RSS

ሁሌ አሸሸ ገዳዎ ይለም

20 Oct

ይኸነው አንተሁነኝ

ጥቅምት 20 2013

በጉልበት አሸናፊ ሆኖ በመውጣት ሰላምን ማምጣት አይቻልም። ሰላም ከመተሳሰብ ከመቻቻል ከመደማመጥና ለጋራ ጉዳይ በጋራ ከማሰብም በተጨማሪ የግልን ፍላጎት ለማሟላት ሌሎችን መጫን አስፈላጊ እንዳልሆነ በማመንና ይህንኑ እምነት በመተግበር ጭምር የሚጎለብት እሴት ነው። በጉልበት የማመን አስተሳሰብ ዘላቂ አሸናፊነትን አያስገኝም። የትላንቱ አሸናፊ በዛሬው አዲስ ጉልበተኛ ተሸናፊ መሆኑ ተፈጥሯዊ ሕግ ነውና። ሰውን ሊመራው የሚገባው ሊያሳድገውና ትልቅ ሊያደርገው የሚችለው የእምሮው የመመራመር አቅም ነው። ጉልበትን አእምሮ ሊመራውና ሊያዘው ይገባል። ያ ካልሆነ ግን ሰው ወደ እንስሳነት ደረጃ ዝቅ ይልና ሁሉን ነገር በጉልበቴ እፈጽመዋለሁ ወደሚል አስተሳስብ ይወርዳል። አንደዚህ ያለ በጉልበት የማመን ነገር ደግሞ ትላንት ባይሆን ዛሬ አልያም ነገ ማዋረዱ አይቀሬ ነው።

የህግ የበላይነት ደካማውን መብት ሰጥቶ ቀና የሚያደርገውን ያህል ጉልበተኛ ነኝ ብሎ የሚፏልለውን ደግሞ ኮርኩሞ በማስተካከል በእኩልነትና በመከባበር ላይ የተመሰረተ መሕበራዊ ግንኙነት እንዲፈጠር ያግዛል። የሰው ልጅ ወደ እንስሳነት በመውረድ በጉልበቱ ተማምኖ ፍጹም አስነዋሪ የሆነ ነገር እንዳይሰራም ይከላከላል። 

በተፈጥሮው ሕሊናዊ ዳኘነት የተቸረው ሰው ጥሩውን ከመጥፎው በመለየት ለመከወን አቅም ያለው ፍጡር መሆኑ እሙን ነው። ይሁን እንጅ ብዙ ጊዜ ግን በግል ፍላጎት ማየል የተነሳ ወይም ለወገንና ላካባቢ በማድላት አልያም ሌላ የሚለውን ክፍል ወይም ቡድን የበለጠ ለመጉዳት ይህን የህሊና ዳኝነቱን በመጫን ፍትሃዊ ያልሆኑ ድርጊቶችን በተደጋጋሚ በመፈጸሙ የተነሳ ራሱ ለራሱ ሁሉን የሚገዛ፤ ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ ሕግ ለማርቀቅ እንደተገደደ ይታመናል። ቢሆንም ግን በተለያዩ ጊዜያት በአንዳንድ የዓለም ክፍሎች አንዳንድ አምባገነን ገዥዎች ራሳቸው ወስነው የበላይ ህግ ብለው ያስቀመጡትን በመሻርና ከህግ በላይ በመሆን አስደማሚ ኢፍትሃዊ ድርጊቶችን መከወናቸው አልቀረም። አምባገነኖችን ልዩ ከሚያደርጋቸው ጉዳዮች አንዱም ይኸው ነው።

በዚህ ዘመን ባለማችን አሉ ከሚባሉት በጡንጫቸው የሚያስቡ አምባገነን ገዥዎች ደግሞ ፋሽስት ወያኔ ዋናው ነው። ፋሽስት ወያኔ ራሱ ላወጣው ህግ እንኳ የማይገዛ አመጸኛ ቡድን ከመሆኑም በላይ አይደለም ከኔ ውጭ ናቸው ላላቸው ይቅርና አብረውት ሲታገሉ የነበሩ ዘለው ያልጠገቡ ወጣቶችን ሂዎት በስበብ ባስባቡ ለመቅጠፍ ያልተመለሰ ጠባብ ቡድን ነው። ፈጽሞ ለህሊናም ሆነ ለህግ የሚገዛ ቡድን አልነበረም አይደለምም።

ገና ያኔ ጥቂት ሆነን ትግል ጀመርን ካሉበት ጊዜ ጀምሮ መሪ የተባሉት ያቀረቡትን ሃሳብ የተቃወሙ በሙሉ ተራ በተራ አልቀዋል። አወጣነው የሚሉትን አለቆችን በተለይ የማይመለከት የጫካ ህግ ጥሳችሗል በሚልም ስንት የድሃ ልጅ ሂዎቱን ገብሯል አሁንም እየገበረ ይገኛል። በተመቻቸው ጊዜና ሁኔታ ሁሉ ያሻቸውን እንዲያደርጉት በችሮታ የተሰጣቸው ይመስል የኢትዮጵያን ሕዝብ ከሰው በታች አድርገው እየገዙት ይገኛሉ። ያዘዙትን ከማድረግ በቀር በሌላ ባንዳች እንኳ ጥያቄ እንዳያነሳ የማድረግን አቅም በደህንነታቸው በጦር ሃይላቸውና በፖሊሶቻቸው አማካኝነት በሃይል አጎልብተው ተቆጣጥረውት ይገኛል።

በኢትዮጵያ ክልል እስከሆነ ድረስ ወያኔዎች ያለመነካት መብታቸውን አስከብረው በጠባቂዎቻቸው ታጅበው ደረታቸውን ገልብጠው የፈለጉት ቦታ ቢደርሱ ያሻቸውን ኢፍትሃዊ ድርጊት ቢከውኑ ልምን ብሎ የሚጠይቅ አንዳች ሃይል የለም። በኢትዮጵያ ክልል እስከሆነ ድረስ የፋሽስት ወያኔ መሪዎችን የሚናገር አይደለም ቀና ብሎ በቅርበት የሚመለከት ሁሉ አሳር ያገኘዋል። ህጉም ቢሆን እነሱን ለመከልከል አቅም የለውም። ታዲያ ይህ ሁሉ ጉልበትና ድንፋታ በኢትዮፕያ ክልል ወይም በሌሎች ወዳጅ አምባገነን ጎረቤት መንግስታት ውስጥ እስከሆነ ድረስ ብቻ ነው።

ወያኔዎች እነሱም ልክ እንደሌላው ሰው መሆናቸውንና ከሌላው የተለዩ አለመሆናቸውን የሚያውቁት በዴሞክራሲ ያደጉ ከሚባሉት ሀገሮች በተለይም አውሮፓና አሜሪካ ሲገኙ ነው። ያ ሁሉ ትእቢትና ማንአህሎኝነት፣ ያ ሁሉ ሰው መናቅና የበላይነት እንክሽክሽ ብሎ እግራቸው ስር በመውደቅ እንደማንኛውም ሰው እኩል የሚታዩበት ከሀገር ርቀው እንደ አውሮፓና አሜሪካ ባሉ ሀገሮች ሲገኙ ነው። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ባለራዕይ የሚሉት መሪያቸውን ጨምሮ ትልልቅ የወያኔ ቁንጮዎች አፋኝ አሳሪና ገዳይ መሆናቸው፣ አገር ሻጭ መሆናቸው፣ ጨቋኝ አምባገነን መሆናቸው ፊት ለፊት እያዩ እውነት መሆኑን እስኪጠራጠሩ ድረስ አይናቸውን እያሹ ጆሯቸውን አቁመው አዳምጠዋል። የሰሞኑ ባለተራ ደግሞ አቦይ ስብሃት ነበር። ሽማግሌው ስብሃት ነጋ ከሕወሃት መመስረት ጀምሮ ኢትዮጵያ በብሔር ብሔረሰብ ግጭት እንድትታመስ፣ በሃይማኖቶች መፋተግ እንድትጨነቅ ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል። እየተጫወተም ነው። ስብሃት ነጋ በተለይ የአማራን ብሔር እና ኦርቶዶክስን ለማጥፋትና ለማፈራረስ ራሱን የዚህ ጉዳይ አቀንቃኝ አድርጎ በመሾም ብዙ ብሏል አድርጓልም። የሕዝባችንን መብትና ነጻነት በመግፈፍ የዘመናችን የኢትዮጵያ ቁጥር አንድ ማፍያ መሆኑም ያታወቃል። ታዲያ ይህ ሁሉ ከሁሉ በላይ መሆን ለካ ኢትዮጵያ ውስጥ እስካለ ድረስ ብቻ ነበር።

ይህን ሁሉ ጉድ በሀገራችን ሕዝብ ላይ ሲከውን የኖረው ተንኮለኛው ስብሃት ነጋ ነው እንግዲህ በጠባቂዎቹ ፊት ”አንተ ወንጀለኛ ነህ አንተ የብዙ ንጹሃን ኢትዮጵያዊያን ደም በእጅህ አለ፣ በግፍ ስለሞቱት ያለፍትህ ስለታሰሩት የነጻነት ታጋዮች ምን ትላለህ?” ህግ ባለበት ሀገር አንተ ከማንም እንደማትበልጥ አሁን  እያየህ ነው፤ በግፍ ያለፍርድ ስለገደልካቸው ንጹሃን ኢትዮጵያንስ ምን ትላለህ? እና ሌሎችንም ጥያቄዎችን ሲጠየቅ እባቡ ስብሃት ነጋ ቀና ብሎ ለማየት እንኳ አልደፈረም። ህግ ማለት ይህ ነው። ህግ ማለት ትዕቢተኞችን በዚህ መልኩ አንገት ሲያስደፋ ነው። ህግ ማለት የአንድን ሰው መብት የደፈረ አምባገነንም ሆነ ሌላ ባለስልጣን ሁሉ እንደማንኛውም ሰው  ለፍርድ ሲቀርብ ነው። በሀገራችን ሆኖ ባናየው እንኳ ጎጠኛው ስብሃት ነጋ አይማርበትም እንጅ የህግን የበላይነት በአሜሪካ ተመልክቷል።

ጥጣቄ እየጠየቀው የነበረውን ኢትዮጵያዊ በማስደብደብ እና መኪና ገጭቶ በማምለጥ ወንጀልም ስብሃት በአሜሪካ ፖሊስ እየተፈለገ መሆኑ ይሰማል። ከዚህ የምንረዳውም ሁሌ አሸሸ ገዳዎ አለመኖሩን ነው። በኢትዮጵያ ስብሃት ከህግ በላይ ነበር፤ ስብሃት ያለው ይፈጸማል። ስብሃት እንዲሞት የፈረደበት ይሞታል። ይህን ብዙ ጊዜ እንዳደረገው የስብሃትን ታሪክ ከጻፉ ጓዶቹ ማወቅ ተችሏል። ዴሞክራሲ የሰፈነባቸውና የሰው ልጅ መብት የተከበረባቸው አውሮፓና አሜሪካ ያለው ታሪክ ግን ሌላ ነው። በነዚህ አካባቢዎች ስብሃት ወንጀል መስራት አይደለም ከዚህ በፊት በሰራው ወንጀል ሊከሰስም ይችላል።

እንዲህ ያለው በሰራነው ወንጀል ባጠፋነው ትፋት እንከሰሳለን የሚል ስጋታቸውም ነው በኢትዮጵያ መሪነትና አስተባባሪነት መላውን አፍሪካ በማቀናጀት የአለም አቀፉን ወንጀል ፍርድ ቤት ላለመቀበል እያስሮጣቸው የሚገኘው። ሕግ ይህን ያህል አስፈሪ ነው። ስለሆነም ለተንኮለኛው ስብሃት እንደፈለጉ መዘላበድና ያሰቡትን ሁሉ ውጤቱን ሰይገምቱ ዝም ብሎ ለመከወን መሞከር  ያልተዋረደ ስብእና የለህም እንጅ ያዋርዳል ያቀላልም ልንለህ እንወዳለን። ያንተም ሆነ የፋሽስት ወያኔ ድርጊት የህግ የበላይነት ባለባቸው ሀገሮች ዋጋ ያስከፍላልና። አበቃሁ።

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on October 20, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: