RSS

ህግ ካልሰራ ጉልበት አማራጭ ይሆናል

05 Jan

ጥር 5 2014

የሰው ልጅ ማህበራዊ ፍጡር ነው። ለመኖር በግል ከሚያስፈልጉት የምግብ፣ የአልባሳትና መጠለያ ማሟላት በተጨማሪ ለቀን ከቀን እንቅስቃሴው እና አካባቢውን በተለየ መልኩ ለሱ እንዲመች አድርጎ ለማስዋብ ከሱ መሰል ሌሎች ሰዎች ጋር መተባበር የግድ ይለዋል። ሁሉንም ነገር በራሳችን የግል ጥንካሬና ችሎታ ብቻ መከወን ያለመቻላችን ሚስጥርም ጠፈጥሮአዊ ማህበራዊነታችን ነው። በእርግጥ ሌሎች እንሰሳትም በማህበር ይንቀሳቀሳሉ እንስሳዊ ፍላጎታቸውንም ያሟላሉ። እጅግ በጥልቀት በማሰብ ለምንቀሳቀሰው ለኛ ለሰዎች ግን ማህበራዊነት ከሁሉም በላይ ፋይዳው የገዘፈ ነው። ያንዳችን እንቅስቃሴ የሌላኛውን መንገድ እንዳያበላሸው ከሌሎች እንስሳት ይልቅ ቀርበን በመወያየት በመነጋገርና በመስማማት ለጋራ ጥቅም የጋራ ውሳኔ እናሳልፋለን። በዚህም መሰረት ትዳር ከመመስረት ጀምሮ ባካባቢያችን የምናቋቁማቸው እንደ እድር እቁብ፣ የሙያ ማህበራት፣ የደቦ ጊዜያዊ ትብብርና ሌሎችም መሰል ስብስቦች ያሉንን እለታዊ እንቅስቃሴዎች ለብቻችን ማሸነፍ ያለመቻላችን ችግር የፈጠራቸው ማህበራዊ መፍትሄዎች ናቸው።

እነዚህን ማህበራዊ ስብስቦች ለመምራት ደግሞ ህሊናዊ ዳኝነትን ከመጠቀም በተጨማሪ ሌሎችንም የጋራ ስምምነቶችንና መመሪያዎችን በስራ ላይ እናውላለን። ለሰው ልጅ ትልቁ ዳኛው የራሱ ህሊና ነው። ህሊናው የሚያዘውን ይከውናል። በግልም ሆነ በማህበር ለሚያጋጥሙት ችግሮች መፍትሄ የሚያገኘው ከህሊናው ሊሆን ይገባል። ነገር ግን ዓለም ሁሌም እነዲህ አይደለችም። አንዳንዱ የራሱን ጥቅምና ማንነት ከሌሎች በተለየ መልኩ ከፍ ለማድረግ፤ ባካባቢው የሚኖሩትን ሰዎች ፍላጎትና ጥቅም ለመጋፋት የራሱን ትልቅና ሀቀኛ ፍርድ ቤት ህሊናውን ይጨቁናል። “እየሰራህ ያለኸው ትክክል አይደለም” እያለ ሌት ከቀን የሚገስጸውን ህሊናውን በመጫን የሌሎችን ፍላጎት የሚጎዳ፣ የአካባቢ ሰላምና ማህበራዊ ግንኙነት የሚያደፈርስና የሀገርን ጥቅም የሚያጠፋ ስራ እንዳይሰራም በጋራና በሙሉ ስምምነት በጸደቀ ህግ ይገዛል። በዚህም መሰረት ለህሊናው ዳኝነት ያልተገዛ የማህበረሰቡ አባል በጋራ በተቀመጠው ህግ መሰረት አግባብነት ያለው ቅጣት እንዲቀበል ይደረጋል።

ስለሆነም ማንኛውም የማህበረሰቡ አባል ይህ በጋራ ፍላጎት የጸደቀ ህግ ሳይዛነፍና አንዱን በተለያ አቅርቦ ሌላውን ሳያርቅ፣ ላንዱ የበለጠ መብትና ጥቅም ሰጥቶ ለሌላው ሳያሳንስ፣ አንዱ የበለጠ እንዲተማመንበትና ሌላው ግን እንዲጠራጠረው ሳያደርግ እንደሚሰራ እርግጠኛ ሊሆን ይገባል። በጥቅሉ ማንኛውም የማህበረሰቡ አባል ሁሉም ሰው ያለልዩነት በጋራ ለጸደቀው መተዳደሪያ ደንብ ወይም ህግ እንደሚገዛ እምነት ሊያሳድር ይገባዋል።

ይሁን እንጅ ይህን አጠቃላይ ሃሳብ በፋሽስት ወያኔ ዘረኛ ጠንካራ መዳፍ ስር ወደምትገኘዋ ሀገራችን ስንመልሰው ሁሉም እንዳይሆን እንዳይሆን ሆኖ እናገኘዋለን። አጉራ ዘለሉ ፋሽስት ወያኔ አለኝ ለሚለው የጋራ ህግ የማይገዛ ከመሆኑም በላይ ይህው የይስሙላ ህግ ራሱ እንደፈለገ የሚዘውረው እንጅ ሁላችንንም የጋራ ተጠቃሚ የሚያደርግ አይደለም። ፋሽስት ወያኔ ያልፈለገውን አንድ ግለሰብ ለማጎሳቆልና በወያኔው የህግ ስርአት ተጠቃሚ እንዳይሆን ለማድረግ ብቻ የነበረውንና አለኝ የሚለውን አሰራር እስከ መቀየር መድረሱ፤ ግለሰቦችን ካሰረ በሗላ ከሗላቸው ለእስራቸው ማስረጃ የሚሆን ህግ ማጽደቅ የሚችል መሆኑ፤ በቁጥጥሩ ስር የሚገኙትንና ራሳቸውን ለመከላከል አቅም የሌላቸውን ዜጎቻቸንን በወንጀል ለመክሰስ የሚያገለግለውን ድራማ እንዲተውኑለት ማስገደዱ፤ በራሳቸው ወይም በቤተሰቦቻቸው ሂዎት በማስፈራራት አልያም መተዳደሪያ ስራቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ አድርጎ በማቅረብ ዜጎች በንጹሃን ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ላይ በሃሰት እንዲመሰክሩ ማድረጉ፤ በዳኞች እንዲፈቱ የተወሰነላቸው ዜጎች የዳኞች ውሳኔ በወያኔ ማፍያ ሃይሎች ተሽሮ ወደ ወህኒ እንዲወረወሩ መደረጉ፤ እንዲሁም በዳኛ ውሳኔ ለሕዝብ እንዳይቀርቡ የተከለከሉ ዝግጅቶች በወያኔ ልዩ ትእዛዝ ለሕዝብ እንዲቀርቡ መደረጋቸውና የመሳሰሉት ፋሽስት ወያኔ አሉኝ የሚላቸው ህጎች ሁላችንንም የጋራ ተጠቃሚ የማያደርጉ መሆናቸውን የሚያጋልጡ ከመሆናቸውም በላይ የወያኔን አጉራ ዘለል ባህሪዎች ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ ጥቂት ማሳያዎች ናቸው።

ስለሆነም በጋራ ፍላጎት ላይ የቆመም እንኳ ባይሆን ፋሽስት ወያኔ ህግ በሚለው ህግ እንኳ ተጠቃሚ እንዳልሆነ የተረዳ ሕዝብ፤ እነዚህ ማፍያ ወያኔዎች ከዓለም ታላላቅ ሀገራት የተቀዳ እያሉ የሚመጻደቁበት ህግ ተብየ ህግ በዜጎች መካከል ልዩነትን እንደሚፈጥረ ያወቀ ሕዝብ፤ ይህ ህግ ተብየ ህግ ዜጎችን ያላግባብ ለማሰር ወይም ለመፍታት የሚውል መሆኑንና በተለይ ደግሞ የፋሽስት ወያኔ ቁንጮዎችን ለመዳኘት አቅም እንደሌለው የተገነዘበ ሕዝብ፤ አሁን የራሴን የቤት ስራ መስራት አለብኝ ብሎ በነፍጥ ለሚደረግ ትግል ራሱን ቢያዘጋጅ ከወያኔ በቀር ማን ስህተት ነው ሊለው ይችላል? ወያኔዎችስ በዘመናቸው የነበረውን የዚያን ጊዜውን የህግ ስርአት ትክክል አይደለም፣ የሀገራችንን ሕዝብ በእኩልነት ለማስተዳደር ብቃት የለውም፣ በተለይ እጅግ ጠበው በመነሳት የኛ የሚሉትን የትግራይ ሕዝብ ለይቶ ይጎዳል በማለት የሃይል አማራጭን እንደተከተሉ ሁሉ፤ አሁንስ መብታችን ተደፈረ፣ በሀገራችን ባይተዋር ሆንን፣ በሀገራችን እኩል ተጠቃሚ አልሆንንም፣ በጥቅሉ ኢፍትሃዊነት ነግሷል በማለት በፋሽስት ወያኔ ላይ የሃይል አማራጭን ለመከተል ለወሰነ ሕዝብ የተደጋጋመ መላሻቸው ሽብርተኞች፣ የእነቶኔ ተላላኪዎችና ትምክህተኛ ስርአት ናፋቂዎች መሆኑ የሚያስተዛዝብ አይሆንም?

ወጣም ወረደ ከነዚህ ሁሉ ወያኔያዊ የአገዛዝ ዓመታት በሗላ የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ያረጋገጠው እውነት ግን ወያኔ ራሱ ህግ መሆኑን ብቻ ነው። ታዲያ ሃቁ ይህ ከሆነ ህግን አምነው በህግ ብቻ ተማምነው ለሚኖሩ ምን ቀረላቸው? ይህ የተወለካከፈ ህግ ተብየ ህግ አንደማይሰራ የተረዳው ማሕበረሰብስ የሚወስደው እርምጃ ምን ሊሆን ያችላል? በህግ ስርአቱ ተስፋ የቆረጠ ሕዝብስ ቀሪ የቤት ስራየን በመሰለኝ መልኩ መስራት አለበኝ በማለት መብቱን በጉልበቱ ለማስከበር ቢንቀሳቀስ ወንጀል ነው የሚለው ማነው? መልሱን ላድማጭ ትቸዋለሁ። አበቃሁ።

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on January 5, 2014 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , , , , , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: