RSS

ጀግንነትህ የገባኝ ዛሬ ነው

10 Jul

 

ስምን መላክ ያወጣዋል አሉ!!! ”አንዳርጋቸው” አሉህ እውነትም አንዳርጋቸው። የዚያን ትውልድ ዓላማ፣ ቁርጠኛነትና ፍቅር፤ ተስፋ አይቆርጤነት፣ ጥንካሬና የአመራር ብቃት ያየንብህ ታላቅ ሰው፤ በራስህ ትውልድ የጀመርከውን የነፃነት ጉዞ ለመቋጨት ከጓዶችህ እጅግ ወርደህ ይህን ትውልድ ስለ ሀገር አንድነትና ሉአላዊነት፣ ስለ ሰው ልጅ ክብርና እኩልነት፤ ስለ ነፃነት አስፈላጊነት በተለይም በዘመንህ አሳምረህ የምታውቃቸው ጠባቦቹ ወያኔዎች በሀገራችንና በወገናችን ላይ እያደረሱት ያለውን ዘመን አይሽሬ ጭካኔና ክህደት ለማስተማር ለማሳወቅና ለማሰልጠን ብሎም በትግል ነፃ መውጣትን በተግባር ለማሳየት ከአውሮፓ ዉብ ከተማ በርሃ ድረስ የወረድክ ምሳሌ የማይገኝልህ ንዑድ ኢትዮጵያዊ ነህ።

”አንበሳው በጅቦች ተከቦ አየሁት” አለ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ እውነት ነው ከምንም በላይ ገዝፈህ ”ልብ ካላችሁ ኑና ግጠሙን” ሲል የነበረውን ወያኔ በፈለገው ቋንቋ ለማናገርና የፈለገውን ለማሳየት ባደረከው ውጠታማ ጉዞ ገና በሩቁ ውሃ ያስጠማህ ያንበሶች አንበሳ ነህ አንዳርጋቸው። ላለፉት ከ 40 ዓመታት በላይ በሚያስደንቅ ጥንካሬ፣ ሀቀኝነትና ታማኝነት ጎልተህ የምትታይ በሳል ፖለቲከኛ፤ የእኩልነትና የመፈቃቀር ተምሳሌት ነበርክ ነህም። እናም በአንክሮ ከማስተዋልህ ጀርባ፣ እናም ከእርጋታህና ከትግስትህ ጀርባ፣ እናም ከምክርህና ከአርቆ አስተዋይነትህ ጀርባ ያለው ማንነትህ፣ ያለው ጀግንነትህ የገባኝ ዛሬ ነው። አወ ጀግንነትህ የገባኝ ዛሬ ነው።

ጀግንነትህ የገባኝ ዛሬ ነው 

አብረን እንደግ እንጅ በመለያየት አንጥፋ

እንደጋገፍ እንጅ አንዳችን ላንዳችን አንክፋ

ሁላችን አንድ አይነት ሰው ነን

ጌታና ሎሌ የሌለን

ስለዚህ እኛው ለእኛ እንወግን

ብለህ የተነሳኸው አነሳስ ከክፉ ተቆጥሮ በነሱ

አንተን ለማጥፋት ምለው ጫካና ጥሻ ሲጥሱ

ረብጣ ዶላር መድበው የወገንን ሃብት ሲያፈሱ

ያንተን ነፍስ ካንተ ለመንሳት ሽህ ጊዜ ወድቀው ሲነሱ

ያየሗቸው ጊዜ ነው የገባኝ ያንተ ጀግንነት

ሃምሳ ቦታ እያስጎደበ ጥላህን ሲከተሉ ያየሁ ለት

እናም ወንድሜ የትግል ጓዴ አንዳርጋቸው

ሁሌም እኔ እንደማውቅህ ናቅ አርግና ተዋቸው።

አሁን ከፊትህ የቆሙት ሁሉ ትእዛዝ ጠባቂ ግዑዝ ናቸው

አስተዋይ ህሊና ይቅርና ሰሚ ጆሮም የላቸው

እናም ወንድሜ የትግል ጓዴ አንዳርጋቸው

ናቅ አድርግና ተዋቸው።

እውነት ነው ይምልህ ጓዴ አንዳርጋቸው

አንተን ለመያዝ የሄዱበትን ሳስበው

የፈጠሩትን ምክንያት የከፈሉትን ስቆጥረው

እንቅልፍ ያጡባቸውን ሌሊቶች ያናወዛቸውን ጊዜ ሳሰላው

ያንተ ጀግንነት የሚገባኝ ያኔ ነው።

ጀግንነት ማለት የሄ ነው ወገንን የማወቅ ብስለቱ

ሀገር በመተሳሰብ አንድ እንድትሆን አንድነት አንድነት ማለቱ

ሕዝብን እንደቤተሰብ በፍቅር ሰንሰለት ማበቱ

አወ ጀግንነት ማለት ይሄ ነው እኛም የምናውቀው ከጥንቱ።

ወንድሜ አንዳርጋቸው ልንገርህ ጀግንነትህ የገባኝ ዛሬ ነው

ሕጻን ወጣቱና አዋቂው በእድሜ የገፋው ሳይቀር

ስላንተ ቅጥል እያለ እየነደደ በፍቅር

አሳዩን ምሩን አስታጥቁን ዛሬ ለትግል እንውጣ

አንዳርጋቸው ከዋለበት እንዋል ከእንግዲህ የመጣው ይምጣ

እያለ ሲፎክር ስሰማ ከሁሉም አቅጣጫ ሲመጣ

ባንተ ጀግንነት ሰከርኩ ሁለመናየ ቅጥ አጣ።

በፊት በቅጡ ያልታየው ስራህ መጎምራቱ የገባኝ

አፋር አትለው ሶማሌ አማራ ትግሬ ወላይታ

ጋምቤላ ጉሙዝ አደሬው ኦሮሞውና ከንባታ

ደቡቡ የመሀል ሀገር ሰሜኑ ያንድነት ጥዑም ዝማሬ የፍቅር ሰፈፍ እፍታ

ሳይ ጊዜ ምስራቁና ምእራቡ ሁሉም ሲሰጠህ ሰላምታ

አልኩኝ እኔ፤ እውነትም ስራህን ሰርተህ አጠናቀሃል ጀግናዬ

አንዳርግ የኔ ከርታታ መከታ ጋሻ ዋናዬ

እናም የሕዝቡ ስሜት ተጋብቶኝ እኔም ተቀኘሁልህ

ዝም ያለ ልሳኔን ልክፈተው ፍቀድ ካንተ እኩል ላውራ እኔም ታናሽህ

ግንቦት 7 እያለ ስለ ሀገር ሲሰብክ ራሱ ሀገር የሆነ

የሀገር ፍቅር ያነደደው ስለ ወገን የኖረ

አወ አንዳርጋቸው እሱ አንዳርጋቸው ነበረ

ለወሬ ቀዳዳ ደፍኖ ሕዝብን ባንድ ያሰለፈ

ኢትዮጵያዊነትን የመነ በሙሉ ክንዱ ያቀፈ

በመጽሃፎቹ ጽፎ በተግባር የተሳተፈ

አንዳርጋቸው ነው እሱ ስለ እውነት የተሰለፈ

መለያ ምልክት ማንዲራችን ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ሲጥር

ከተማ በርሃ ኳታኙ ራሱም ግዙፍ ባንዲራ ነበር

እናም ዛሬ ላይ ሆኜ ያንን ጀግናዬን ሳስበው

እላለሁ ለጀግና እስሩ አይደለም ሞቱ ክብሩ ነው

የዘራኸው እንደሁ ጎምርቷል እየታየ ነው በገሃድ

ሁሉም ጀምሯል ጉዞ አንተ የሄድክበትን መንገድ

ያለምካት ባንዲራ ሳይሰቅል የድል ችቦ ሳይለኩስ

የተመኘሃትን ኢትዮጵያ ሳይፈጥር ሳንጃውን ወደ አፎቱ ላይመልስ

እኔም ግንቦት 7 ነኝ እያለ ሕዝቡ ከሗላህ ተመመ

አንዳርጋቸው ዓላማዬ ነው እያለ ኢትዮጵያ ሁሉ አደመ

እናም እስርህ ሰርግ ሆኗል ልንገርህ የትግል ጓዴ

ቢሰድብህ እንዳትበሳጭ ቢገርፍህ ያገር ወንበዴ

እናም እስርህ ሰርግ ሆኗል ልንገርህ የትግል ጓዴ

ቢሰድብህ እንዳትበሳጭ ቢገርፍህ ያገር ወንበዴ

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on July 10, 2014 in AMHARIC, ARTICLE, POEM, VIDEO

 

Tags: , , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: