህሊናን እንዳደሙ ዘልቀዋል። የቁጭት እሳት በውስጣችን እንደጫሩ አሉ። የሀገራችንን የቅርብ ታሪክ የወያኔን ዘመን ብንመለከት እንኳ፤ በሀገርና በሕዝብ ላይ የተሰሩት በደሎችና የተፈጠሩት ችግሮች መቼ ሊፈቱ እነደሚችሉ ስናስብ ለምን ይህን አደረጉ? ከሚለው ጀምሮ የአመራር እርካታስ እስከምን ድረስ ነው? ብለን ለመጠየቅ እንገደዳለን። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on December 29, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , ,

መብት ረገጣውና ግድያው መልኩን ቀይሮ ቀጠለ እንጂ አላባራም

ይኸነው አንተሁነኝ

ታህሳስ 18 2013

በከተማው መሃል ስብሰባ ሊያስብል የሚችል ያህል ሕዝብ ተከማችቷል። ሁሉም በስሜትና በንዴት ይናገራል፣ ይጮሃል አንዳንዴም ይባርቃል። ራቅ ብሎ ለሚመለከታቸው እርስ በርሳቸው የሚደማመጡ እንኳን አይመሰሉም፤ ሁሉም ራሱን እያዳመጠ መናገር መናገር መናገር ብቻ። በመሃሉ የፋሽስት ወያኔ ታጣቂዎችና ወታደሮች በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎችና ወደ ተሰበሰበው ሕዝብ አካባቢ መታየት ጀመሩ። አለፍ ብሎም በትልቅ ካሚዮን ሙሉ የተጠቀጠቀ የወያኔ ጦር ተስተዋለ። ነገሮች ባልተጠበቀ ሁኔታና ፍጥነት መለዋወጥ ጀመሩ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በማን እንደተገደሉ የማይታወቁ ስምንት አስከሬኖችን የወያኔ ጦር ከሌላ መኪና ላይ ሲያወርድ ታየ። ሁሉም አስከሬኖች በከተማው መሃል ተሰብስበው ሲነጋገሩ የነበሩት ማሕበረሰብ አባላት የሆኑ የደገኞች ነበሩ። ይህ የሗለኛው የወያኔ ጦር አስከሬን የማውረድ እንቅስቃሴ በግልጽና በሕዝብ መሃል መደረጉ ሆን ተብሎ የተከወነና በከተማው መሃል የተሰበሰበውን ደገኛ ሕዝብ ስሜት የበለጠ ለማናር እንደነበር በሗላ ላይ ታውቋል። ይህ ከሆነ በሗላ ተሰብሳቢው ሕዝብ  ቆንጨራ፣ መጥረቢያና የመሳሰሉትን አይነት ቤት ሰራሽ ጥቃት መሰንዘሪያ መሳሪያ ለማምጣት እንዳበደ በየቤቱ ተበተነ። በካሚዮኑ ውስጥ ሲታዩ የነበሩ ወታደሮች ከመኪናቸው በመውረድ የተፈጠረውን አደገኛ ሁኔታ ሊያበርዱት ነው ተብሎ ሲታሰብ በደገኞቹ እየተመሩ ቁጥር እንድ ጥቃት ዘንዛሪዎች እነሱ ራሳቸው ሆኑ። ያለ ርህራሄ የከተማውን ኗሪ ሕዝብ በጥይት ይቆሉት ጀመር። መኖሪያ ቀያቸውን ማደሪያ ጎጇቸውን በእሳት በመለኮስ መሮጫ መንገድ መደበቂያ ፉካ አሳጥተው ያርበደብዳቸው ገቡ። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on December 18, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , , , ,

ኢትዮጵያ ትላንትናና ዛሬ

ይኸነው አንተሁነኝ

ታህሳስ 15 2013

ይህ ጊዜ የመበታተንና የመለያየት ጠላት፣ የፋሽዝም ቅስም ሰባሪ፣ የዘመኑ ፋሽስቶች የሌት ቅዠት፣ የመቻቻልና የዲፕሎማሲ አባት፣ የአዱዋ አናብስቶች መሪ የነበሩት እምዬ ዳግመዊ አፄ ሚኒሊክ መቶኛ ሙት ዓመት የሚከበርበት ሳምንት ነው። እምዬ አፄ ሚኒሊክ፤ ከነበረው የቀደምት አባቶቻችን የአስተዳደር ስርአት ውጭ ከሰባ ዓመታት በላይ በባላባቶችና መሳፍንቶች ተከፋፍላና ተቦጫጭቃ ስትበላ የነበረችውን ኢትዮጵያ እንደገና ወደ ቀደመው ክብሯና አንድነቷ ለመመለስ አቅደውና ጀምረው ሳይቋጩት ያለፉትን የአፄ ቴዎድሮስን ራእይ የተገበሩ፤ ሀገራችን ከውጭው ዓለም ጋር ሊኖራት የሚገባውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በተገቢው መንገድ ለማስኬድ የታተሩ፣ የዘመኑ የዓለም ቴክኖሎጂ ወደ ሀገራችን እንዲገባና እንዲስፋፋ በእጅጉ የጣሩ ከመሆናቸውም በላይ ሀገራችንን ወደ ቀደመው ቅርጿ በመመለሱ በኩል በዋናነት የሚጠቀሱ የትላንትም ሆነ የዛሬ ኩራት ናቸው- እምዬ አጼ ሚኒሊክና የዚያ ዘመኑ አስተዳደራቸው።

በሌላ መልኩ ፋሽስት ወያኔ ከቀደመው የአባቶቻችን የአስተዳደር ስርአት ፍጹም በተለየና ባፈነገጠ መልኩ ጥላቻንና መለያየትን የሰበከና በመስበክ ላይ ያለ፤ በአንድነት ስም መገነጣጠልን እያስተማረ ያለና ለዚህም ሽንጡን ገትሮ ያለ ሀፍረት የሚከራከር፤ ሰለ ፍቅር በሚል በቂምና በጥላቻ በተመረዘ አስተሳሰብ ድንበርን አሳልፎ በመስጠት ወይም በመሸጥ የሀገራችንን ክብር ያስደፈረ፤ በተዛባና የሀገርን ጥቅም ባላስቀደመ መልኩ በተቃኘ የዲፕሎማሲ ግንኙነት የተለከፈ፤ በፋሽስት አመለካከት የሚመራ አገዛዝና በዚሁ ሳቢያም ዜጎችን ለርሃብና ለስደት የዳረገ እጅግ ጠባብና ጎጠኛ አገዛዝ በመሆኑ ዛሬም ሆነ ወደፊት ስናፍርበት የምንኖር ነው ፋሽስት ወያኔና አገዛዙ። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on December 15, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , , ,

ብአዴን ውርደቱን የተከናነበበት እና ስድቡን የጠጣበት ዝግጅት በኦጋዴን

 

የራስን እድል በራስ መወሰን፣ እርስ በርስ እስከ ማጣላት…

ዘንድሮ በኢትዮጵያ ተከበረ የተባለውን የብሄሮች  ቀን ምን ያህሎቻችሁ እንደተከታተላቹህ አላቅም። ላላያችሁት ግንዛቤ ለመፍጠር ያህል… ዘንድሮ በአሉ የተከበረው ሱማሌ ክልል፣ በኦጋዴን ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን በመንገር ወጋችንን እንጀምራለን። ይህ ዝግጅት እስከዛሬ በትግራይም፣ በአማራውም ክልል ተደርጓል… ሆኖም በአሉ ላይ ሁሉም የየብሄሩን ባህል ለማሳየት ሲጥር እንጂ፤ አንደኛው ብሄር ሌላውን ሲሰድብ ያየንበት አጋጣሚ አልነበረም። የዚህ አመቱ የብሄር ብሄረሰቦች ወይም የብሄረተኞች ቀን ሌላውን ኢትዮጵያዊ በመውቀስ ላይ የተመሰረተ ነበር። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on December 13, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , , , ,

የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ፪ – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

harar

ባለፈው ሳምንት የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካን ተጨባጭ እውነታዎችን ቃኝቼ ተከታዩን ክፍል በይደር አቆይቼው እንደነበረ ይታወሳል፤ እነሆም ዛሬ እንዲህ እቀጥላለሁ፡-

ሐረር እንደ ማሳያ

(መቼም ኢህአዴግ በብቸኝነት የሚኩራራበት የፖለቲካ ‹ስኬት›፣ ለዘመናት አንድ ሆኖ የኖረ ሕዝብን ‹ብሔር ብሔረሰቦች› በሚል ከፋፋይ የ‹ክርስትና ስም› እጥምቆ በአደባባይ ማስጨፈር ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ርግጥ ነው በአንድ ወቅት በፍትህ ጋዜጣ ላይ ‹‹የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከ መጨፈር›› በሚል ርዕስ የታተመ መጣጥፍን ተከትሎ ‹ፀረ-ብሔር ብሔረሰቦች› ተደርጌ በተመሰረተብኝ ክስ ፍርድ ቤት መመላለሴ ዛሬም ድረስ መቋጫ አላገኘም፤ ርግጥ ነው ኢትዮጵያውያን ወንድም እህቶቼ በስታዲዮሞች እየተሰባሰቡ የራስ ፀጉራቸው ላይ ላባ ሰክተው፣ ቆዳ አገልድመው እየዘለሉ ትርኢት ከማሳየት ባለፈ የመልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ መብቶቻቸው ተጠቃሚ መሆን አልቻሉም፡፡ …እውነታው ይህ ቢሆንም ወደ አጀንዳችን /የከሸፈው ፌደራሊዝምን/ ወደ መፈተሹ በአዲስ መስመር እንመለስ፡፡

ቋንቋን መሰረት ያደረገው ኢህአዴግ ሰራሹ ‹ፌደራሊዝም› አወቃቀር የሀገሪቱ መፃኢ ዕድል የተቋጠረበት ‹የሰዓት ቦንብ› መሆኑን ለመረዳት የምስራቅ ኢትዮጵያዋን ሐረር እንደ መሳያ መውሰዱን ግድ የሚያደርጉ በርካታ ገፊ ምክንያቶች አሉ፡፡ እንደሚታወቀው የሐረር ከተማ አመሰራረት ብዙሃኑ ህዝብ ከሚኖርበት ‹ጀጎል› ከተሰኘው በግንብ የተከለለ ቅፅር ጋር ይያያዛል፡፡ በ16ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ራሳቸውን ከብሔር ወረራ ለመከላከል በአካባቢው ነዋሪዎች እንደታነፀ በርካታ ድርሳናቶች የሚናገሩለት ጥንታዊውና ታሪካዊው የጀጎል ግንብ በአምስት (ሐረር፣ ኤረር፣ ሠንጋ፣ ቡዳ እና በርበሬ በር በሚባሉ) በሮች የተከፋፈለ ነው፡፡ Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on December 12, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , , , , ,

ትግላችን የሞተን ከመሸኘት፣ ለታሰረ ከመጮህ በላይ እና ዘላቂ ይሁን

ከይኸነው አንተሁነኝ

ታህሳስ 8 2013

ኢትዮጵያዊያን በዓለም ዙሪያ ካሉትም ሕዝቦች በተለየ መልኩና ላቅ ባለ መንገድ ሀገራችንን እንደምንወድ ይታወቃል። የሀገራችን ሉአላዊነት ሲደፈር ክብሯ ሲነካ አንድነቷ ጥያቄ ውስጥ ሲወድቅ እገሌ ከገሊት ሳይባል ሁሉም በያለበት ያቅሙን ሲያደርግ ኖሯል እያደረገም ይገኛል። የወገኖቻችን ማንነት ሲናቅ ሲዋረድም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በያለበት ጮሗል፣ አልቅሷል፣ አዝኗል። ከሰላማዊ ሰልፍ እስከ ገንዘብ ማዋጣት በመተባበርም የተፈጠረውን ችግር ለማስወገድ ከፍተኛ ርብርብ ሲያደርግ እንደነበር የሚታወቅ ነው። አሁንም በሳውዲ አረቢያና በአካባቢው እየደረሰ ላለው የወገን እንግልትና ግድያ በከፍተኛ ሁኔታ በቁጣ ገንፍሎ በመውጣት ችግሩን የዓለም ማሕበረሰብ እንዲያውቀውና ወገኖቻችን እየደረሰባቸው ካለው ስቃይ እንዲላቀቁ ለማድረግ ለወገኖቻችን አርነት ከፍተኛውን ትግል በማድረግ ላይ ይገኛል። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on December 8, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , ,

ኢሳትና አበራ የማነአብ ክፍል አንድ እና ሁለት (ቪዲዮ)

አበራ የማነ አብ  በተማረውና ፖለቲካ ቀመስ በሆነው ኢትዮጵያዊ ዘንድ ስማቸው አዲስ አይደለም። ፋሽስት ወያኔ ሀገራችንን ከተቆጣጠረ ማግስት ጀምሮ በእስር ላይ ከቆዩ በሗላ በቅርቡ ከእስር መለቀቃቸው የሚታወስ ነው። ስለሆነም ኢሳት ከትግል በፊት በተማሪነታቸውና ከዚያም በሗላ በነበራቸው  የፖለቲካ ሂዎት ዙሪያ ሰፊ ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸዋል። የዚህንንም ቃለምልልስ ቀዳሚ ሁለት ክፍሎች እንደሚከተለው ቀርቧል። መልካም እይታ። ቀሪውንም ክፍል ተከታትለን እናቀርባለን።

http://ethsat.com/video/esat-yesamintu-engeda-abera-yemane-ab-november-2013/

http://ethsat.com/video/esat-yesamintu-engeda-abera-yemaneab-december-2013-part-2/

 
Leave a comment

Posted by on December 8, 2013 in AMHARIC, VIDEO

 

Tags: , , , , ,

ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለዳ አይቀበለውም

ከይኸነው አንተሁነኝ

ህዳር 5 2013

ሁሉም ሰው ሰው በመሆኑ ባቻ የሚያገኛቸው ሰብአዊ መብቶች እንዳሉት ሁሉ፤ በዜግነቱ ደግሞ ከሀገሩ የሚጠብቃቸው መንግስታዊ እገዛዎችና ከለላዎች እንደሚኖሩ እሙን ነው። በሕዝብ የተመረጠው ወይም ተመርጫለሁ የሚለው መንግስትም መርጦኛል የሚለውን ማሕበረሰብ ፍላጎት ለማሟላት መጣሩ የሚጠበቅ ከመሆኑም በላይ ከዜጎቹ አንዱ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ አደጋ ቢያጋጥመው አግባብነት ያለው ፍትህ እንዲያገኝ መሟገቱና ፍትህ እንዲያገኝ መጣሩ ከመንግስታዊ ግዴታዎቹ ውስጥ እንዱና ዋነኛው ነው። ይህ እንግዲህ እንደመንግስት መንግስታዊ ግዴታዎችን ለሚያስተዳድረው ማሕበረሰብ እያበረከተ ላለ መንግስታዊ አካል የሚሰጥ ሃላፊነት ነው። መንግስትነትን መስም ብቻ ተጎናጽፈው እንደሚገኙት ፋሽስት ወያኔ አይነቶቹ ግን ሁሉም ነገር ነግድ ነው። የዜጎች ሰላምና ጤንነት እንዲሁም የሀገር ድንበር መከበርና ሉአላዊነትም እንኳ ቢሆን ከወያኔ ባለስልጣናት ጥቅም አኳያ የተቃኘ ነው። በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያለው የዜጎች ሁለንተናዊ ሰላም ከወያኔ ፖለቲካና የስልጣን ዘለቂነት አንጻር የተለካ ነው። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on December 5, 2013 in AMHARIC, ARTICLE, POEM

 

Tags: , , , , ,

የሳውዲ መንግስት የማሰርና የማሳደድ፤ የመግረፍና የመግደል ሉአላዊ መብት አለው፡- ሽመልስ ከማል

ከይኸነው አንተሁነኝ

ታህሳስ 5 2013

ሀገሮች ሕዝባቸውን የሚያስተዳድሩበት የውስጥ ህግ እንዳላቸው ሁሉ በሌላኛው ሀገር የሚገኝ ዜጋቸውን ሰላም ከማስጠበቅ አንጻር ወይም ደግሞ  ንግድና መዋዕለ ንዋይ ፍሰትን የመሳሰሉ የሁለትዮሽ ግንኙነት የሚፈልጉ ጉዳዮችን በተረጋጋና የራሳቸውን ዜጋ በማይጎዳ መልኩ ለመከወን ይመቻቸው ዘንድ የጋራ ስምምነት ሊያደርጉ ይችላሉ። ይሁን እንጅ ማንኛውም የሀገር ውስጥም ሆነ የሁለትዮሽ ስምምነት ዜጎችን ለችግር የማያጋልጥ መሆን የሚጠበቅበት ከመሆኑም በላይ በዓለም አቀፍ ህግጋት መርህ የተቃኘ ሊሆን ይገባዋል። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on December 5, 2013 in AMHARIC, ARTICLE, POEM

 

Tags: , , , , ,