RSS

ተስፋዬ ገ/አብ እንደ “ካቡጋ”

04 Oct

bbb
በጋዜጠኛነት ስም መድረክ በማበጀት በኢትዮጵያዊያን ሚዲያ ኢትዮጵያን ለማፈራረስና ህዝቧ እርስ በርስ እንዲባላ ተልዕኮውን ሲያስፈጽም የነበረው ተስፋዬ ገብረ አብ በሰነድ የተረጋገጠ ማንነቱ ገሃድ ሆነ። ዜናውን የሰሙ እንዳሉት ተስፋዬ ካሁን በሁዋላ “በቁሙ ሞተ” ነው የሚባለው ሲሉ ተደምጠዋል።
በኢትዮጵያ የኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ይሰሩ እንደነበር የገለጹ የጎልጉል መረጃ ሰጪ “ተስፋዬ አስቀድሞም ቢሆን ሆን ብሎ በተቀነባበረ ስልት ጦርነቱ ሊጠናቀቅ ሲል ወታደር እንዲሆን የተደረገ የሻዕቢያ ሰላይ እንደነበር ይታወቃል” በማለት ለጎልጉል ተናግረዋል። “ተስፋዬ አሁንም በደም ከሚገናኛቸው የህወሃት ሰዎችና የደህንነት የላይኛው መረብ ጋር ግንኙነት አለው” ያሉት እኚሁ ሰው አጋጣሚው “በወያኔ ላይ ጠጠር የሚጥል ሁሉ …” በሚል ጭፍን አመለካከት በጅምላ ለምንነዳ ወገኖች ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ እንደሆነ አመልክተዋል።


“ግሪን የሎ ሬድ” በሚል የፓልቶክ ተቀጽላ ስም የሚታወቁት አገር ወዳድ በተደጋጋሚ ተስፋዬን ሲሞግቱና ማንነቱን ሲገልጹት፣ ተስፋዬ በመለሳለስ ያልፍ እንደነበር ያስታወሱት እኚሁ ሰው “ተስፋዬ ላይ የሚሰበሰቡ መረጃዎች ከተጠናከሩና ከዜና አልፈው ወደ ህግ የሚያመሩ ከሆነ እሱ ላይ ምስክር ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን ማቅረብ የሚችሉ ወገኖች አሉ፤ በጽሁፍ እስካሁን ያሳተማቸው በበቂ መረጃነት ሊቀርቡ ይችላሉ” ብለዋል።
በሩዋንዳ በተካሄደው የዘር ማጥፋት (ጄኖሳይ) በዋንኛነት ከሚጠቀሱት መካከል የሚዲያውን ኃይል በመጠቀም RTLM (Radio Télévision Libre des Mille Collines) በተሰኘው የሬዲዮ ማሰራጫ አማካኝነት የተነዛው የዘር ጥላቻ ተጠቃሽ ነው፡፡

ll
ይህንንtesfaye andkabuga ተግባር ሲፈጽሙና ሁቱዎች በቱትሲዎች ላይ እንዲነሱ ያደረገውና ቱትሲዎችን “በረሮ” (“cockroaches”) እያለ በመጥራት “እንዲገደሉ” በሬዲዮው አማካኝነት “ትዕዛዝ” ሲሰጥ የነበረው ፌሊሲዬን ካቡጋን (Félicien Kabuga) ዋነኛ ተጠቃሽ ነው፡፡ የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በሩዋንዳ ዘር ማጥፋት ዙሪያ ባደረገው ጥናት ካቡጋን እና የሬዲዮ ጣቢያው ልፈፋ ለ51ሺህ ሰዎች መገደል ቀጥተኛ ተጠያቂ አድርጓል፡፡ ይህም በአጠቃላይ ከተጨፈጨፉት ሰዎች ውስጥ 10በመቶ መሆኑን ጥናቱ ጠቁሟል፡፡
በዓለምአቀፉ ፍርድቤት በወንጀለኛነት ተከስሶ እየተፈለገ ያለው ካቡጋን እስካሁን ሳይያዝ ቀርቶ በአሁኑ ጊዜ በኬኒያ ራሱን ደብቆና በከፍተኛ ባለሥልጣናት ሽፋን ተሰጥቶት ይገኛል የሚል ግምት፡፡
የተስፋዬ ጉዳይ በህግ መታየት አለበት በማለት ሲወተውቱ የነበሩ ሁሉ ይህ አሁን የወጣውን መረጃና ሌሎች ዘርን ከዘር ጋር እንዲጋጭ ለማድረግ የሚዲያን ኃይል በመጠቀም የፈጸመውን ተግባር በሩዋንዳ ከሆነው ጋር ያገናኙታል፡፡ አክርረው ሲናገሩም “ተስፋዬ ማለት ካቡጋ ነው፤ የቡርቃ ዝምታ ደግሞ የካቡጋ ሬዲዮ RTLM ነው” ይላሉ፡፡ ስለሆነም “ሆላንዳዊው” ተስፋዬ እንደ ካቡጋ “ወደ አባት አገር” በመሄድ ከመሸሸጉ በፊት ውጤታማ ሥራ መሰራት ያለበት አሁን ነው ይላሉ፡፡
ዳኛ ወልደ ሚካኤል መሸሻ ጊዜ ወስደው ያቀረቡት የአለማየሁ /ትንታግ/ ድንቅ የምርመራ መረጃ ውጤት ይፋ አንዳደረገው ተስፋዬ ክቡር በሆነው የጋዜጠኛነት ሙያ ተሸሽጎ በውጪ አገር ያሉትን ስደተኞችና ድርጅቶች የሚሰልል፣ በተቀነባበረ ትዕዛዝና መመሪያ በጀት ተመድቦለት ኢትዮጵያ ውስጥ ተስማምተው የሚኖሩ ቤተሰቦች ደም እንዲቃቡ የሚሰራ ወንጀለኛ ነው።
በልጅነቱ ወቅት በአንደበቱ “ኢትዮጵያዊ አይደለሁም” በማለት ለአስተማሪው መናገሩን የመሰከረውና አስተማሪው ተናደው በጥፊ ስለመቱት መቆጨቱን የተናገረው ተስፋዬ “ከኢትዮጵያውያን ታሪካዊ ጠላቶች በጀት ተመድቦለት የሚሰራ፣ ሆዱን ከሞላና ለሴሰኛነቱ ጥማት መወጫ ኪሱ ካበጠ ህሊና የሌለው ተራ ሰው በመሆኑ መረጃ ተገኘ በሚል የማይገባውን ደረጃ መስጠት አግባብ አይደለም” የሚሉት አስተያየት ሰጪ “ተራ ሰዎችን ህግ ፊት በማቅረብ ማስቀጣት ግን ለአፍታም ሊዘነጋ አይገባውም” ሲሉ በሰብአዊ መብት ዙሪያ እንሰራለን ለሚሉ ወገኖች የማስተባበሩን ስራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ “አድሚን” “ሙያዬ ምስክር” “የቡርቃ ዝምታን በመጻፍህ ህዝብን ይቅርታ ትጠይቃለህ?” በሚል ላቀረበችለት በማብራሪያ የተደገፈ ጥያቄ “ይቅርታ አልጠይቅም” በማለት ታብዮ መልስ ሰጥቶ የነበረው ተስፋዬ አሁን ለቀረበበት በማስረጃ የተደገፈ ወንጀልና የማንነቱ መገለጫ መልስ ሊኖረው እንደማይችል፤ አለኝ የሚል ከሆነም ፍርድቤት ቢያቀርበው የሚሻል እንደሆነ ይገመታል፡፡
በዲያስፖራ ውስጥ ላሉት ወገኖች ታላቅ ትምህርት እንደሚሆን የተነገረለት የተስፋዬ ማንነት መገለጽ አሁንም በተለያዩ ድረገጾች ፌስቡክን ጨምሮ በተለያዩ አምዶች ጽሁፍ የሚለጥፉትን ሁሉ በርጋታ መመልከት እንደሚገባው የሚያመላክት እንደሆነም አስተያየት እየተሰጠ ነው።
አገር ቤት ሆነውም ሆነ በውጪ ተቀምጠው ሰዎች የመሰላቸውን ስለጻፉ ቅጽበታዊ “የጀግና ማዕረግ” በመስጠት ተራ “ሸብ እረብ” አስፈላጊ እንዳልሆነ የሚጠቁሙ ወገኖች ተስፋዬ አስቀድሞ በወገን ሚዲያ ወገንን ለማፈራረስ ላቀደው ሴራ ድር ማድሪያ ሲገለገልበት የተቃወሙ፣ “ገብረ እባብ” በማለት ለማጋለጥ የደከሙ ወገኖች እንደነበሩ በመጥቀስ ለወደፊቱ በጅምላ ከመነዳት መቆጠብ ተገቢ እንደሆነ ይመክራሉ።
ከሰነዱ ከተገኙት መረጃዎች መካከል ተስፋዬ በእጁ የጻፈው ይህ መረጃ ይገኛል፡-
“ኢትዮጵያዊያን የኤርትራ ታሪክ በትክክል እንዲያውቁ ይረዳል። ይህም በአዲሱ የኢትዮጵያ ትውልድ አእምሮ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል እንዳልነበረችና እንደማትሆንም የአመለካከት ዘር መዝራት ያስችለኛል። ለዚህ ሥራም የናንተ መ/ቤት ሆነ ህገደፍ (ሻዕቢያ) ሰነዶችን እንድመለከት በመፍቀድ ያግዘኝ ዘንድ እመኛለሁ። እነዚህ መጻሕፍትን ጽፌ እስከምጨርስ ሁለት ዓመት ይፈጅብኛል። ቢያንስ በቢሮና በጽሕፈት መሣሪያዎች እንዳልቸገር ብደረግ እመኛለሁ።” …
cc“በኤርትራ ጉዳይ፣ በሻዕቢያ አላማዎችና አሰራሮች፣ እንዲሁም ኢሳያስን በተመለከተ ያለኝ በጣም ግልጽ ነው። ከነሙሉ ችግራችን ኤርትራ በትክክለኛው ሃዲድ ላይ እየተጓዘች ነው ብዬ አምናለሁ። የሚታረሙ ነገሮች ካሉ ዋናው ጉዞአችን ሳይነካ እየተስተካከለ ሊሄድ ይችላል ብዬ አምናለሁ። የምጽፈውም ሆነ የምሠራው ይህን መሠረት ያደረገ ነው።” …
“አሻግሬ ስመለከት በርቀት ሰማያዊ ተራሮች ይታየኛል። ከተራሮቹ ስር ያለው ለጥ ያለ የእርሻ ሜዳ የአባቴ አገር ነው።” …
“ይህን ታሪክ እጽፈዋለሁ: 3 ተከታታይ መጽሐፍ ሊወጣው ይችላል። ባህረነጋስያን በመጀመር የኤርትራን ታሪክ እጽፈዋለሁ። የሻቢያን የትግል ታሪክ እጽፈዋለሁ። ይህም ኢትዮጵያዊያን ስለኤርትራ ተገቢውን ሃቅ እንዲገነዘቡ ያደርጋቸዋል። በዚህ መጽሐፍ ጠላት አፈራለሁ። ቢሆንም ግን እጽፈዋለሁ። ስለዚህ ከአሁኑ ፍንጭ መስጠቱ ጠቃሚ ነው። በተቃውሞ የምጽፍ የሚመስላቸው ስለሚኖሩ እስከዚያው ድረስ ይዝናኑበት። ኤርትራ ለመመለሴ ምክንያት ይሰጥልኛል።”
ይህ ታላቅ አገራዊ ማንነት ላይ ያነጣጠረ ደባ በአገር ቤትም ሆነ በውጪ ያሉ ሚዲያዎች ህዝብን በማሳወቅ ረገድ የሚፈተኑበት አበይት ጉዳይ ነው፡፡
የደራሲው ማስታወሻ በታተመበት ወቅት በሽፋን ገጹ ላይ ሊነበብ የሚገባውና ታላላቅ ቁምነገሮች ያሉበት መጽሐፍ መሆኑን በመጥቀስ ኢትዮጵያውያን እንዲያነቡትና መጽሐፉም እንዲሸጥ በተገኘው ሚዲያ ሁሉ የማስታወቂያ ሥራ የሰሩም እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

http://www.goolgule.com/

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on October 4, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , , , , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: