RSS

ሕዝብን በማዋረድ ሀገር እየመራሁ ነው ማለት አይቻልም

09 Mar

 

መጋቢት 9 2014

በአማራነት ከእኔ ወዲያ ላሳር በማለት የሚያጭበረብረው በረከት ስምኦን፤ የአማራ ክልል ምክትል ገዥ አለምነው መኮንን የአማራን ህዝብ መሳደቡን ተከትሎ ለአማራ ሕዝብ በማሰብና በመጨነቅ ሳይሆን ወያኔ ሕወሃት ጥርስ ውስጥ ገባ፣ እኛንም አሳጣኸን በዚህ የተነሳም ሕዝብ ተነሳብን በሚል አለምነው መኮንንን እንደገመገመው የታወቀ ቢሆንም፣ ሕዝብን ማዋረድና መሳደብ ግን ባለምነው መኮንን የተጀመረ ሳይሆን የዛሬው ገምጋሚ ነኝ ባይ በረከት ስምኦንም የተካነበትና ጥርሱን የነቀለበት መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ አሳምሮ ያውቃል።

ሀገር መምራት ሕዝብን ማገልገል መሆኑን ረስተው ሕዝብን ከሰው ደረጃ ዝቅ አድርገው በመግዛት በሕዝብ እየተገለገሉ ያሉት እንደ በረከት ስምኦንና አለምነው መኮንን ያሉ ወያኔ ሕወሃቶች ህዝብን ዝቅ አድርገው በማየታቸው እነሱ ከፍ ያሉ ስለሚመስላቸው ሁሌም ሕዝብን በመሳደብ ራሳቸውን ሲያዋርዱ ይታያሉ።

ሀገር መምራትና ሕዝብን ማስተዳደር ማለት ግን ጉልበተኛ መሆንና ሁሉን እኔ ብቻ አውቃለሁ ባይነት ሳይሆን ይህን አገልግሎት ለሕዝብ ለመስጠት ተገቢ እውቀት መያዝና ሕዝብን በማዳመጥ ከሕዝብ መማር አስፈላጊዎች ናቸው። ስልጣን የሕዝብ መሆኑን አምኖ መቀበልንና እየመራሁት ነው የሚሉትን ሕዝብም ማክበር ቀዳሚዎች ናቸው። የሕዝባችንን ፍላጎት መሰረት ባደረገ መልኩ የሀገራችንን የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝቦች ተቻችለው በአንድነት እንዲኖሩ በማድረጉ ሂደት ከፍተኛውን ስራ ሰርቻለሁ፤ በዚህም ከፍተኛ ስኬትን አስመዝግቢያለሁ እያለ ወያኔ ሕወሃት በተላላኪዎቹ አማካኝነት ጧት ማታ ቢለፍም፤ ምንም እንኳ ”በጠባቂዋ የተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች” እንደሚባለው በተሸከመው ጠመንጃ በሚያስበው ፋሽስት ወያኔ የተማመኑ የሕወሃት ተላላኪዎች ባለቆቻቸው የበለጠ ተወዳጅና ተመራጭ ለመሆን ሕዝብ የማይፈልገውን እንዲያደርግና እነሱ የመረጡለትን ብቻ እንዲቀበል ለማስገደድ በማንጓጠጥ፣ በመሳደብና በማዋረዱ  እንደገፉበት በተደጋጋሚ እየሰማን ነው።

ስለመከባበር የሚያወራ፣ አብሮ ስለመኖር የሚያስተምር፣ የጋራ የሆነ ራዕይ እንዲኖረን የሚፈልግ ግለሰብም ሆነ ድርጅት ልዩነትን አይሰብክም። አንደኛውን ለይቶ ባደባባይ አይሰድብም። በማን አለብኝነት መንፈስና ማን ይጠይቀናል በሚል መንፈስ አቅም የሌለውን ሕዝብ በማዋረድና በመሳደብ እየሰራነው ያለው ትክክለኛ ነው ለማለትም አይቻልም። ሕዝብን በማንነቱ መሳደብ፣ ማንቋሸሽ፣ መናቅና የመሳሰሉት የወረዱ ድርጊቶች ሁሉ አቅም የማጣት፣ ለማሳመን ያለመቻልና የዝቅተኝነት ምልክቶች እንጅ የማወቅና ሀገር እየመሩ ለመሆኑ ማሳያዎች ሊሆኑ አየችሉም።

ሀቅን እንዳለ ማሳየት ካስፈለገ ደግሞ ባሁኑ ሰአት በሀገራችን ያለው ብቸኛው ማን አለብኝ ባይ ”እንኳንም ከእናንተ ተፈጠርን፤ እንኳን ከሌሎች አልሆንን” እያለ የሚደነፋው ወያኔ ህወሃት ብቻ ነው። አሁን በሀገራችን በጠባቦች እየተደነቀ ያለው የአገዛዘዝ መንገድ የተወሰኑ የማሕበራችን ክፍሎችን በተለይም አማራውን ከእንቅስቃሴ ውጭ ለማድረግ፣ ሞራሉን በመንካት ምንም አይነት የመብት እንቅስቃሴ እንዳያደርግ ለመሰባበር፣ ለዘመናት ለሀገራችን ሲሰራው የኖረውን ሀገር የማዳን፣ የማሳደግና ሀገራችን ጠንካራ ሆና እንድትታይ የማድረግ ስራ ለማኮሰስና ድካሙን መና ለማድረግ በወያኔ የተጠነሰሰና አማራ ነን በሚሉ የራሱ ልጆች እየተተገበረ  ያለ የተንኮል ስራ ነው።

ዛሬ በወያኔ ተላላኪዎች የሚሰደበው አማራ ሀገር ለማዳን በየድንበሩና በርሃው ሂዎቱን ሲገብር ደሙን ሲያፈስ አጥንቱን ሲከሰክስ የኖረ እንጅ የራስን ከርስ ለመሙላትና በፍርሃት በመርበድበድ ሀገር አሳልፎ ሲሸጥ በታሪክ አልተመዘገበም። ዛሬ ለአቋራጭ ስልጣን ማግኛነት በማንም የወያኔ ቡችላ የሚሰደበው አማራ ከሌሎች የሀገሪቱ ብሄሮች ጋር በመተባበር ሀገራችንን አስከብሮ የኖረ የድንበር አጥር ነበር እንጅ የሀገራችንን ክብር ሲያዋርድ፣ ባንዲራዋን ሲያረክስ፣ አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳ ሲቀሰቅስና ሲያስተምር አልታየም። ይህ ብሔር ከሌሎች ብሄሮች ጋር በመተባበር ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የነጻነት ምሳሌ ተደርጋ እንድትታወቅና እንድትታይ በማድረጉ የሚከበር ነበር እንጅ በፋሽስት ወያኔዎቹ ጥቁር አማሮች እንዲህና እንዲያ እየተባለ የሚዘለፍ አልነበረም።

ትላንት የመቻቻል ምሳሌ የተባሉ ሰዎች ዛሬ በትምክህተኘነት በሚከሰሱባት የፋሽስት ወያኔዋ ኢትዮጵያ፣ ትላንት ስለፍቅር ሰብከው አንቱ የተባሉ ሁሉ ተራ በተራ እንደገና ትምክህተኛ በሚባሉባት ምድር ስለትምክህተኛነት ለመናገር ያላጋደለ መለኪያ ይኖር ይሆን? ለመሆኑ ለፋሽስት ወያኔ የትምክህተኘነት መለኪያ ሚዛን ምንድን ነው? ባማራነቱ ፋሽስት ወያኔን ሲደግፍ የመቻቻል ምሳሌ የተባለው እንዴት ነው ስለመብቱ ሲጠይቅ ትምክህተኛ የሚሆነው? ያም ሆነ ይህ ለፋሽስት ወያኔ ተምክህተኛነት መለት አማራ ሆኖ መገኘት ብቻ ነው። ሃይማኖታዊ ስርአቱን የጠበቀ ኦርቶዶክስ ክርስቲያንና ሙስሊም ሃይማኖታዊ አሸባሪ ያለው ፋሽስት ወያኔ ስለሀገር አንድነት፣ ስለድንበር መከበር፣ ስለሁሉን አቀፍ መብትና መሰረታዊ ነጻነት የሚጠይቅ ግለሰብ ወይም ስብስብ አማራ ከሆነ ትምክህተኛና የመሳሰሉትን በማለት ያዋርደዋል። በዚህ መሰረትና በእስከዛሬው የሕወሃት አካሄድ ትምክህተኛነት የሰዎች አመለካከት ሳይሆን አማራ ሆኖ መገኘት ሆኗል። ይህም ነው እንግዲህ በወያኔ የዜና ማሰራጫዎችና ተንቀሳቃሽ ጥቁር አማራ ካድሬዎች ሳይደከም የሚጮኸው።  

ሁሌም እንደሚታወቀው ሳይነካ የሚጮኸው ግን ባዶ የሆነ እቃ ነው። ምንም የሌለበት ባዶ ተርሙስ ወይም ሌሎች ሲፈልጉ የፈለጉትን የሚሞሉት ባዶ በርሜል ከልክ በላይ ይጮሃል። በሕወሃት እየተሞሉ በሉ የሚባሉትን ያለሃፍረት በሕዝባችን ላይ የሚተፉት ጥቁር አማሮችም አንደነኝህ ካሉት ባዶ ጠርሙሶች ወይም ባዶ በርሚሎች መካከል ቀድመው ለመወደድና ለመመረጥ ፈጥነው የጮሁ ባዶ ጭንቅላቶች መሆናቸውን ለመገመት ብዙ ማሰብ አያስፈልግም። ከዚህ በፊት በነበረው የሀገራችን ታሪክም ሆነ አሁን እያየነው ባለው ነባራዊ ሁኔታ ደግሞ ባዶ ጭንቅላቶችና ያሰባሰበው ሕወሃት እንጅ ምስኪን ወገኖቻችን ሀገራችንን አልጎዷትም። እንደተለከፈ ውሻ በቁና ሙሉ ሴቶች ላይ ለሃጫቸውን የሚያዝረበረቡ ፣ በሙስና ልክፍት ረብጣ ዶላር ላይ አፍጥጠው ምራቃቸውን መሰብሰብ የተሳናቸው ሕወሃቶችና ጥቁር አማሮች እንጅ ፋሽስት ወያኔ በፈጠረው ድህነት ተቆራምዶ ገደብ በሌለው ርሃብ እየተንገላታ ያለው ያገሬ አማራ አይደለም። የወቅቱ የሀገራችን ችግር ዘረኝነት እንጅ ትምክህተኝነትም አይደለም፣ አንዴ ትምከህተኛ ሌላ ጊዜ ነፍጠኛ አየተባለ የሚሰደበውና አቅም የለሾች በወያኔ እውቅና ለማግኘት ሲፈልጉ የሚሰድቡት አማራ ከሌሎች የሀገሪቱ ህዝቦች ጋር በመሆን ሀገራችንን ለዘመናት ታፍራና ተፈርታ እንድትኖር ከፍተኛውን ሚና የተጫወተ ነው።

አረ ለመሆኑ እስከ መቼ ነው ሕወሃት ሀገራችንን እንዳጠፋና ሕዝባችንን እንደተሳደበ የሚኖረው? አማራውስ መቼ ነው በሕወሃትና ህወሃት በፈጠራቸው የራሱ ልጆች የስድብ መለማመጃ መሆኑ የሚያበቃው? ሀገራችንንና ሕዝባችንን ለመታደግስ የምንነሳበት ጊዜ ዛሬ ካልሆነ ለመቼ ይቀጠራል? የአማራው የሰሞኑ ሁሉም መረን ወጣ አሁንስ በቃ አይነት እንቅስቃሴና ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብም ከአማራው ጋር አብሮ በመቆም ያሳየው ጠንካራ ትብብር ወያኔ ሕወሃትን በማርበርበዱ ፋሽስት ወያኔ በግንቦት 7 እያመካኘ ወጣቶችን እያፈሰ ወህኒ ማውረዱ እየተሰማ ነው። ከዚህ ሁሉ ጀርባ ያፈጠጠው እውነት ግን ሕወሃት ሀገራችንን ለማጥፋትና ሕዝብ ለማተራመስ አቅዶ በከፍተኛ ሁኔታ እየሰራ መሆኑ ሲሆን እኛ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ ሀገራችንን ለማቆየትና ከነሙሉ ክብሯ ለልጆቻችን ለማስረከብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ልንተባበርና አንድ ሆነን የመቆም ግዴታ አለብን እንላለን። 

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on March 9, 2014 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: