RSS

የሳውዲ መንግስት የማሰርና የማሳደድ፤ የመግረፍና የመግደል ሉአላዊ መብት አለው፡- ሽመልስ ከማል

05 Dec

ከይኸነው አንተሁነኝ

ታህሳስ 5 2013

ሀገሮች ሕዝባቸውን የሚያስተዳድሩበት የውስጥ ህግ እንዳላቸው ሁሉ በሌላኛው ሀገር የሚገኝ ዜጋቸውን ሰላም ከማስጠበቅ አንጻር ወይም ደግሞ  ንግድና መዋዕለ ንዋይ ፍሰትን የመሳሰሉ የሁለትዮሽ ግንኙነት የሚፈልጉ ጉዳዮችን በተረጋጋና የራሳቸውን ዜጋ በማይጎዳ መልኩ ለመከወን ይመቻቸው ዘንድ የጋራ ስምምነት ሊያደርጉ ይችላሉ። ይሁን እንጅ ማንኛውም የሀገር ውስጥም ሆነ የሁለትዮሽ ስምምነት ዜጎችን ለችግር የማያጋልጥ መሆን የሚጠበቅበት ከመሆኑም በላይ በዓለም አቀፍ ህግጋት መርህ የተቃኘ ሊሆን ይገባዋል።

የአንድ ሀገር መንግስት ነኝ የሚል አካል በህጋዊም ሆነ በህገወጥ መንገድ ወደ ሌላ ሀገር ለገቡ ዜጎቹ ሃላፊነት አለበት። በችግራቸውም ጊዜ የሚኖሩበት ሀገር ህግ በሚደነግገው መሰረት እንዲዳኙ አስፈላጊውን እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅበታል። ይህን በተመለከተ ፋሽስት ወያኔ በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገሬ ገቡ ብሎ የከሰሳቸውን ስዊድናዊያን ጋዜጠኞችን ለማስለቀቅ የስዊድን መንግስት ያሳረፈውን ተጽእኖ ማስታወስ በቂ ይሆናል። ፋሽስት ወያኔና ጥጋበኛ ባለስልጣናቱ ግን በሳውዲ አረቢያ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ላለው የበዛ ስቃይና ግድያ ለሳውዲ መንግስት እውቅና ሲሰጡ ይሰማሉ። የትኛውም ሀገር ከህግ በወጣ መልኩ የየትኛውንም ሀገር ዜጋ ማጥቃት አይችልም። ጠፋት ተሰራ ቢባል እንኳ በሀገሪቱ ህግ መሰረት ይዳኛል እንጂ ማንም እንደፈለገ እንዲበጠብጠውና እንዲገድለው የሚያዝ አኬሃድም ሆነ አሰራር የለም። እንዲህ ያለ መረን የወጣ ነገር ተደርጎ ቢገኝ እንኳ ህጋዊ ባለመሆኑ ጥቃቱ የደረሰባቸው ወገኖች መንግስታት ጉዳዩን ወደ ህግ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው። ከፋሽስት ወያኔ በኩል እየሰማን ያለነው ግን እጅጉን የሚደንቅ ሆኗል። ዲና ሙፍቲ የሚባለው ወያኔ ዓለም ያየውንና ያወቀውን ገሃድ የወጣ እውነት በመሸፋፈን ምንም እንዳልተፈጠረ ለማድረግ ሲጥርና እንዲያውም የማህበራዊ መገናኛዎች ወሬ ነው ብሎ ሊያጣጥለው ሲሞክር ሌላው ሽመልስ ከማል የሚባለው ወያኔ ደግሞ የሳውዲ መንግስት የማሳደድና የማሰር፣ የመግረፍና የመግደል ሉአላዊ መብት አለው ብሎ ለሳውዲ መንግስት ሲከራከር እየሰማን ነው። በእርግጥ አሁን ሁላችንም ያለልዩነት ሀገራችን መሪ አላት ወይ? ብለን የምንጠይቅበት ወቅት ላይ ነው ያለነው። ፋሽስት ወያኔ ሀገር አየመራሁ ሕዝብ እያስተዳደርኩ ነው ቢልም በተግባር እየሆነ ያለው ግን የማይገናኝ ነው። ለወገኖቻችን ያለነው እኛው ወገኖቻቸው ብቻነንና በጋራ በመቆም በሳውዲ በእንግልት ላይ ላሉ ወገኖቻችን እገዛ ከማድረግም ባሻገር ለዚህ ሁሉ መከራ የዳረገንን ፋሽስት ወያኔን ለማስወገድ ትብብራችንን እናፋጥን እያልኩ ዝግጅቴን ልቋጭ።

በእርግጥ ሀገሬ መሪ አላት?

ይህች ባለ ሶስት ሽ ዓመት ባለታሪክ ኢትዮጵያ

የሐበሻ ምድረገነት የእኛነታችን መለያ

ይህች ጥንተ ገናና አትንኩኝ ባይ ቀብራራ

በክብር የኖረች፣ ምልክት የጥቁር ዓለም እማውራ

እስኪ ንገሩኝ ባካችሁ በርግጥ ይህች ሀገር መሪ አላት?

ሰላምን የተሸከመ የፍቅር የእውነት ባለቤት

እንደጥንቶቹ አባቶች ወድቆ  ተነስቶ አለሁ የሚላት

ካንች በፊት እኔ ልዋረድ ብሎ የሚሞትላት

ሕዝቧ ሲከፋ ሲሰደድ እስከ ዓለም አናት

በአረብ ምድር  ሲደፈር ሲገረፍ ሲሞት

የት ነው ያላችሁ ብሎ ሚጠይቅ የሚደርስ ለሕዝብ ጭንቀት

እስኪ ንገሩኝ ባካችሁ በእርግጥ ይች ሀገር መሪ አላት?

አካሏን ጎምዶ ጎማምዶ ለሽያጭ የማያቀርብ ባተሌ

ለአረብ ለነጭ ውላጅ ለማንም የማይሆን ሎሌ

የማንነት ምልክት ባንዲራዋን የማያዋርድ የማይወረውር በዘፈቀደ

ክብር ሞገሱን አጣጥሎ ለጨው መቋጠሪያ የማያድል እየጎመደ

ትዕቢቱ ካነገቱ ሞልቶ ቋቅ ብሎ የማይተፋባት

እድሜ ዘመኗን ቆማምጦ ያገር ጎረምሳ  የማያደርጋት

አንደኛው ልጇን ከሌላው የማያቀርበው አብልጦ

ሌላውን ገፍትሮ ንቆ እንዲኖር ባይተዋር ሆኖ ተውጦ

አንዱን እንዲንፈላሰስ መብት የማይሰጠው ለይቶ

ሌላው ሰርቶ ለመኖር እንዳይችል የማያደርገው አዳልቶ

እኩል እድል የሚሰጥ ለትምህርትና ለስራ

ቁርሱን ደቡብ ላይ ቀምሶ እራቱን ሰሜን ቢያጣራ

ምስራቅ ሲነግድ ውሎ ምዕራብ ፎቁን ቢሰራ

ለምን ብሎ የማይጠይቀው ወነወጀል እስካልተሰራ

እስኪ ንገሩኝ ባካችሁ በርግጥ ይህች ሀገር መሪ አላት?

ሰላምን የተሸከመ የፍቅር የእውነት ባለቤት

እንደጥንቶቹ አባቶች ወድቆ  ተነስቶ አለሁ የሚላት

ካንች በፊት እኔ ልዋረድ ብሎ የሚሞትላት

ሕዝቧ ሲከፋ ሲሰደድ እስከ ዓለም አናት

በአረብ ምድር  ሲደፈር ሲገረፍ ሲሞት

የት ነው ያላችሁ ብሎ ሚጠይቅ የሚደርስ ለሕዝብ ጭንቀት

እስኪ ንገሩኝ ባካችሁ በእርግጥ ይች ሀገር መሪ አላት?

 

የራሱን ህዝብ ረስቶ ለሌላው የማይጨነቅ

እግሮቹን አንች ላይ ተክሎ አሻግሮ ማዶ እማይናፍቅ

በደም ባምሳልሽ ተስሎ አንችን እናቱን የማይንቅ

እራሱ መጠኑን ሰፍሮ ባወጣው ቀላል ጫወታ

ሲረታ ዘራፍ የማይል በንዴት መቶ እማይመታ

እሱ የለበሰውን ልብስ ያልለበሰ ዜጋሽን

እንዲለብስ የማያስገድድ የማይጠይቀው መያዣ ነፍሱን

የማይገርፍ የማያስገርፍ ተጨዋች ዘመድ ወገኑን

ይህንን ሁሉ የሚያደርግ ጨዋ ሐበሻ የሰላም አባት

ዛሬስ ልጠይቅ ደፍሬ በዕውነት ሀገሬ መሪ አላት?

እንደጥንቶቹ አባቶች ወድቆ  ተነስቶ አለሁ የሚላት

ካንች በፊት እኔ ልዋረድ ብሎ የሚሰዋላት

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on December 5, 2013 in AMHARIC, ARTICLE, POEM

 

Tags: , , , , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: