RSS

አትከፋፍሉን! አንድ ነን! ነፃነት ነፃነት ነፃነት!!!

21 Mar

መጋቢት 21  2014

ፋሽስት ወያኔ የተለያዩ ማባበያ መነገዶችን በመጠቀም፣ አንዳንድ ችሮታዎችን በማዘጋጀትና ይህም ሳይሆን ሲቀር ሃይልን በመጠቀም ጭምር የኢትዮጵያን ሕዝብ በስሩ ለማሰለፍ ሲጥር የቆየና እየጣረ ያለ ቢሆንም ከጥቂት ሆዳሞች በቀር ሰፊውን ሕዝብ ለመያዝ አልተሳካለትም። ሆዳሞቹም ቢሆኑ ለአላማቸው ሆዳቸውን ለሞሙላት እንጅ ልባቸውን ለወያኔ እንዳልሰጡ አጋጣሚውን በመጠቀምና ወያኔን በመክዳት እየረጋገጡ ይገኛሉ። ከዚህ ሲያልፍ ደግሞ ከወያኔ ምንም ነገር እንደማይጠበቅ ሁሉ ወያኔ ያዝኳቸው የሚላቸውም ሆዳሞች ለሀገር እና ለሕዝብ የሚፈይዱት ነገር ስለሌለ ከነሱም ማንም  ምንም የሚጠብቀው ነገር የለም። ከቁም ነገር ቆጥሮም ማንም ቦታ የሚሰጣቸው የለም። ስለሆነም ወያኔ ብቻውን ነው ለማለት ይቻላል። ባናቱም በራሱ በወያኔ ሰራሽ የክልል ገዥዎች መካከል አለመተማመኑ ከማየሉም በላይ የየክልሎቹ ሕዝቦች ክልላቸውን ቁንጮዎች ራሳቸው ለመምረጥ አለመቻላቸው ከፍተኛ ውዝግብ ማስነሳቱ ታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም ጎጠኛው የሕወሃቱ ቁንጮ በሞተበት ወቅት በቦታው መተካትን በተመለከተ ተፈጥሮ እንደነበረው አይነት ዓለምን ህምምምም ያስባለ መከፋፈልና መቧደን ሰሞኑን በሞተው የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ምክንያት ተመሳሳይ ሁኔታ ሊከሰት እንደሚችል መረጃዎች እያመለከቱ ነው። የኦሮሚያውን ፕሬዚዳንት ሞት ተከትሎ በቦታው ለመተካት በሚደረገው ጥረት በወያኔ መንደር ከፍተኛ ፍጥጫ እንደተፈጠረ ምንጮች የረጋገጡ ሲሆን እስከ መቼ ድረስ ነው ለክልላችን ሕወሃት መሪ የሚመርጥልን? እንደ አንድ የክልል መንግስት የራሳችንን መሪዎች ራሳችን የማንመርጠው ለምንድን ነው? ክልላችንን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሕወሃት የሚያስተዳድርልንስ እስከመቼ ነው? በእርግጥ ብቃት ያላቸውን ሰዎች ክልላችን አላፈራችም? የሚሉና ሕወሃትን ያስጨነቁ ጥያቄዎች ከኦሮሚያ ክልል ቁነጮዎች አካባቢ እንደተነሱ ታውቋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም ፋሽስት ወያኔ ከላይ ካለው የሕዝብ የመንግስት ባለቤትነት ጀምሮ እስከ ታችኛው እያንዳንዱ ቤተሰብ ድረስ በተቀነባበረ መንገድ ጣልቃ በመግባት የሚደረገውን ሁሉ ለማወቅ የሚዳዳውና ለመቆጣጠር ሙከራ ከማድረግ የማይመለስ ፋሽስት በመሆኑ ለመቆጣጠር በሚያደርገው ሙከራ ብዙ ትርምሶችን ከመፍጠሩም በላይ አሁን በሀገራችን እየታየ ላለው አለመረጋጋትና አለመተማመን ዋናው መንሰኤ ሆኗል። በዚህ ሂደትም በሃይማኖት ተቋማት አመራር ምርጫ የራሱን አፈ ቀላጤዎች በጉልበት ማስቀመጡን ተከትሎ እኛ መቼ ነው የራሳችንን ወኪሎች በአመራር ቦታ ላይ የምናስቀምጠው ከሚለው ጉምጉምታ ጀምሮ ምእመኑን ለተቃውሞ አደባባይ ድረስ ያስወጣና እስካሁንም ድረስ ያልበረደ ከፍተኛ ችግር ፈጥሯል።

በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ያልታየበት፣ ህሊናዊ ዳኝነት ያልታከለበት፣ ምን ይሉኝ የሚለው ባህላችን ፈፅሞ የጠፋበትና ፍጹም ጭካኔ የተሞላበት መንግስተዊ ሙስና ወደ ወታደሩ ሰፈር ጭልጥ ብሎ ገብቶ ሚሊየነር ጀነራሎችን ያፈራ በመሆኑና ይህም በተራው የወያኔ ወታደር ዘንድ በግልጽ እየታወቀ በመምጣቱ ውጥረት እንደተፈጠረ በወያኔ መንደር እየተሰማ ነው። በዚህና በተመሳሳይ ችግሮች ምክንያት ትግስት እያጣ የመጣው የወያኔ ጦር በተቀናጀ መልኩ ተደራጅቶ አፈሙዙን አዙሮ ራሱን ወያኔን ለመውጋት በሚያደርገው ጥረት የሚያስተባብረው ሃይል እየፈለገ ባለበት ባሁኑ ሰአት ቁጥሩ ጥቂት የማይባለው የወያኔ ጦር ደግሞ እየከዳ ከተቃውሞ ሃይሉ ጋር እየተቀላቀለ መሆኑ ታውቋል። ስለሆነም በወታደሩ ሃይል የሚተማመነው ፋሽስት ወያኔ የጦሩን ቁጥር አስሬ እያነበበ ይደሰት እንጅ ሃቁ ግን ብቻውን መቆሙን ነው የሚያመለክተው።

ፋሽስት ወያኔ እውቀት እንዳይኖረው አድርጎና ታሪካዊ መሰረቱን አዛብቶ እሱ በፈለገው መልኩ ቀጥቅጦ ሊሰራው የሞከረው ከፍተኛው የሀገሪቱ ተረካቢ ሃይል ወጣቱ ቢሆንም፤ ይህ ትኩስ ሃይል ግን ማባበሉ ሳይበግረው፣ የትምህርትና ስራ ልዩ እድሉ እና የገንዘብ ድጎማው ዓላማውን ሳያስለውጠው ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልኩ ኢትዮጵያዊነትን ናፋቂ ኢትዮጵያዊነትንና አንድነትን ዘማሪ ሆኖ መውጣቱ ወያኔን ያሳሰበ ጉዳይ ሆኗል። ወጣቱ ያገኘውን አጋጣሚ በመጠቀም ኢትዮጵያዊነትንና አንድነትን ሰባኪ ሆኑ መገኘቱ ከቀደሙት መንግስታት በበለጠ ሁኔታ ለወጣቱ አስባለሁ፣ የተሻለ ሁኔታንም ፈጥረያለሁ ለሚለው ወያኔ ሕወሃት ብቻውን ለመቆሙ ማረጋገጫ ነው።

ከዚህ ጋር በተያያዘ አጋጣሚውን በመጠቀም ሃሳቡን በመግለጽ ላይ ያለው ወጣቱ ክፍል አካል የሆኑ ወጣት  ሴቶች ሰሞኑን ተደርጎ በነበረውን የሴቶች ታላቅ ሩጫን በመጠቀም ተቃውሟቸውን ማሰማት ችለዋል። ምንም እንኳ በጉልበቱ የሚተማመነው ሕወሃት ወጣቶቹን በማሰር ተቃውሞን በሃይል ዝም ለማድረግ ጥረት እንዳደረገ በሩጫው መጨረሻ ላይ የታየ ቢሆንም ወጣቶቹ ከመታሰራቸው በፊት ግን በከፍተኛ ድምጽ ”አትከፋፍሉን፣ አንድ ነን፣ አንዲት ኢትዮጵያ፣ አንድ ሕዝብ፣ ነፃነት ነፃነት ነፃነት” እና የመሳሰሉትን መፈክር ማሰማታቸው ሲታወስ ወያኔና ወጣቶች ዳግም ላይገናኙ መለያየታቸው ግልጽ እየሆነ መምጣቱን አመላካች ሆኗል።

በመሆኑም ሕወሃት ብቻውን ቀርቷል፣ የማስተባበርና የቅንጅት ችግር እንጅ የሚተማመንበትን መሳሪያም  ለሕዝብ መጨቆኛነት ሳይሆን መጠበቂያነት ለማዋል የሚቻልባቸው ክፍተቶች እየታዩ ነው። ባናቱ ደግሞ በማንኛውም ሰአት ጥቃት ለመሰንዘር ዝግጅቱን እያጣጧፈ ያለው እንደ ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል አይነቱ የትጥቅ ሃይል አመራሩን ወስዶ ወያኔን የማስወገድ ትግሉን በከፍተኛ ቁርጠኝነትና ትጋት እያካሄደ መሆኑ መታወቁ ለኢትዮጵያዊያን ከተስፋም በላይ ትልቅ ተስፋ በማሰደሩ ሕዝባዊ ሃይሉን የሚቀላቀለው ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ እየተሰማ ነው።

ከዚህ ሁሉ በሗላ ታዲያ ለወያኔ ሕወሃት ምን ቀረለት? ግልጽ ነው፤ ሁሉም ቀሩበት እንጅ የቀረለት ምንም የለም። ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በማቃቃር በስሙ ሲነግድበት የነበረው የትግራይ ሕዝብም የሕወሃትን መሰሪ አካሄድ ተረድቶ አይንህ ላፈር ካለው ቆይቷል። በመሆኑም ሕወሃት ሕዝብን ከሕዝብ በማጋጨት ለመከፋፈልና ሀገራችንን ለመበታተን ቢተጋም በተቃራኒው ኢትዮጵያዊነት እና አንድነት ጎልቶ መውጣቱ ታይቷል። ስለሆነም ኢትዮጵያዊያን ሁላችንም በዚሁ አንድነታችንን የማስጠበቅ ዓላማ አጠናክረን በመቀጠልና ትብብራችንን የበለጠ በማስፋት ብቻውን የቀረውን ጎጠኛ ጉጅሌ ሕወሃትን የማስወገዱን ሂደት እናፋጥን።

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on March 21, 2014 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: