RSS

Monthly Archives: April 2013

ሕወሃት- አድሮ ጥጃ

ይኸነው አንተሁነኝ

ሚያዚያ 30 2013 

እንደ ሀገራችን ወግና ባህል እንደ እድሜ ጠገቦቹ አባቶቻችንና እናቶቻችን ትውፊት ስለራስ ስራና ታታሪነት ሌሎች ሰዎች ሲናገሩልን እንጅ እኛው ስንለፈልፈው አያምርም፤ ለዚያውም የተደረገ የተከወነ ታሪክ ከሆነ ማለቴ ነው። ከዚያም ሲያልፍ ስራችን እራሱ ስለሚናገር የኛን የራሳችንን ምስክርነት አይፈልግም። እንዲያ ካደረግን ግን ጉረኛ ከማስባሉም በተጨማሪ በራስ ብቻ መታበይን ሊፈጥር ይችላልና ነው። እንግዲህ ቀደም ብየ እንዳልኩት ይህ ሁሉ በእርግጥ የከወነው ስራ ካለ ማለት ነው። ይሁን እንጅ አንዳንድ ሰዎች ከወግ ባህላችንና ከእድሜ እኩዮቻቸውም እረ ከታናናሾቻቸው ስርአትም ባፈነገጠ መልኩ ሲዘባርቁ ይታያሉ። የሰው ማንነቱ በማይታወቅበት ስራው በማይነገርበት የቀን ተቀን እንቅስቃሴው በማይታይበት ሀገር ቢሆን ያሻውን ቢያወራ እንዲህም እንዲያም ነኝ ቢል አይታወቅምና ቢያንስ እስኪታወቅ በመጠኑም ቢሆን ተቀባይነት ሊያገኝ በቻለ ነበር። እንደ ፀሐይ በጠራ ብርሃን በሚነበብበት ሀገር ሲነገር ግን ያስተዛዝባል ያስተቻል ያቀላል ያዋርዳልም በተለይ የቀረ ያልተዋረደ ክብር ያልቀለለ ማንነት ላለው ማለቴ ነው።

 የዚህ ጽሁፍ መነሻም ሆነ መሽከርከሪያ የህወሃት የጥፋት መሃንዲስ የሚባልለት ተነጋጋሪውና አነጋጋሪው ሽማግሌው ስብሃት ነጋ ባንድ አታካች ንግግሩ “ሕወሃት ኢሕአዴግን የመሰለ ፓርቲ በአፍሪካ የለም” ብሎ የተናገረው ነው። መቼም እኔም ካልተሳሳትኩ ይህ ንግግር ለኢትዮጵያዊያን የተነገረ ነው። ሕወሃት ኢሕአዴግን ግጥም አድርገን ለምናውቅ፣ ማስረጃ ማቅረብ ቢያስፈልግ እስከ አገጭ ጢም አድርን ለምናቀርብ ኢትኦጵያዊያን፣ ታሪኩን መዘርዘር ቢያስፈልግ ከምስረታው እስካለንበት ድረስ የከወናቸውን ድርጊቶች ከቦታና ጊዜ ጋር አቀናጅተን ለምናቀርብ ዜጎች መነገሩን ስናስታውስ እውነትም  “ባለጌ አፉን እንጅ እግሩን አያድጠውም” የሚባለውን እናረጋግጣለን። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on April 30, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , ,

በስዊድን የኢትዮጵያ ቆነስላ ሰራተኞች በኖርዌ ሊያደርጉት የነበረው የአባይ ቦንድ ሽአጭ ለሁለተኛ ጊዜ ተቃረጠ (ቪዲዮ)

 
Leave a comment

Posted by on April 28, 2013 in AMHARIC, VIDEO

 

Tags: , ,

“የተዘነጉት እስረኞች” እና የተዘነጋው የቤተሰቦቻቸው ስቃይ

ላለፉት አራትዓመታት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቅዳሜ እና እሁድ የሄደ ሰው ወጣቷን ናርዶስን ሳያገኝ አይመለስም፡፡ ናርዶስ ገና የ20 ዓመት ወጣትእና በኪያሜድ የመጀመሪያ ዓመት የነርሲንግ ተማሪ ናት፡፡ ናርዶስ ዘሪሁን በየሳምንቱ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትመላለሰው በ‹‹አሸባሪነት›› ‹በእነብርጋዴር ጄኔራልተፈራ ማሞ መዝገብ› ከተከሰሱት 36 ሰዎች መካከል ዕድሜ ልክ የተፈረደባትን እናቷን ልትጎበኝ ነው፡፡ እነዚህ እስረኞች ሚያዝያ16/2001 አመሻሹ 12 ሰዓት አካባቢ ነበር ሁሉም በያሉበት በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡ እኛም 4ኛ ዓመታቸውን ለማሰብ ተሰባስበንወደቃሊቲ ማረሚያ ቤት በተለይ እማዋይሽ ዓለሙን ለመጠየቅ ሄደን ነበር፡፡ እንደተለመደው ናርዶስንም አገኘናት እና ብዙ ነገሮችንአጫወተችን፡፡

ናርዶስ ትረካዋን የጀመረችው እናቷን እና ሌሎችም በተመሳሳይ መዝገብ ተከሰው የተፈረደባቸውንሰዎች አያያዝ ነበር፡፡ ‹‹ሳስበው የተረሱ ያህል እየተሰማኝ ነው፤ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ሚዲያዎች ስለነሱ አይደለም እያነሱ ያሉት፡፡በእናቴ ክስ የታሰሩት ከ30 ሰዎች በላይ ናቸው፡፡ አንድ ሰሞን ከይቅርታ ጋር በተያያዘ ስማቸው እየተነሳ ነበር አሁን ግን ሁሉነገር የተረሳ ይመስለኛል›› በማለት የእስሩ ሕመም ለታሳሪዎቹ እና ለቤተሰቦቻቸው ግን የሚረሳ ዓይነት አለመሆኑን ነገረችን፡፡

‹‹ሚያዝያ16፣ አርብ ቀን ነበር ሁሉም የተያዙት›› በማለት ሲታሰሩ የነበረውን ጠቅላላ ሁኔታ በማስታወስ ትጀምራለች፡፡ ‹‹ለአንድ ሰው የመጡየማይመስሉ ብዙ ሲቪል የለበሱ እና የፌዴራል ፖሊስ ልብስ የለበሱ ፖሊሶች መሳሪያቸውን አቀባብለው ነበር ወደቤት የገቡት፡፡ ስልካችሁንአጥፉ ወደማንም እንዳትደውሉ አሉን፡፡ የብርበራ ማዘዣ ይዘው ነበር፤ ‹ቤት ልንፈትሽ ነው የመጣነው እማዋይሽ ዓለሙ በቁጥጥር ስርውለሻል› አሏት ቤት ፍተሻው እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ ቀጥሏል፡፡ ቀኑ አርብ ነበር፤ እናቴ ደግሞ እስከ 12 ሰዓት ትጾምስለነበር ከሥራ ወደቤት እንደገባች ‹ምግብ ስጡኝ› እያለች እያለ ነበር ፖሊሶች የገቡት ስለዚህ ምግብ ሳትበላ ውላ ነው ወደ እስርቤት የወሰዷት፡፡ ከዚያ በኋላ አራት ወራት ያክል ዓይኗን አላየነውም ነበር፤ ትሙት ትኑር የምናውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ደግነቱ በሌላ ጉዳይ ታስራ በተፈታች ሴት አማካይነት መልዕክት ደረሰኝ፡፡ ‹አንቺደህና ከሆንሽ ሽሮ እና ጎመን ሰርተሸ አስገቢልኝ፤ እኔ ደግሞ ደኅንነቴነን የባናና ማስቲካ ወረቀት እልክልሻለሁ፡፡ ደኅና ካልሆንኩኝግን ያ ነገር ይቀራል› ብላ ላከችብኝ፡፡ ከዚያ እኔም ሽሮ እና ጎመን ሠርቼ በመላክ፣ እሷም የባናና ወረቀት በመላክ ደኅንነታችንንየሚገልፅ መልዕክት እንለዋወጥ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት ሰዓት እኛ በሌለንበት ጉዳያቸው ፍርድቤት ይታይ ነበር፡፡›› በማለትጉዳያቸው በኢፍትሐዊ መንገድ በመንግሥት እንደተያዘ አጫውታናለች፡፡ Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on April 28, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , ,

ኢትዮጵያና ኤርትራ በሰብዓዊ መብቶች አያያዛቸው ተወቀሱ

 

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤትበኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ የዜጎች ነፃነቶች ጉዳይ አሣሣቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርቱ አስታወቀ፡፡

ሪፖርቱ ኢትዮጵያን በተለይ የተመለከታት ፀረ-ሽብር ሕጓን ጋዜጠኞችን ለማሣደድ ጉዳይ የተጠቀመችበት መሆኗን ገልፆ በዓመቱ ውስጥ ጋዜጠኞቹ ውብሸት ታየ፣ ርዕዮት ዓለሙ እና እስክንድር ነጋ የተከሰሱትና የተፈረደባቸው ፀረ-ሽብር አዋጁን ተላልፋችኋል ተብለው መሆኑን አመልክቷል፡፡

ሌሎች ስድስት ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት ፅሁፍ አውጭዎች ወይም ብሎገሮች በሌሉበት ጥፋተኝነት የተበየነባቸው መሆኑን በአጠቃላይም የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላትና የፖለቲካ ተዋንያንን ጨምሮ 31 ሰዎች በዚሁ ሕግ የተፈረደባቸው መሆኑን ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የዘፈቀደ ግድያዎች መፈፀማቸውን፣ በእሥረኞች ላይ የሥቃይ አድራጎትና አያያዝ መከናወኑን፣ በትምህርት ሂደት ነፃነት ላይ ገደቦች መጣላቸውንና በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መገባቱን ሪፖርቱ አትቷል፡፡ Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on April 25, 2013 in AMHARIC, NEWS

 

Tags: , , , ,

የህወሀት ደህንነቶችን ጤና የነሳው የፌስቡክ ጦማር

 

Ethiopian blogger Abraha Desta from Tigry, Mekeleበህወሀት/ኢህአዴግ ውስጥ መግባባት ጠፍቷል፣ የወያኔ ቁንጮዎች ወዴት እንደሚሄዱ አያውቁም። እንደው በደፈናው “የመለስ ዜናዊ ራዕይ” ይበሉ እንጂ ራዕዩን እነርሱም አያውቁትም። ካድሬውም ሹማምንቱም እርስ በርስ ተናንቋል። በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ሁኔታቸውን ህዝብ እንዳያውቅባቸው እያደረጉ ያሉት ጥረት እምብዛም የሰራ አይመስልም። የሙስሊሞች ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው፣ በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ግፍ ህዝቡን ከዳር እስከዳር አስተባብሯል/ቀስቅሷል፣ ምርጫውን ምርጫ ለማስመሰል ያደረጉት ጥረት አልተሳካም፣ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ አለማቀፉ ማህበረሰብ እና ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ጫና ፈጥረዋል። ለዚህም ይመስላል የወያኔ የደህንነት ሹሞች የሀሰት ዜናዎችን በፌስቡክ እያሰራጩ ፋታ ለማግኘት የሚጣጣሩት። ከዚህ በታች አብረሃ ደስታ ከመቀሌ በፌስቡክ የለቀቀውን ጦማር፣ የህወሃት/ኢህአዴግን ወቅታዊ አቋቋም እንደወረደ አቅርበነዋል።

በህወሓት የጉባኤ ኣጀንዳ ዙርያ ስብሰባ ሊጠራ ነው

አብረሃ ደስታ፣ ከመቀሌ
ከኢህኣዴግ ጉባኤ በኋላ መሪዎቻችን (ከበፊቱ ብሶባቸው) መግባባት ኣቅቷቸዋል። በፌደራል ደረጃ የሚደረጉ ስብሰባዎች ያለ ዉጤት ይጠናቀቃሉ። ለምን ኣይግባቡም? (‘ቀሽም ጥያቄ’)። የሚያግባባ ነጥብ የላቸውማ። ድሮ (ከ‘ባለራእዩ መሪ’ ዕረፍት በፊት) ሁሉም ነገር እሳቸው ይሰሩት ስለነበር) በመሪያቸው ነበር ‘የሚግባቡት’ (አብረው የሚጓዙ)። በሰው ‘ይግባባሉ’ (ሌላ ሊያግባባቸው የሚችል ሓሳብ ወይ መርህ አልነበራቸውም፣ የላቸውም)። አሁን ታድያ እንዴት ይግባቡ? Read the rest of this entry »
 
Leave a comment

Posted by on April 25, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , ,

”ፍየል ወዲህ…”

ይኸነው አንተሁነኝ

ሚያዚያ 23 2013

“ከእንግዲህ የገበሬው ችግር የርሃብ ችግር ሳይሆን የሚያመርተውን የተትረፈረፈ ምርት በርካሽ እንዳይጥለውና በገንዘብ መልክ የሚኖረው ገቢ እንዳያንስበት ነው፡፡” ባለራዕዩ መለስ ዜናዊ በዘመነ አካለ ስጋው የወሸከተው ደርዝ የሳተ ቃል

የተለያዩ መንግስታት ሕዝባቸውን ለማስተዳደርና ቁሳዊ መንፈሳዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት፣ የሀገራቸውን ጸጥታና ደህንነት አስጠብቆ ለመምራት፣ እንዲሁም ከሌላው ዓለም ጋር ጥቅምን ያገናዘበ ግንኙነት ለመመስረት የሚያግዙ የተለያዩ ፖሊሲዎችን ያጸድቃሉ ይተገብራሉም። አፈጻጸሙንም በተመለከተ የተለያዩ መመዘኛዎችን በማውጣት ይከታተላሉ፤ ተጠቃሚውን ምሕበረሰብ መሰረት ያደረገ የእርምት እርምጃዎችንም መውሰድ ከአንድ መንግስት ነኝ ከሚል አካል የሚጠበቅ ሃቅ ነው። ይህ ሲሆን እንግዲህ የተዘጋጁትን ፖሊሲዎች፣ አተገባበራቸውንና ሊያመጡ የሚችሉትን ውጤት በተመለከተ የሚወጡ መንግስታዊ ቅድሚያ መግለጫዎችም ሆኑ ማብራሪያዎች ከዚያም ሲያልፍ እቅዶችና የተስፋ ቃሎች በሙሉ በባለሙያ የተቃኙና በመሰረታዊ የትንበያ ሳይንስ የተዳሰሱ ሊሆኑ መቻላቸው አያጠያይቅም እጅግ በጣም ቢያንስ ሃላፊነትና ተጠያቂነት ለሚሰማቸው መንግስታት።

እስከ አሁን ያልነውን ሀቅ ይዘን ወደ ሀገራችን ስንመጣና ከላይ የተጠቀሰውን የባለራዕዩን ንግግር ከዚህ ሀቅ ጋር ስናወዳድር በፓርላማ የጭብጨባ አጀብ ሞቅታ፣ በጉሽ ጠላ ብርታት አልያም በምርቃና መንፈስ የተነገረ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር አይኖረንም። ምክንያቱም ያለ እረፍት ለዘመናት ስትታረስ የኖረችና ለምነቷን ያጣች የበሬ ግንባር የምታክል መሬት ይዞ ዓመት ሙሉ የሚቆዝምን ገበሬ የትኛው የግብርና ፖሊሲ የተትረፈረፈ ምርት ባለቤት ሊያደርገው እንደሚችል ከባለራዕዩ በቀር የሚያውቅ የለምና። ባለፉት ጥቂት ዓመታትም የታየው ገበሬው የተትረፈረፈ ምርቱን የሚሸጥበት ገባያ ሲያጣና እንደተባለውም በርካሽ ሲሸጠው ሳይሆን ልሰው የማያውቁ ልሰው ወይም ቀምሰው የማያውቁ ቀምሰው የእህል ዋጋ ከመቸውም በላይ ሲወደድ ነው። “የግፍ ግፍ…” እንደሚባለው ይራበውም ይጥማው ያችኑ ቁራጭ መሬት ይዞ የሚያዘግመውን ገበሬ ሕወሃት መራሹ ገዥ በልማትና ኢንቨስትመንት ሰበብ እያፈናቀለ ለልመናና ለባሰ ግፍና በደል እየዳረገው መሆኑ ሲታይ የባለራዕዩ ንግግር በሞቅታ እንጅ ጥናትን መሰረት ያደረገ እንዳልነበረ ያሳያል። የሚታየው ያገጠጠ እውነት ያረጋገጠውም ገበሬው ትርፍ አምርቶ ሲደሰት ሳይሆን ከትናንሽ እስከ ትላልቅ ከተሞቻችንን ወረራ በሚመስል መልኩ በስደት ሲያጥለቀልቅ ነው። የቀረውም Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on April 23, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , , ,

Ginbot 7 Democratic: Can You Put up or…

 by Ersasu Mere

For several decades, Ethiopians have been yearning for democracy, equality and the prevalence of the rule of law.Put Up Or Shut Up Citizens from every walk of life, groups and parties are confronting the brutal and dictatorial Ethiopian regime to change its political discourse towards the implementation of a democratic system that honors and respects its people and reserve their right to live happily and speak freely. To our chagrin, in spite of tremendous effort and sacrifice, our aspiration to see a responsible government has not been brought into fruition. One can recite a laundry list of reasons for our failure.  I think we all agree that amongst all the causes that perpetuate the undemocratic life of the ruling government, the opposition parties’ lack of compromise to work together and to galvanize the general public to one direction is the bitter reality we all have a hard time to swallow. In our recent history, it almost has become a fad that opposition parties are prone to split and that most likely will lead them to their own eventual demise.  In the meantime, it sad to see the agony and the emotional distress the compatriots are going through.  It is in our freshest memory to remember how we were indulged to relive the excruciating emotional pain and utter despair caused by the Kinjit debacle. With the advent of Ginbot 7, we hoped the days of political bickering to nourish individual or group interests and the days of distraction from within are over. Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on April 19, 2013 in ARTICLE, ENGLISH

 

Tags: , , , ,

Protest rally in Oslo, Norway: Against the recent forceful eviction of Amharas

Image

Ethiopians in Norway have held a great and spectacular demonstration opposing the recentevictions of ethnic Amharas from different parts of Ethiopia and demanding freedom in Ethiopia.

The demonstrators in their huge numbers showed their anger and frustration walking through the main street in Oslo and chanting slogans denouncing the barbaric act of the TPLF regime and demanding democracy and regime change in Ethiopia. Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on April 19, 2013 in ENGLISH, NEWS

 

Tags: , , , ,

ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ፦ አንድ

መስፍን ወልደ ማርያም

በአለፉት ሠላሳ ዓመታት በኢትዮጵያ የለውጥ እንቅስቃሴ ላይ እንደኢሳት (የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዥንና ራዲዮ) ያለ ኃይል የትኛውንም የኢትዮጵያ አገዛዝ አጋጥሞት አያውቅም፤ በመሠረቱ የኢሳት መሣሪያነት ከባህል ውጭ ቢሆንም የባህል ይዘት አለበት፤ ወደኋላ አመለክታለሁ፤ ወደድንም ጠላንም የኢትዮጵያ ታሪክ በመሠረቱ ሁሌም በኃይል ላይ ቆሞ በኃይል የሚሽከረከር ነው፤ በአለፉት አርባ ዓመታት ውስጥ የመጡት አብዮተኞች ሁሉ ይህንን በመሠረታዊነት የመክሸፍ ምንጭ የሆነውን የጉልበት አምልኮት እንደዓላማም እንደመሣሪያም ይዘው የተነሡ ናቸው፤ ዛሬም ቢሆን ተሸናፊዎችም ሆኑ አሸናፊዎች አብዮተኞች የሚያወሩትና የሚጽፉት ከጉልበተኛነት ከረጢታቸው ሳይወጡ ጥፋታቸውን እንደልማት፣ አላዋቂነታቸውን እንደብልህነት በማድረግ ራሳቸውን አታልለው ሌላውን ለማታለል እየሞከሩ ነው፤ አንድም የከሸፈ አብዮታዊ መሪ ያለጠዋሪ ልጅ የቀሩትን እናቶችና አባቶች፣ የብልጣብልጦች መሣሪያ ሆነው እንደወጡ የቀሩትን ወጣቶች በኃላፊነትን ተቀብሎ በእውነት የሚዘክራቸው የለም፤ እነዚያ በየሜዳው በጥይት ነደው ጅብና አሞራ የበላቸው ወጣቶች እንደማንም ሰው ሕይወትን ለማጣጣም የሚያስችሉ ሌሎች ዓላማዎች ነበሩአቸው፤ ዛሬ ‹‹መስዋእት ሆኑ›› እየተባለ ይነገርላቸዋል፤ ዶሮን ሲያታልሏት ዓይነት ነው፤ ይህንን የሚሉት የራሳቸውን ሕይወት እየሳሱለት ጠብቀው በሌሎች ሕይወት ጉልበተኞች ለመሆን የተመኙት ናቸው፤ በወጣቶቹ አጥንት ላይ ጉልበተኛነታቸውን የተከሉት አጥንቱ እየቆረቆራቸው ይባንናሉ ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፤ በወጣቶቹ አጥንት ላይ ከአሜሪካ የመጣ ድርብርብ ፍራሽ ስላነጠፉበት አጥንቱ መኖሩንም አያስታውሱትም፤ ዛሬም የሚሳሱለትን ሕይወታቸውን በሰፊ ግምብና በታጠቁ ወጣቶች አጥር ይጠብቃሉ፤ በአንጻሩ በምኞት የቀሩት ከንፈራቸውን እየነከሱ ከጠርሙስ ጋር ይታገላሉ፤ ከምኞት ባርነት ወጥተው ለንስሐና ለነጻነት ገና አልበቁም፤ ለንስሐ ሳይበቁ የሞቱም አሉ፤ የመክሸፍ ክፉነት እውነትን ፊት-ለፊት የመጋፈጥ ወኔ ሳያገኙና ንስሐ ሳይገቡ ከነኃጢአት በወጣቶች ደም ተጨማልቆ መሞት ነው፤ የከሸፈውን እንዳልከሸፈ፣የከሰረውን እንዳልከሰረ፣ተሸንፎ የተንኮታኮተውን እንዳልተሸነፈ እያደረጉ የሬሳ ቀረርቶ ማሰማት የማይሰለቻቸው ሞልተዋል፤ ወደፊት መግፋት የሚቻለው ሬሳ ሬሳን ተሸክሞ ሳይሆን፣ ስሕተትን አርሞ የሞተውን ቀብሮ ነው። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on April 18, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , , ,

“ታላቋ ትግራይን” የመመስረት የ 21 ዓመታት ጉዞ

kae

በ1968 ዓ ም ባወጣው ማንፌስቶ ህወሓት “ታላቋን ትግራይ” ከኢትዮጵያ ገንጥሎ የራሷን ሪፐብሊክ እንድትመሠረት የማድረግ ግብ ነድፎ እንደነበር የግንባሩ መስራች አባላት የመሰከሩት ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያዊነቱ በሚኮራው የትግራይ ሕዝብ ማንፌስቶው ተቀባይነት እንደማያገኝ የሕወሓት መሪዎች ሲረዱ ትተነዋል ብለው ቢያውጁም እነመለስና ስብሀት ግን ለ 21 ዓመታት ሲፈፅሙት የኖሩት ያን ግብ ለማሳካት ነበር። ዋና ዋናወቹን ክንውኖች እንመልከት፦

1ኛ. ህወሓት ጫካ እያለ የሰራውን “የታላቋን ትግራይ” ካርታ እውን ለማድረግ ከጎንደርና ከወሎ ሰፋፊ ለም መሬቶችን በማንአለብኝነት በመውሰድ ወደትግራይ ከለለ። ኢትዮጵያን በዘር ሸነሸነ፤ ኢትዮጵያዊያንን በዘር በመከፋፈል ስለ አንድነታቸው ሳይሆን ስለልዩነታቸው እያሰቡ እንዳይተባበሩ ለማድረግ ተጣጣረ፤ በኢትዮጵያዊነት ላይም ዘመተ።

2ኛ. ሕወሓት ባረቀቀው አዲስ ህገ መንግስት “የራስን ዕድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል ድረስ” የሚል አንቀፅ አስገባ፤ በአንቀፅ 39 ላይ ተቃውሞ ሲነሳ መለስ ንዴቱን መቆጣጠር ተስኖት በቁጣ መልስ ይሰጥ እንደነበር እናስታውሳለን። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on April 18, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , ,