RSS

ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት ሕዝቡ በታዘበውና ባስተናገደው የሰሞኑ ውድድር ፋሽስት ወያኔ መቶ በመቶ ተቀድሟል ተበልጧልም

03 Oct

ይኸነው አንትሁነኝ

ጥቅምት 3  2013

ውድድር፣ ቅስቀሳ፣ ትምህርት፣ ስብሰባና እነዚህን መሳይ ድርጊቶች ነጻ ሆኖ ማሰብንና መከወንን ይፈልጋሉ። ከየትኛውም አካል ተጽእኖ የጸዱ ካልሆኑ አስተማማኝነታቸውም ሆነ ዘላቂ ውጤታማነታቸው ያጠራጥራል። ስለሆነም ውድድር ምንም አይነት ይሁን ብቻ ላንደኛው ተወዳዳሪ በሚጠቅም መልኩ ተጽእኖ ሲኖርበት አያምርም። በተለይ ተጽእኖ አድራጊው ከተወዳዳሪዎች አንዱ ሲሆን ደግሞ ውድድሩ የተበለሸ ይሆናል። እጅግ ሲበዛ ደግሞ ለውድድሩ ግብአት አቅራቢና አስፈጻሚ የሆኑ ተቋማትን ከተወዳዳሪዎቹ አንዱ ተቆጣጥሮ እሱ በሚፈለገው ምልኩ እንዲያስፈጽሙ ካደረገ ውድድሩ አንድኛውን የሞተ ይሆናል። ይሁን እንጅ የህዝብ ዐይን ሁሉን ያያልና ምንም እንኩዋ አካሄዱም ሆነ ውጤቱ የተገለባበጠ ቢሆን ትክክለኛው አካሄድ ምን መምሰል እንደነበረበት ብቻም ሳይሆን ውጤቱ የማን እንደነበረም ጭምር ያውቃል። አድል ከገጠመውና መድረክ ካገኘም ይህን ሁሉ ለማጋለጥ ወደ ሗላም አይልም። የህን ጽሁፍ ስታነቡ ምርጫ አልደረሰም አሁን ታዲያ ስለምን ውድድር ነው የሚነግረን ትሉ ይሆናል። አወ እርግጥ ነው አሁን ምርጫ የለም ነገር ግን ውድድሮች ሁልጊዜም አሉ። ሰሞኑንም በፋሽስት ወያኔና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ውድድር ነበር። ፋሽስት ወያኔ ተቃዋሚዎችን ጥላት ለመቀባት ተቃዋሚዎች ደግሞ ማንነታቸውን ላማሳየት ሲደረግ የነበረ ውድድር፤ ፋሽስት ወያኔም ሆነ ተቃዋሚዎች ሕዝብን ከጎነቸው ለማሰልፍ ሲያደርጉት የነበረ ውድድር፤ ሁለቱም የኢትዮጵያ ሕዝብ ከማን ጋር እንደቆመ አስረግጦ ለማሳየት ሲያደርጉት የነበረ ውድድር፤ በሌላ በኩል ደግሞ ፋሽስት ወያኔ የተቃዋሚውን እንቅስቃሴ ለመገደብ ተቃዋሚዎች ደግሞ ከዚህ አፈና በመላቀቅ አቅማቸውን ለማሳየት ሲያደርጉት የነበረ ውድድር፤ በመጨረሻም ሁለቱንም ግራ ቀኝ የተመለከተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለማንም ጣልቃ ገብነት የሰጠው አስተያየትና መልሱ የሰሞኑ ውድድሮች ጥቂት ገጽታዎች ነበሩ።

ፋሽስት ወያኔ ባለፉት የአገዛዝ ዘመኖቹ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላም ተከባብሮ እንዳይኖር የሚያደርጉ ብዙ አፍራሽ ስራዎችን ሰርቷል። በአንድነት ፋንታ ልዩነትን፣ በፍቅር ፋንታ ጥላቻን ሰብኳል። በብሔር ብሔረሰብ፣ በቋንቋ እና በሃይማኖት ሰበብ አንዳችን ካንዳችን እንዳንዋዋጥ ለማድረግ ተግቷል። ትምክህተኝነትና አሸባሪነት የሚሉ ቃላትን በማስቀደም ባንድ ብሔረሰብ፣ ቡድን ወይም በተወሰኑ ግለሰቦች ላይ ሕዝብ እንዲነሳ ለማድረግ አቀንቅኖባቸዋል። ላለፉት ሙሉ የአገዛዝ ዘመኖቹም ፋሽስት ወያኔ እነዚህኑ ቃላት በመጠቀም ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ሰርቶባቸዋል። ሆኖም ጥረቱ ወያኔ ያሰበውን ያህል የተሳካ አልነበርም። ወያኔ ወደ አገዛዝ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁንም ድረስ የምናየው እውነት የኢትዮጵያ ሕዝብ ፋሽስት ወያኔ እንደፈለገው ሳይሆን በተቃራኒው ሲንቀሳቀስ ነው። ለዚህም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚ ሃይሎች ሕዝባችንን በተፈለገው ደረጃም እንኳ ባይሆን በማንቃትና በማስተባበር ያቅማቸውን በመስራታቸው እና አሁንም እየሰሩ በመሆናቸው ነው። የዚሁ ቀጣይ የሆነው ወያኔን የማጋለጥና የማዳከም ድርጊት እንዲሁም ሕዝብንም የማንቃት እንቅስቀሴ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ ሲሆን የዚሁ ተቃራኒ የሆነው የፋሽስት ወያኔ ተንኮል የተሞላበት እንቅስቃሴ ግን እንዳልሰመረለት እየተስተዋለ ነው።

በሀገር ውስጥ በተቃዋሚ ፓርቲዎች የተመራ የፋሽስት ወያኔን አፈና፣ እስራት፣ ግርፋትና ግድያ አሸንፎ ፈንድቶ የወጣው ተከታታይ የሕዝብ ሰላማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴና ትልልቅ ስብሰባዎች ወያኔን ያስደነገጡ ሲሆን በተለይ ራሱ በጠራው የድጋፍ ሰልፍ ከፍተኛ ተቃውሞ መሰማቱ ወያኔ ብቻውን መቅረቱን ባደባባይ አሳብቆበታል። ይህም የፋሽስት ወያኔን ጣልቃ ገብነትና ተጽእኖ አሸንፎ በወጣው የሰሞኑ እንቅስቃሴ እውነተኛ የሕዝቡ ፍርድ የታየበትና ወያኔ እጅ እንደሰጠ የሚያረጋግጥ ሃቅ ነበር። በውጭ ደግሞ ወያኔ ሰብሬዋለሁ ወይም እየሰበርኩት ነው ያለውን የሕዝብን በመከባበር አብሮ የመኖር ወርቅ ባሕል ከፍ የሚያደርጉ፣ ግንኙነታችን የበለጠ ተጠናክሮና ተስተጋብሮ መቀጠል እንዳለበት የሚያስገነዝቡ፤ ፋሽስት ወያኔ ልዩነታችን እያለ ሁሌ የሚለፈውም ቢሆን ወያኔ ለፕሮፓጋንዳ ያለው እንጅ ሕዝባችን በፍቅር አብሮ እየኖረ እንደሆነ የሚያረጋግጡ ስብሰባዎችና ሰላማዊ ተቃውሞ ሰልፎች ውጭ በሚገኘው የተቃውሞ ሃይል አስተባባሪነት መደረጋቸው ለሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፍተኛ የሞራል ድጋፍ ከመሆኑም ባሻገር ዲያስፖራውን ለመያዝ በብዙ ሚሊዮን ዶላር ለሚያፈሰው ፋሽስት ወያኔ አፍንጫን በቦክስ የመመታት ያህል የሚያም ነበር።

አንዱ ሲበላሽበት በሌላው ይህኛው ሲጠፋበት በዚያኛው እያለ ያለው ፋሽስት ወያኔ፤ በተለይ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ የግንባር መፈክር ያደረገውን የአባይ ግድብን ለማንገስ የልማትና የቤት መስሪያ ቦታ እደላን እንዲሁም የኮንዶሚኒየም ቤት ግንባታን በማሰቀደም ዲያስፖራውን በማቁለጭለጭና በማባበል ለመያዝና ለመቆጣጠር ቢጥርም በሄደበት ሁሉ በቆራጥ ኢጥዮጵያዊያን ተጋድሎ የተከራየውን አዳራሽ እየለቀቀ ተዋርዶ እንደወጣ ያደባባይ ሚስጥር ሆኗል።

ፋሽስት ወያኔ በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከሕዝብ የተነፈገው ሞገስና በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የተቀበለው ውርደት ሳያንሰው የዚህ ሁሉ ድምር ግፊት በውስጡም ሰላም እንዲያጣ አድርጎታል። ከትምህርት ደረጃና አቅም ይልቅ ዘርና የጥቅም ተጋሪነትን በሚያንጸባርቀው የፋሽስት ወያኔ የስልጣን ክፍፍል ባለመደሰት ተፈጥሮ የነበረው የውስጥ ክፍፍል እጅግ ሰፍቶ ከመሰነጣተቅ ደረጃ ደርሷል። የወያኔ ቁንጮዎች አንዳቸው አንዳቸውን ለማጥፋት ምቹ ጊዜ በማስላት አጋጣሚውን ለመጠቀም ሲያደቡ እንደነበር ሰሞኑን በሙስና ሰበብ እየወሰዱት ካለው እርምጃ መረዳት ይቻላል። በዚህ የተነሳም አንዳንድ የፋሽስት ወያኔ መሪዎች ለስብሰባ ወይም ለስልጠና በማለት ወደ ውጭ በመውጣትና በዚያው በመኮብለል ”ከነገሩ ጦም እደሩ” ያሉ ይመስላል። እንደ አርከበ እኩባይ አይነቶቹ ደግሞ ሕወሃት ከነግማትሽ እዚያው ተግማሚ ብለው ሙሉ ቤተሰቦቻቸውን ጠቅልለው በስተርጅና የስደት ሂዎትን ሀ ብለው እየጀመሩ ይገኛሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ ፋሽስት ወያኔ እያደረሰው ባለው የመብት ረገጣና የዲሞክራሲ እጦት ምክንያት እየሆነ ያለውን ስደት እስራትና ሞት እየተቹ ያሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሁሉን አቀፍ አቤቱታ ምክንያት ፋሽስት ወያኔ እንደ ጉድ የእርዳታ ዶላር ከሚያፈሱለት ወዳጅ ምእራባዊያን ሀገሮች እንዳይነጠል በመስጋት በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ይገኛል። አንዳንድ ምእራባዊያን ሀገሮችም ካሁኑ ጥያቄዎችን እያነሱ ሲሆን በዚህ በኩልም ቢሆን መጪው ዘመን ለፋሽስት ወያኔ የጭንቅና የአጣብቂኝ እንደሚሆን ጥርጥር የለም።

እነዚህ ሁሉ እንግዲህ ባጋጣሚ የተከሰቱ ሳይሆኑ  ዓለማቀፋዊ ሁኔታና ነባራዊው የትግል ሂደት የፈጠራቸው ኩነቶች ናቸው። ድምር ውጤታቸውም በተለይ ለፋሽስት ወያኔ የአገዛዝ ዘመኑ ማክተሚያ መድረሱን የሚያረዱ የመጨረሻ ተከታታይ ደወሎች ሲሆኑ ለተቃዋሚው ደግሞ ሀገር ለመምራት የሚችሉ መሆናቸውን የሚያሳዩበት፣ ብቃት ያለው የሰው ሃይል እንዳላቸው የሚያስመሰክሩበትና ሕዝብን ማደራጀትና መምራትን በተግባር የሚያሳዩበት ወቅት በመሆኑ በተለይ ተቃዋሚው ሃይል ሀገር ለመምራት እንደቀረበ ራሱን አሳምኖ በሁሉም መስክ ተጠናክሮ መታየት ይኖርበታል።

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on October 3, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: