RSS

All world dances came from Nile valley (Video)

http://www.ethiotube.net/video/32208/Must-Watch-Ethiopian-American-Filmmaker-Haile-Gerimas-inspirational-speech-in-Philadelphia–September-2014

 
Leave a comment

Posted by on October 16, 2014 in AMHARIC, VIDEO

 

Tags: , , ,

ጀግንነትህ የገባኝ ዛሬ ነው

 

ስምን መላክ ያወጣዋል አሉ!!! ”አንዳርጋቸው” አሉህ እውነትም አንዳርጋቸው። የዚያን ትውልድ ዓላማ፣ ቁርጠኛነትና ፍቅር፤ ተስፋ አይቆርጤነት፣ ጥንካሬና የአመራር ብቃት ያየንብህ ታላቅ ሰው፤ በራስህ ትውልድ የጀመርከውን የነፃነት ጉዞ ለመቋጨት ከጓዶችህ እጅግ ወርደህ ይህን ትውልድ ስለ ሀገር አንድነትና ሉአላዊነት፣ ስለ ሰው ልጅ ክብርና እኩልነት፤ ስለ ነፃነት አስፈላጊነት በተለይም በዘመንህ አሳምረህ የምታውቃቸው ጠባቦቹ ወያኔዎች በሀገራችንና በወገናችን ላይ እያደረሱት ያለውን ዘመን አይሽሬ ጭካኔና ክህደት ለማስተማር ለማሳወቅና ለማሰልጠን ብሎም በትግል ነፃ መውጣትን በተግባር ለማሳየት ከአውሮፓ ዉብ ከተማ በርሃ ድረስ የወረድክ ምሳሌ የማይገኝልህ ንዑድ ኢትዮጵያዊ ነህ።

”አንበሳው በጅቦች ተከቦ አየሁት” አለ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ እውነት ነው ከምንም በላይ ገዝፈህ ”ልብ ካላችሁ ኑና ግጠሙን” ሲል የነበረውን ወያኔ በፈለገው ቋንቋ ለማናገርና የፈለገውን ለማሳየት ባደረከው ውጠታማ ጉዞ ገና በሩቁ ውሃ ያስጠማህ ያንበሶች አንበሳ ነህ አንዳርጋቸው። ላለፉት ከ 40 ዓመታት በላይ በሚያስደንቅ ጥንካሬ፣ ሀቀኝነትና ታማኝነት ጎልተህ የምትታይ በሳል ፖለቲከኛ፤ የእኩልነትና የመፈቃቀር ተምሳሌት ነበርክ ነህም። እናም በአንክሮ ከማስተዋልህ ጀርባ፣ እናም ከእርጋታህና ከትግስትህ ጀርባ፣ እናም ከምክርህና ከአርቆ አስተዋይነትህ ጀርባ ያለው ማንነትህ፣ ያለው ጀግንነትህ የገባኝ ዛሬ ነው። አወ ጀግንነትህ የገባኝ ዛሬ ነው።

ጀግንነትህ የገባኝ ዛሬ ነው 

አብረን እንደግ እንጅ በመለያየት አንጥፋ

እንደጋገፍ እንጅ አንዳችን ላንዳችን አንክፋ

ሁላችን አንድ አይነት ሰው ነን

ጌታና ሎሌ የሌለን

ስለዚህ እኛው ለእኛ እንወግን Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on July 10, 2014 in AMHARIC, ARTICLE, POEM, VIDEO

 

Tags: , , ,

ለምን ይህን መረጠ – 1

ሰኔ 27  2014

በታላቁ መጽሐፍ ባንድ ቦታ ”እናንተ እንኳን ዝም ብትሉ ድንጋዮች አፍ አውጥተው ያመሰግኑኛል” የሚል ታላቅ መልእክት የያዘ ሃሳብ ትዝ ይለኛል። ሃይማኖታዊ ትንታኔውን ለጊዜው ወደ ጎን ትተን ጥቅል ሃሰቡን በግርድፉ ለመመልከት ብንሞክር እንኳ ሁሉም ባንዴ ዝም አይልም፣ ፈሪ ባለበት ሁሉ ደፋርም አለ፣ ዝምተኛ ካለ ተናጋሪም አለ፣ የሚጠበቁት የተዉትን ያልተጠበቁት ያነሱታል እና ሌሎችንም ብዙ ሃሳቦችን የያዘ መሆኑን መዘርዘር እንችላለን።

ወያኔ እንደ ጠባብ ቡድንም ሆነ ወያኔዎች እንደ ግለሰብ ኢትዮጵያዊነት የሚሰማውን አንድ ድርጅት ወይም ጠንካራ ግለሰብ በማስወገድ ወይም በማዳከም ኢትዮጵያን የማፈራረስ ምኞታችንን እናሳካለን ብለው ያስባሉ። የኢትዮጵያዊነት ጠንካራ መንፈስ በደማቸው ውስጥ እየፈላና እንደ እሳተ ገሞራ ቅላጭ እየነተረ መላ ሰውነታቸውን የሚያንቀጠቅጣቸውን ኢትዮጵያዊያን በማስወገድ፣ በማጥፋት ወይም በማሰር ያን ከኢትዮጵያዊያን ልብና ደም በላይ ወጥቶ በአረንጓዴ ቢጫና ቀይ ሕብር አምሮ በኢትዮጵያ ሰማይ የረበበውን ሃያል የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ያጠፉና ፍላጎታቸውንም ያሳኩ ይመስላቸዋል። ለዛሬ ግን ሕወሃት በሃይማኖት ተቋማት ላይ እያደረሰው ካለው ጥቃት በመነሳት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት ለምን እንደመረጠ በመመልከት እንጀምር። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on June 27, 2014 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , ,

ኢትዮጵያዊያንን መበታተን፤ ያልተሳካው የሕወሃት ራዕይ

ሚያዚያ 13 2014

አንድ ቡድን ወይም ድርጅት አንድን ችግር ነቅሶ አውጥቶ ሕዝብ እንዲከተለው ለማድረግ፤ የተነሳው ሃሳብ ወይም ችግር  የሕዝብ ጥያቄ መሆን ይኖርበታል። ችግሩን የመፍታት መንገዱም በሕዝብ ሙሉ እውቅናና ድጋፍ የሚንቀሳቀስ ሊሆን ይገባዋል። ብዙ ጊዜ ጥቂት የማይባሉ የፖለቲካ ድርጅቶች የራሳቸውን ፍላጎት በሕዝብ ስም ይዘው ቢነሱም የሕዝብ ድጋፍ በማጣታቸው እንደከሰሙ ከኢትዮጵያ የተሻለ ጥሩ ምሳሌ ልናገኝ አንችልም። እንደ ሕወሃት አይነቶቹ ደግሞ በበቀልና በጥላቻ አምጠው የወለዱት አማራን የመጥላትና ብሄሮችን የማጋጨት አባዜ የሕዝብን ይሁንታ ቢያጣም በመሳሪያ በማስፈራራት፣ በጥቅማጥቅም በመደለልና እንዲሁም እንደነሱ አይነት ጠባቦችን ከያካባቢው በማሰባሰብና ሕዝብን በመጫን የሕዝብ ጥያቄ ነው ብለው አርባ ዓመት ሙሉ የሙጥኝ እንዳሉ አሉ። ያም ቢሆን ግን የሚያፍር ህሊናና ዝም የሚል ምላስ የላቸውም እንጅ አካሄዳቸው አሁንም ትክክል እንዳልሆነና ፍጻሜያቸው ውድቀት እንደሆነ ከሕዝብ እየተነገራቸው እና እነሱም እያዩት ነው።

የሕወሃት ባለስልጣናት ከደማቸው በተወሃደው የአማራ ሕዝብ ጥላቻ እየተገፉ፤ ከሕዝብ በተዘረፈ ገንዘብ ነጋ ጠባ መልካም ነገር በማይወጣው ጉሮሯቸው በሚንቆረቆር የውስኪ ጉልበት እየተንደረደሩና በስጋ ብስናት እየታጠኑ አርባ ዓመታት ሙሉ ሰርተውት ደክመውበት ያላጠናቀቁትን የኢትዮጵያን ሕዝብ የመበታተን ራዕያቸውን ለመተግበር ዛሬም ድረስ እንቅልፍ አልተኙም። ዛሬም ሕወሃት ጉዳዩ አልጋባብ ሲወጠር እያላላ የላላ ሲመስለውም በሚመስለው መልኩ እየወጠረ ሕዝብን የማበጣበጥና የመለያየት ሰይጣናዊ ስራውን ገፍቶበታል። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on April 13, 2014 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , ,

የግዳጅ ሰልፍ በማዘጋጀት ሀቅን መሸፈን አይቻልም

ሚያዚያ 13 2014

በመጀመሪያዎቹ የወያኔ የአገዛዝ ዘመን አካባቢ ሕወሃት ሕዝብን ለማሳመንና የተሻለ መስሎ ለማታየት እጅግ ብዙ ማስመሰያ ድራማዎችን ሲከውን እንደነበር የቅርብ ጊዜ የሀዘን ትዝታዎቻችን ናቸው። በጊዜው ምንም እንኳ በአብዛኛው የሀገራችን ሕዝብ ያልተነቃበት ቢሆንም ከምሁራን አካባቢና በተለይም የጨካ ዘመን ታሪኩን ብጥር አድርገው በሚያውቁት ግለሰቦችና ባንዳንድ ዓለማቀፍ ተቋማት ዘንድ በጥንቃቄ መታየቱ አልቀረም ነበር። በሗላ ላይ ግን የሚሰሩት ወንጀሎች አይነትና ብዛት እየበዛና በሕወሃት በኩል የሚቀርበው የሽፋን ስእላቸውም የድፍረት እና በግግምና ዝም ብላችሁ እመኑን አይነት እየሆነ ሲመጣ ግን ሁሉም ፋሽስት ወያኔ የውሸት ተዋናይ መሆኑን ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱን የትወና ታሪክና ዘንግ ሳይቀር መተንበይ ጀመረ። እናም ዛሬ ሕወሃት ለልቅሶ ሳይቀር ትወና አጥንቶና አስጠንቶ እስከማጭበርበር ድረስ ተዳፈረ።

በእርግጥ በፊትም የሃውዜንን ሕዝብ ራሱ ባቀነባበረው የጭካኔ ተግባር ካማስጨፍጨፉና ባዘጋጃቸው የካሜራ ሰዎች ከያቅጣጫው ጥቃቱን አስቀርጾ ለዓለም በማሰራጨት እሪታውን ከማሰማቱም በፊት ቢሆን ተመሳሳይ ድራማዎችን በትግራይና በሰሜን ወሎ አካባቢ በሚኖረው ሕዝባች ላይ በመፈጸም ኡ ኡ እኔ አይደለሁም ሲል እንደነበር ”ማን ያርዳ የቀበረ…” ነውና ድርጊቱን በመቃወም ወደ ህዝብ የተቀላቀሉ ጓዶቹ ማጋለጣቸው አይዘነጋም። እናም ሕወሃት ለሕዝብ ቆምኩ ብሎ ጠመንጃ ካነሳበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በሕዝብ ላይ ሸፍጥ እንደሰራና ሕዝብን እንዳመሰ አለ። እኛም በግለሰብ ደረጃ እከሌ ጻፋቸው የማይባሉ በጣም ብዙ የሕወሃት የጥፋት ሽፋን ተውኔቶችን እንዳየን አለን። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on April 13, 2014 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , ,

በምንም ምክንያት ቢሆን ሀገርንና ሕዝብን በመክዳት ከህሊና ወቀሳ የጸዳ ሀብትም ሆነ ክብር ማግኘት አይቻልም!!!

መጋቢት 25 2014

ሀገራችን ኢትዮጵያ በወጣት ህዝቦች ከተገነቡት ጥቂት የዓለማችን አገሮች አንዷ ናት። ይህ ደግሞ ከሃገር ምርታማነት፣ ሀገርን ከውጭ ወራሪ ጥቃት ከመከላከል፣ የሀገርን አመራርና አስተዳደር በአስተማማኝ ደረጃ ላይ ከማስቀመጥ እና ለውጥን በፍጥነት ተቀብሎ በሚፈለገው ጥራት ወደሚፈለገው ውጤት ከመቀየር አኳያ ሲታይ እንደ ኢትዮጵያ ያሉት ሃገራት የወደፊት እድላቸው በጣም ሰፊና ያማረ እንደሚሆን በብዙ ሰዎች ይታመናል። ይህ ማለት ግን፣ ወጣቶቹ፤ መብትና ግዴታቸውን በትክክል ተገንዝበው በተገቢው ጊዜ ተገቢውን ርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል የመንፈስ ጥንካሬ እንደሚያሻቸው እርግጥ ከመሆኑም ባሻገር፣ መብታቸውን አስከብረው ግዴታቸውን ለመተግበር የሚያስችል ሁኔታ መኖርና አግባብ ካለው አካል ሁሉ ድጋፍና ማበረታቻ የሚያስፈልጋቸው መሆኑ ሳይዘነጋ ነው።

Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on March 25, 2014 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , ,

አትከፋፍሉን! አንድ ነን! ነፃነት ነፃነት ነፃነት!!!

መጋቢት 21  2014

ፋሽስት ወያኔ የተለያዩ ማባበያ መነገዶችን በመጠቀም፣ አንዳንድ ችሮታዎችን በማዘጋጀትና ይህም ሳይሆን ሲቀር ሃይልን በመጠቀም ጭምር የኢትዮጵያን ሕዝብ በስሩ ለማሰለፍ ሲጥር የቆየና እየጣረ ያለ ቢሆንም ከጥቂት ሆዳሞች በቀር ሰፊውን ሕዝብ ለመያዝ አልተሳካለትም። ሆዳሞቹም ቢሆኑ ለአላማቸው ሆዳቸውን ለሞሙላት እንጅ ልባቸውን ለወያኔ እንዳልሰጡ አጋጣሚውን በመጠቀምና ወያኔን በመክዳት እየረጋገጡ ይገኛሉ። ከዚህ ሲያልፍ ደግሞ ከወያኔ ምንም ነገር እንደማይጠበቅ ሁሉ ወያኔ ያዝኳቸው የሚላቸውም ሆዳሞች ለሀገር እና ለሕዝብ የሚፈይዱት ነገር ስለሌለ ከነሱም ማንም  ምንም የሚጠብቀው ነገር የለም። ከቁም ነገር ቆጥሮም ማንም ቦታ የሚሰጣቸው የለም። ስለሆነም ወያኔ ብቻውን ነው ለማለት ይቻላል። ባናቱም በራሱ በወያኔ ሰራሽ የክልል ገዥዎች መካከል አለመተማመኑ ከማየሉም በላይ የየክልሎቹ ሕዝቦች ክልላቸውን ቁንጮዎች ራሳቸው ለመምረጥ አለመቻላቸው ከፍተኛ ውዝግብ ማስነሳቱ ታውቋል። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on March 21, 2014 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , ,

የክስና የተማጽኖ ብዛት ያላስተማረው ወያኔ ዋጋውን ከሕዝብ ክንድ የሚያገኝበት ቀን ቀርቧል

መጋቢት 9 2014

በዴሞክራሲአዊ አካሄድ የተመሰርቱ መንገስታት ይህን ታላቅ ሃላፊነት ያስረከባቸውን ሕዝባቸውን ያከብራሉ፤ ይፈራሉም። በመሆኑም ስልጣኑን የሰጣቸውን ሕዝብ ፍላጎት ለማሟላት ይጥራሉ። ይህ ሳይሆን ቀርቶ አንዳች የተምታታ ነገር ቢፈጠርና  ጉዳዩን በተመለከተ ከሕዝባቸው ጥያቄ ቢነሳ ያላንዳች ማመንታት ጥያቄውን ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ። ካልሆነም ሕዝብ የሰጣቸውን አመኔታ አልተገበሩምና የሰጣቸውን ሃላፊነት ይነጥቃቸዋል። በዚህ የተነሳም ዴሞክራሲያዊ ነኝ የሚል መንግስት ዴሞክራሲአዊ ስርአት የሚያስፈልጉትን አሰራሮች ይተገብራል ማለት ነው።

ባሁኑ ሰአት ባለው የዓለም ነባራዊ ሁኔታ የየትኛውም ሀገር መንግስት ስለዴሞክራሲ ሲያውራ በሀገሩ መልካም አስተዳደር ስለመስፈኑና የዜጎች ሰብአዊ ምብት መከበሩን በጉልህ ማረጋገጥን ጨምሮ ሌሎችም የዴሞክራሲ ትሩፋቶች እየተተገበሩ ስለመሆናቸው በግልጽ ማመላከት ይኖርበታል። ይህን ካላደረገ ደግሞ የየሀገሮችን ዓመታዊ የዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር፣ የሕዝቦችን መሰረታዊና ፖለቲካዊ መብቶች መከበርንና የመሳሰሉትን እንቅስቃሴዎች ከሚዘግቡ ዓለማቀፍ ተቋማት ሪፖርት ጋር መፋጠጡ ግድ ይሆናል። ከዚያም ሲያልፍ የዴሞክራሲን ስርአት ከመገንባት ጋር በተያያዘ ከዓለማቀፉ ማሕበረሰብ የሚቀርቡ ብድርና እርዳታዎችን እስከመከልከል ሊደርስ ይችላል። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on March 9, 2014 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , ,

ሕዝብን በማዋረድ ሀገር እየመራሁ ነው ማለት አይቻልም

 

መጋቢት 9 2014

በአማራነት ከእኔ ወዲያ ላሳር በማለት የሚያጭበረብረው በረከት ስምኦን፤ የአማራ ክልል ምክትል ገዥ አለምነው መኮንን የአማራን ህዝብ መሳደቡን ተከትሎ ለአማራ ሕዝብ በማሰብና በመጨነቅ ሳይሆን ወያኔ ሕወሃት ጥርስ ውስጥ ገባ፣ እኛንም አሳጣኸን በዚህ የተነሳም ሕዝብ ተነሳብን በሚል አለምነው መኮንንን እንደገመገመው የታወቀ ቢሆንም፣ ሕዝብን ማዋረድና መሳደብ ግን ባለምነው መኮንን የተጀመረ ሳይሆን የዛሬው ገምጋሚ ነኝ ባይ በረከት ስምኦንም የተካነበትና ጥርሱን የነቀለበት መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ አሳምሮ ያውቃል።

ሀገር መምራት ሕዝብን ማገልገል መሆኑን ረስተው ሕዝብን ከሰው ደረጃ ዝቅ አድርገው በመግዛት በሕዝብ እየተገለገሉ ያሉት እንደ በረከት ስምኦንና አለምነው መኮንን ያሉ ወያኔ ሕወሃቶች ህዝብን ዝቅ አድርገው በማየታቸው እነሱ ከፍ ያሉ ስለሚመስላቸው ሁሌም ሕዝብን በመሳደብ ራሳቸውን ሲያዋርዱ ይታያሉ። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on March 9, 2014 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , ,

የቡሄ ዕለት የደነቆረ ሆያሆዬ ሲል ያረጃል 2

ጥር 31 2014

እድገትን፣ መልካም አስተዳደርን፣ ነጻ ሚዲያን፣ ዴሞክራሲን፣ የሕዝብን ነጻነትና የመሳሰሉትን በአንዲት ሀገር የሚከወኑ ለውጦችን ነቅሰው በማውጣት ዓመታዊ ሪፖርት የሚያቀርቡ ዓለማቀፍ ተቋማት በተደጋጋሚ የወያኔን ውሸት እያጋለጡና አገዛዙ የደረሰበትን የዝቅጠት ደረጃ በማስረጃ እያመሳከሩ ቢያስረዱም የአዲስ አበባው ወያኔ ዜና አገልግሎትና በረከት ስምኦን ግን ሀገራችን በፋሽስት ወያኔ አገዛዝ እያሳየች ያለችው እድገት ከውድድር በላይ ሆነ እያሉን ይገኛሉ።

ባንዲት ረፋድ አርሶ የሚጨርሳትን ቁራጭ መሬት ይዞ ለዚያውም ባናቱ የፓርቲ አባልነት ካርድ ካልያዘ ይችኑ እንደሚያጣ ጧት ማታ የሚዛትበት ገበሬ በሕወሃትና በነበረከት ዓይን ዓመታዊ ተቀማጩ የሀገሪቱን ባንኮች አንዳጣበበ ሳይታከት ይነገርለታል። ሀብቱ ጣራ ነካ እየተባለ የሚነገርለት ገበሬ ግን ይልሰው ይቀምሰው አጥቶ በሀገር ውስጥ ስደት ከተሞችን እንዳጣበበ የሀገራችን ነባራዊ ሀቅ ነው። የቀረውም ቤት የሌለው ሃብት የሌለው የመንገድ ላይ ተንጠራዋዥ ከሆነ ቆይቷል። ከስደት የተረፈውም ከልክ በላይ በጠበበው የእርሻ መሬት ከልክ በላይ ተጣቦ ለከብቶቹ የግጦሽ ሳር ለማስቀረት ተስኖት በግል ከብቶቹ የሚቆጠር አጥንት ሂዎቱን ሊያቆም ላይሞላለት ይታትራል። ከዚህ ሁሉ ድካሙ በሗላ የሚገኝና ለገበያ የሚቀርብ ነግር ካለ እንኳ እሱ ሀገሪቱን የተቆጣጠረው የቢዝነስ ኢምፓየር ኤፈርት ሲሳይ እንጂ የድካሙን ፍሬ የሚያገኘው ያገሬ የተገፋ ገበሬ አይደለም። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on January 31, 2014 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , ,