RSS

ሕዝብ እና ወያኔ ወዲህና ወዲያ!!!

18 Nov

ይኸነው ዓለሙ

ህዳር 18 2013

ኢትዮጵያዊያን ረከስን፣ በዓለም ዙሪያ ማንም እንደፈለገ የሚዘግነን ሆንን፣ ራሳችንን ለመከላከል የማንችል፤ ስለ እኛም ቆሞ የሚከራከርንል ያጣን ምስኪን ሕዝቦች ሆንን። በሀገራችን ሳይቀር ያሰብነውን ለመከወን አቅም የሌለን፣ አቅጣጫ ጠቋሚ ኮምፓሳችንን የተነጠቅን፤ የጉዞ መቆጣጠሪያ መሪያችንን ያስረከብን ምስኪን ሕዝቦች። ባቅራቢያችን ባካባቢያችን የተፈጠረውን ለኛ ምቹ ያልሆነ ድርጊት ለመቆጣጠር መወያየትና መተባበር የተሳነን፤ ሽሽትን፣ ስደትን ሩጫን እንደ ብቸኛ አማራጭ የተቀበልን ምስኪን ሕዝቦች። በተለይ በፋሽስት ወያኔ ዘመን ረከሱ ሳይሆን ዋጋ አጡ መባል የሚገባን ምስኪን ሕዝቦች። ወያኔዎች ካንደኛው ችግር ወደ ሌላው፣ ከቀዳሚው መከራ ወደ ቀጣዩ እንደፈለጉ ሲያገለባብጡን ለምን ብለን መጠየቅ ያቃተን፤ እሽን ብቻ የተካንን ምስኪን ሕዝቦች። ፋሽስት ወያኔ ልጆቻችንን፣ ባለቤቶቻችንን፣ ወገኖቻችንን ባደባባይ በጠራራ ፀሐይ ዐይናችን እያየ በሕዝብ ፊት በጥይት ሲደፋቸው እያየን ”ሲያልፍ ያልፋል እስኪያልፍ ያለፋል” እያልን አንድም ቀን ሳይልፍልን እኛ ቀድመን በማለፍ ላይ የምንገኝ ምስኪን ሕዝቦች። ኢትየጵያኒዝም የተሰኘ የአሸናፊነት መንፈስ በቅኝ ግዛት ሲማቅቁ በነበሩ አፍሪካዊያን ወገኖቻችን፣ በላቲን አሜሪካና የሰሜን አሜሪካ ጥቁር ሕዝቦች ደም ውስጥ እንዲንተከተክ ምክንያት እንዳልነበርን፤ ዛሬ በፋሽስት ወያኔ ዘመን ግን ያንን መንፈስ የምንናፍቅ፣ እንዲያጋሩን የምንሻ አሳዛኝ ሕዝቦች ሆነናል።

ማንኛችንም በዝቅተኛ ደረጃ ለምናየው የአረብ አገር የግርድና ስራ እንኳ የፋሽስት ወያኔ አባልነት አልያም ደጋፊነት መስፈርት ሲሆን ጸጥ ብለን ተመልክተናል። ለኮብል ስቶን ማንጠፍ ስራ፣ በየቢሮው የጽዳትና ተላላኪነት ስራ ለመቀጠር ሳይቀር ወያኔነትን እንድንቀበል ስንጠየቅ ለምን ብለን ለመጠየቅ አቅም ያጣን ፋሽስት ወያኔ እንዳሻው እያደረገን ያለን ኢትዮጵያዊያን ነን እኛ ዛሬ። ለአባይ ግድብ ግንባታ ቦንድ ሽያጭ ፍላጎታችንን የማንጠየቅ፣ እንደ ህጻን የምንባበል ከዚያም ሲያልፍ በማስፈራራት የምንገደድ ነገር ግን ላለፉት ጥቂት የማይባሉ  ዓመታት በአፍሪካሀገሮች በታንዛኒያ፣ በማሊ፣ በሳውዝ አፍሪካ፣ በኡጋንዳ፣ በኬኒያ፣ በሱዳን፣ በጂቡቲና በሶማሊ ሳይቀር መከራ ፍዳችንን ስንቆጥር አንዳች ለኛ የሚቆም ያጣን። በመካከለኛው ምስራቅ ሳውዲ አረቢያን ጨምሮ በሌሎችም አረብ ሀገሮች የምድር ሲኦል ውስጥ ስንገኝ አይዟችሁ ብሎ አብሮ የሚታመም ገመና ከታች አርበኛ የምንሻ ሆነናል እኛ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ። በፋሽስት ወያኔ የጎጥ አገዛዝ ዘመን  ጉልበታችን፣ ሃሳባችን፣ ሃብታችንና ገነዘባችን እንጅ እኛ የማንፈለግበት ሚዛን የማንደፋበት እጅግ እጅግ የረከስንበት ዘመን ነው ዛሬ። ይህም ቢሆን ግን ለምን ብለንና ችግሩን ከመሰረቱ በማወቅ ወደ መፍትሄው ለመንደርደር ራሳችንን ያዘጋጀን አንመስልም። የዚህ ሁሉ ስቃያችን መሽከርከሪያ አናት ወያኔ ሆኖ እያለ ይህን ችግራችንን ለማስወገድ ግን በወያኔ ላይ ለመነሳት ተቸግረናል። ሰሞኑን በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ባለው ሰቆቃ እንኳ ፋሽስት ወያኔ ወገንን ለመታደግ ያደረገው የእገዛ እንቅስቀሴ አለመኖር እጅግ አሳፋሪ ከመሆኑም በላይ እነዚህ ወገኖቻችን በዚህ መልኩ ከሳውዲ እንዲወጡና ሌሎች ባስር ሺዎች የሚቆጠሩ  በወያኔ ርዳታ በግርድና ወደ ሳውዲ እንዲገቡ ፋሽስት ወያኔ ተስማምቷል መባሉ ብዙዎችን አቁስሏል። ተስፋ አስቆርጧልም።

ፋሽስት ወያኔ እንደ ዜጋ በየትኛውም የዓለም ክፍል ለሚደርስብን ችግር ከጎናችን ሊቆም ካልቻለና በተለይም ደግሞ ከጀርባችን እኛን ሊጎዱ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ የሚደራደር ከሆነ ከዚህ በላይ አንድ አድርጎ ሊያቆመን የሚችል ነገር ያለ አይመስለኝም።

በሃሳብ ልዩነት የተነሳ ወይም በዚህ ወይም በዚያ ይቃወሙኛል በሚል እሳቤ ብቻ ስንቶችን ወህኒ የሚጨምረው ወያኔ፣ ስለ እኔም ሆነ አሰራሬ ተችታችሁ ጻፋችሁ በሚል ብቻ ብዙዎችን የገደለው ያሰረውና የሰደደው ወያኔ፣ የሰራሁትን የግድያ ሚስጥር አወጣችሁ ጻፋችሁ በሚል ስንቶችን የት እንደደረሱ ደብዛቸውን ያጠፋው ወያኔ፤ ዛሬ በሳውዲ አረቢያ እየደረሰ ባለው ዓለምን አስጨንቆ የያዘ የወገኖቻችን የሞትና የመጎሳቆል አደጋ ከጎናቸው ከመቆም ይልቅ ይመርም ይክፋ በሀገራችን የዲሞክራሲን ጭላንጭል ብልጭ እናደርጋለን ብለው በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ራሱ ወያኔ እውቅና የሰጣቸው ሰላማዊ ፓርቲ መሪዎችን ጠልፎ ለመጣልና ለእርድ ለማቅረብ ተግቶ እየሰራ ይገኛል። ይህን ለማስፈጸምም ሲልም የሕዝባችንን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ አደጋ ውስጥ ከቶት ይገኛል። ወገኖቻችን በአረብ ሀገር ደራሽ አጥተው በጭንቀት ራሳቸውን ሲያጠፉ፣ በአረብ ፖሊሶች ደማቸው በየመንገዱ ሲፈስ፣ ማረፊያ አጥተው ሲንከራተቱ እገዛ ማድረግ የሚጠበቅበት ፋሽሰት ወያኔ ግን ጠቅላይ ሚንስትር ከሚባለው ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጀምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የወያኔ ቁንጮዎች ሙሉ ጊዜያቸውን ”ወያኔ ኦ ሚሊኒየም” ብለው በጠሩትና የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች እገዛ በማድረግ ላይ የነበሩ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ መሪዎችን በመግደል ላይ ያተኮረ የግድያ ኦፕሬሽን ለማስፈጸም ላይ ታች ይሉ እንደነበር ሲሰማ ፋሽስት ወያኔ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምን ያህል የወረደ ግምት እንዳለው ፍንትው አድርጎ ያሳያል።

ወገኖቻችን በአረብ ሀገር በተለይም በሳውዲ አረቢያ እጅ እግራቸው ታስሮ አቅም አጥተው በወጥመድ እንደተያዘ እንስሳ አይናቸው ርዳታ ፍለጋ ሲንከራተት ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው ፋሽስት ወያኔ ግን ለዚህ የወገን ችግር ፈጥኖ ከመድረስ ይልቅ በሀገራችን ሙሉ በሙሉ ሰላም ሰፍኗል ለማለትና ለዓለም ለማውራት የመልካም ስም ግንባታ ላይ ነበር።

ፋሽስት ወያኔ ይህንን የምስል ግንባታ በመቀጠል ምንም እንኳ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ለማለት በሚያስደፍር መልኩ የተረጋጋ ሰላም አለ ለማለት ባያስደፍርም በተለይ በምስራቁ የሀገራችን ክፍል በኦጋዴን የሰፈነውን የሰላም እጦት ለመሸፈን፤ በተለይ ሁለት የስዊድን ጋዜተኞች ባካባቢው የሚገኙ ታጣቂዎችን ሲያግዙ ተያዙ በሚል ድራማ እንዲሰሩና ይህም በፊልም መልክ እንዲቀረጽ በማድረግ ወያኔ ከሶ ካስቀጣቸው በሗላ በይቅርታ ተለቀው ሚስጥሩን ካጋለጡ ወዲህ የተፈጠረውን አካባቢውን የተመለከተ እውነት ለመገልበጥና ቆንጆ አድርጎ በማቅረብ ዓለምን ለማታለል ፋሽስት ወያኔ ሲደክም ቆይቷል። ከዚህ በፊትም ሆዳም አርቲስት ተብየዎችን እና ጥቂት የወያኔ ቁንጮዎችን በከፍተኛ አጀብ አካባቢውን በማዞር ባካባቢው ሰላም አለ ለማስባል ሲሞክር ቆይቷል። ሰሞኑንም እንግዲህ ወገኖቻችን በሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ እገዛ ሲፈልጉ ፋሽስት ወያኔ ግን ወደፊት በኦጋዴን ጅጅጋ ለሚያከብረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እያለ ለሚጠራው በአል ዝግጅት ላይ ነው። አካባቢው ወጥ ሰላም ያለበት ነው ብሎ ለዓለም ለማሳየት ጥረት ላይ ነው። ሰላምን በማስከበር ሰበብ ያካባቢውን ሕዝብ ኑሮ በማደፍረስ ላይ ነው ፋሽስት ወያኔ። ፋሽስት ወያኔ በሳውዲ አረቢያና በሌሎችም አረብ ሀገሮች የሚገኘውን ወገናችንን ችግር፣ በሀገራችን በየትኛውም ቦታ እየደረሰ ያለውን አድሎ፣ ዘረኝነትና ኢፍትሃዊነት የራሳችሁ ጉዳይ ካለን ቆይቷል።

ፋሽስት ወያኔ የራሳችሁ ጉዳይ ቢል እኛ ዝም ብለን ልናይ አይገባንም። እየሆነና እየደረሰ ላለው መከራ ተጠያቂው በሀገራችን ኮርተን ሰርተን እንዳንኖርና በስደት ተዋርደን እንድንሞት ያደረገን ወያኔ ነው። በሀገራችን በዘር ላይ መሰረት ያደረገ አገዛዝን በማስፈን ማናችንም እንዳቅማችን እንደችሎታችን የላባችንን አግኝተን እንዳንኖር ያደረገን ፋሽስት ወያኔ ነው። ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ የወያኔ ተከታይ ለማድረግ ምሎ በስራ፣ በትምህርት፣ በውጭ እድል፣ በመዋእለ ንዋይ ፍሰትና በሌሎችም እድሎችና የገንዘብ ምንጮች በማታለል ወይም በማስገደድ ለህሊናቸው ያደሩትን ከጫወታ ውች ለማድረግ እየሰራ ያለው ወያኔ ነው። ታዲያ ይህን ሁሉ ግፍና በደል እያደረሰብን ያለውን ፋሽስት ወያኔ ተባብሮ ለመታገል ከዚህ የተሻለ ጊዜ ይኖር ይሆን? ታዲያ መኖሪያ ሀገር መጠለያ ቤት አሳጥቶ በስደት እያንከራተተን የሚገኘውን ፋሽስት ወያኔ ለማስወገድ ከዚህም የከፋ በደል መጠበቅ ይኖርብን ይሆን? ሕዝባችንን ከሰው በታች አድርጎ በመግዛት ሀገራችንን በመበጣጠስ ሀገር ሊያሳጠን እየጣረ ያለውን ፈሽስት ወያኔን ለመደምሰስ የሚመረጥ ጊዜና ቦታ ይኖር ይሆን? መልሱ የለም ነው። ወገኖቻችን ሲታመሙ አብረን ልንታመምና ገመናቸውን ልንከት ይገባናል። ሀገራችን በፈለገችን ሰአት ልንገኝላትና አቤት ልንላት ይገባል። ሀገራችንም ሆነች ሕዝባችን እርዳታችንን የፈለጉበት ትክክለኛው ጊዜ ደግሞ አሁን ነው። ለጥሪያቸው ምላሽ የመስጠት የሞራል ግዴት አለብን። ለጥሪያቸው ምላሽ በመስጠትና ፋሽስት ወያኔን በመታገል ለወገኖቻችንና ለሀገራችን ቤዛ እንሁን።

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on November 18, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: