RSS

ፋሽስት ወያኔ ከሁሉም የነጻነት ሃይሎች ጋር ለሁሉን አቀፍ የሰላም ውይይት የሚገደድበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም

12 Jan

ጥር 12 2014

ሀገራችን በታዋቂ ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ምዘና አሁንም ፍጹም ድሃ ከሚባሉት መካከል መሪዋ ነች። አብዛኛው ሕዝባችን ከድህነት ወለል እጅግ በታች በሆነ ገቢ የስቃይ ኑሮውን እየገፋ ነው። የኑሮ ውድነቱ ሕዝባችን እያገኘ ካለው በጣም አናሳ ገቢ በላይ እጅግ ገዝፎ የምግብ እህሎችን ማየት እንጅ መግዛት ወደማይችልበት ዝቅተኛ ደረጃ እውርዶታል። በዚህና በሌሎችም ተያያዥ ምክንያቶች ሳቢያ ልመና ከማሳፈር አልፎ የኑሮ ዘዴ በመሆን ከታላላቆቹ ወደ ትናንሾቹ ከተሞቻችን ተዛምቶ በስፋት መታየት ከጀመረ ቆይቷል። የአፍሪካ የውሃ ማማ የምትባለዋን ሀገራችንን በሃይል የተቆጣጠረው ጎጠኛው ወያኔ የውሃ ፍላጎትን ማሟላት ባለመቻሉ በኢትዮጵያና አፍሪካ በመዲናዋ አዲስ አበባ አንዳንድ ቦታዎች ሳይቀር ሕዝባችን የጎርፍ ውሃ ለመጠጣት እስከመገደድ ደርሷል።

የአንዲትን ሀገር ሁለንተና ከመሰረቱ የሚቀይረው ትምህርት፤ ፋሽስት ወያኔ እየተገበረው ባለው ፍጹም የተበላሸ የትምህርት ስርአት ምክንያት በመሞት ላይ ይገኛል። በዚህ የተነሳም ወያኔ ዩኒቨርሲቲ እያለ ከሚጠራቸው ጀምሮ በየመንደሩ እስከ ተቋቋሙት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ወይም ኮሌጅ እስከሚባሉት ድረስ ሁሉም ምንም መፍጠርም ሆነ መለወጥ የማይችል ዜጋ በማስመረቅ የስራ አጡን ቁጥር ከመጠን በላይ አንረውታል። በመሞት ላይ ያለውን የወያኔ የትምህርት ተቋም ምርት  ግብአት አድርገው በመጠቀም ላይ የሚገኙት የሀገሪቱ የጤና ተቋማት ከስም በቀር በተግባር ከመንደር መርፌ ወጊ የተሻለ አቅም ማዳበር አልቻሉም። ፋሽስት ወያኔ ለራሱ ዘረኛና ከፋፋይ አካሄድ ይረዳው ዘንድ ከላይ እስከ ታች በዘረጋው የሙስና ሰንሰለት፣ በራሳቸው አቅም ማነስ የተነሳ በተፈጠረ በራስ አለመተማመን እንዲሁም ምንም መፍጠር ያለመቻላቸው በፈጠረባቸው ግድየለሽነት ምክንያቶች በሌሎችም ሙያዎች ተመርቀው በስራ ላይ ያሉትም ቢሆኑ ታዛዥነትን እንጅ ራስን ችሎ መንቀሳቀስን ማሳደግ አልቻሉም። በጥቅሉ የቱንም ያህል ቢሆን ፊደል የቆጠረውን ሃይል የሚያስተናግዱት ሲቪል ተቋማት በፋሽስት ወያኔ ሰዎች ከውጭ በሚመጣ ትእዛዝ እንጅ በራሳቸው ሙጣጭ አቅም እንኳን ላይመሩ ቃል የገቡ በሚያስመስል ሁኔታ ሁሉም ተመሳሳይ ርምጃዎችን ሲወስዱ ያታያሉ። ስለሆነም አቅም ማጣትም ብቻ ሳይሆን እንደ ሲቪል ተቋም ለመቀጠል የማይችሉ ሽባዎች እየሆኑ በመምጣታቸው የሕዝባችንን ችግሮች ለመፍታት የማይችሉ ልፍስፍሶች ሆነዋል።

ካቅም በላይ መከራ የተጫነው ሕዝባችን፣ ከኑሮ ውድነቱ በተጨማሪ ተቋማዊ መፍትሄ በማጣት እየተንጠራወተ ያለው ወገናችን በራሱ መፍትሄ የሚፈልግበት ወቅት ላይ ደርሷል። ይህ ሁሉ ወያኔ ሰራሽ ስቃይ አንገቱን አስደፍቶት የነበረው ሕዝባችን አማራጭ ፍለጋ አንገቱን እንደገና ቀና በማድረግ ላይ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ ናቸውና። ሕዝባዊ እምቢተኝነት ከትምህርት ተቋማት እስከ ወያኔ ስብሰባዎች፤ ከቤተእምነት እስከ ቤተመንግስት፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ከሚሰጠው እስከ ወያኔ ጦር ድረስ እየተዛመተ ይገኛል።

ባራቱም መአዘናት በሚገኙ የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ታጣቂዎች ጥቃት እየሰነዘሩና አቅማቸውን እያሳዩ መሆናቸው በተደጋጋሚ ሪፖርት እየተደረገ ነው። ወደ እነዚህ የትጥቅ ሃይሎች የሚጎርፈው ወጣትና እያገኙት ያለው ሁሉን አቀፍ ሕዝባዊ ድጋፍም ወያኔን ከማስጨነቅ በላይ ሆኗል። ወያኔ በቃኝ የሚለውን ሕዝባዊ የተቃውሞ ሃይል ከትጥቅ ሃይሉ ጋር በማቀናጀት ወደ አጠቃላይ ሀገራዊ ንቅናቄ ለመለወጥና የተደራጁና መስመር የጠበቁ ጥያቄዎችን ለማቅረብ እንዲቻል ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ከፍተኛውን ሚና በመጫወት ላይ ነው። ስለሆነም በዚህ በኩልም ከፍተኛ እመርታ እንየታየ መሆኑ እየተጠቆመ ይገኛል።

ፋሽስት ወያኔ በራሱ ውስጥ ተፈጠሮ የነበረውን አለመግባባት በጊዜያዊነት ለመፍታት የሞከረ ቢሆንም፤ ተፈጥሮ የነበረው ችግርና በጊዜያዊነት የፈታበት መንገድ የራሴ በሚለው የትግራይ ሕዝብ ዘንድ ሳይቀር እንዲተፋ ስላደረገው በአየር ላይ እንደሚንሳፈፍ ባየር የተሞላ ፊኛ ሆኗል። ባናቱም የትግራይ ሕዝብ ወደሌሎች አማራጭ ፓርቲዎች ለመመልከት መገደዱን ማሳየት መጀመሩ ወያኔን በጠራራ ፀሐይ ብርድ ብርድ እንዲለው አድርጎታል። ትእዛዝ ፈጻሚ ሆነው በተቀመጡትና እህት ተብለው በሚጠሩት ብአዴን፣ ኦሕዴድና ደሕዴን በሚባሉት የሕወሃት ግልገል ቡድኖች መካከል አለመተማመን መታየት መጀመሩ ለወያኔ ተጨማሪ ስጋት ሆኗል። የሕወሃት ታዛዥነት ሰለቸን እያሉ ቡድኖቹን እየጣሉ እየወጡ ያሉ አባሎች ቁጥር መበራከቱ ደግሞ ሌላው የወያኔ የጎን ዉጋት ሲሆን በሕወሃት ዓይን እህት የሚባሉት ቡድኖች ራሳቸው ስማቸው በግልጽ ያልተጠቀሰ ተቃዋሚ ደርጅቶች ተደርገው እየታዩ ይገኛሉ።

ይህ ሁሉ የሚያሳየው እንግዲህ እየተጠናከረና እየሰፋ የመጣው የሕዝብ ምሬት ወደ ሕዝባዊና ወያኔያዊ ተቋማት ምሬትነት በፍጥነት እየተለወጠ በመምጣት ላይ መሆኑን ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ ፋሽስት ወያኔን በትጥቅ ትግል ለማስወገድ እየሞከረ ያለው ሃይል ወደ ተግባር እየተሸጋገረ መሆኑንም ጭምር ነው። በዚህ መንገድም እየተጠናከረ የመጣውን ሕዝባዊና ተቋማዊ ምሬት ራሱን ወደ ቻለ ግዙፍ ሕዝባዊ እንቢተኘነት በመለወጥና ይህንንም አንቢተኝነት ጥቃት በመሰንዘር ላይ ባሉት የትጥቅ ድርጅቶች ሃይል በማጀብና ወደ ሀገራዊ ንቅናቄ በመቀየር ፋሽስት ወያኔን ከሁሉም የነፃነት ሃይሎች ጋር ወደሚደረግ ሁሉን አቀፍ የሰላም ድርድር እንዲመጣ መስገደድ ይቻላል። ስለሆነም ኢትዮጵያዊያን ያለልዩነት ሁላችን በተለያዩ ምክንያቶች እየተፈጠሩ ያሉትን ሕዝባዊ ምሬቶች ወደ ሕዝባዊ እንቢተኝነት በመለወጡ ሂደት ያላሳለሰ ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል። የትጥቅ ትግል እያደረጉ ካሉ ሃይሎች ጋር በመተባበርም ፋሽስት ወያኔን ከሁሉም የነፃነት ሃይሎች ጋር ለሚደረግ ሁሉን አቀፍ ድርድር ለማስገደድ ወይም ጭራሹኑ ለማስወገድ እየተደረገ ላለው የሞት ሽረት ርብርብ የግላችንን ማበርከት ይጠበቅብናል።

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on January 12, 2014 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , , , , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: