RSS

ፋሽስት ወያኔ የገደለው ባልሽ የሞተው ወንድምሽ ሃዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ ይሉት ጫወታ የዟል

28 Sep

ይኸነው አንተሁነኝ

መስከረም 28 2013

አንድን ነገር አደርጋለሁ ብሎ በመናገርና ጉዳዩን በመተግበር መካከል ከፍተኛ ልዩነት አለ። ማድረግ ወይም ቃልን እንዳሉት መፈጸም እንደመናገር ቀላል አይደለም። መክንያቱም ከጊዜ እርዝመት ጋር አደርገዋለሁ ያሉትን ነገር ለመከወን የግል ተነሳሽነት መቀዝቀዝ፣ ያቅም ውሱንነት፣ እንዲሁም በጊዜው የተፈጠረው አዲስ የአካባቢ ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ደንቃራ ሊፈጥር ስለሚችል ነው። ምንም ይሁን ምን የተናገሩት እንዳሉት ሳይከወን ሲቀር በተለይ ለተናጋሪዎች እጅግ በጣም ቢያንስ ባካባቢው መሕበረሰብ ትዝብት ውስጥ መግባትና ክብር ማጣትን ጨምሮ ለወደፊት የሚናገሩትም እንዳይታመንና ተቀባይነት እንዲያጡ ያደርጋል።

እጅግ ሲከፋ ደግሞ በቃላቸው ያልተገኙት ሰዎች የመንግስት ወኪሎች የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የማሕበረሰብ መሪዎች ከሆኑ ደግሞ እንደያስፈላጊነቱ ይዘውት ከነበረው የመንግስትና ሃይማኖት የውክልና ደረጃ እንዲነሱ ከመደረጉም በላይ በጉዳዩ በሕግ የሚጠየቁበት ሁኔታ ይፈጠራል። የማሕበረሰብ መሪዎች ከሆኑም የማሕበረሰቡን አመኔታ ስለሚያጡ ሳይወዱ በግድ መሪነቱን ለሌሎች የሚያስረክቡበት ሁኔታ ይፈጠራል። ከዚህ አጠቃላይ ገለጻ ስንነሳ ታዲያ ባንድ አጋጣሚ የምንይዘው የክብር ወንበር ሰዎችን እንድናገለግልበት እንጅ እንድንበድልበት ወይም ከዓለምም ሆነ ከህሊና ሕግ ውጭ እንድንፈነጥዝበት አለመሆኑን እንረዳለን። በዚህ መልኩ ሳንንቀሳቀስ ብንገኝ ግን ቀደም ብየ ለመግለጽ እንደሞከርኩት አለመደመጥን፣ መናቅን፣ መገለልንና ክብር ማጣትን የመሳሰሉ ልማዳዊ የማሕበረሰብ ቅጣቶችን ጨምሮ በወንጀል መከሰስንና መቀጣትን ሊያስከትል ይችላል። ይህ እንግዲህ በየትኛውም ሁኔታ ላይ ብንገኝ ባጠፋነው ጥፋት በበደልነው በደል ሊያጋጥመን የሚችልን የህሊና ጠባሳ እና ወቀሳን ሳይጨምር መሆኑ ነው።

”በታላቁ መጽሐፍ ባንድ ቦታ ሐናንያና ሰጲራ ስለሚባሉ ባልና ሚስቶች ከላይ የጠቀስኩትን የመሰለ ትሪክ ከነቅጣቱ እናነባለን። እነዚህ የትዳር ጋደኞች መሬታቸውን ሸጠው የሚያገኙትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ላምላካቸው ለማስገባት ቃል ገቡ። በዚያ ዘመንም ሆነ አሁን በሚኖረው ማሕበረሰብ ለቤተ መንግስትም ሆነ ለቤተ እምነት የተገቡ ቃሎች እንዲፈጸሙ ይጠበቃሉ። ሆኖም ግን ከመሬት ሽያጭ ያገኙት ገንዘብ እነዚህን ጥንዶች አባበላቸው። ከመሬት ሽያጭ ካገኙት ትንሽ ቀንሰው ለራሳቸው በማስቀረት ሙስና ለመስራት ተወያዩና ወሰኑ። ሙስናውን ተአማኒ ለማድረግም ባል የተናገረውን ውሸት ሚስት እንድትደግመው ተነጋግረው ተስማሙ። አደረጉትም። ይህን በማድረጋቸው ታዲያ እንዲሁ እንዳልታለፉ ይልቁንስ ከፍተኛውን ቅጣት እንደተቀብሉ ታላቁ መጽሐፍ ያስረዳናል።” 

ሙስና ዘርፈ ብዙና እንደ ሸረሪት ድር የተወሳሰበና የጥፋት ደረጃውም ሰፊና ጥልቅ ነው። ሙስና አንድ ሰው ብቻውን ሊፈጽመው የሚችለው ጉዳይ አይደለም። ከላይ እንዳየነው ታሪክ ሁለትና ከዚያም በላይ የሆኑ ሰዎች በትብብርና በስምምነት የሚፈጽሙት ጉዳይ እንጅ። በተለይ አሁን በሀገራችን እያየነው ያለው ግዙፍ የሙስና ወንጀል በፍጹም ባንድ ሰው ወይም በጥቂት ሰዎች ትብብር የሚከወን አይደለም። ይህ የሀገራችን ንቅዘት የወያኔ ትላልቅ ባለስልጣናትንና የጦር መሪዎችን ጨምሮ የበታች ወያኔዎችንና ተራ ደጋፊዎችን እንዲሁም ሆድ አምላኩ የሆኑ ነጋዴዎችንና መውዐለ ንዋይ አፍሳሾችን ድርና ማግ አድርጎ በማቆራኘት የሚደረግ ሀገር የማጥፋት የሙስና እንቅስቃሴ ነው።

በሀገራችን ያለው ሀገርን ያራቆተው ሕዝብን እራቁቱን ያስቀረው ሙስና በጥቂት የፋሽስት ወያኔ ቁንጮዎች የሚመራና ከታች ከትናንሽ ንግድና ገንዘብ ምንጮች አካባቢ ጀምሮ እስከ ላይ የሚደርስ ሰንሰለት ነው። ከዚህ በፊት በቀደመው ዘመን የሸዋው ንጉስ ሚኒሊክና የጎጃሙ ንጉስ ተክለ ሃማኖት የሀገሪቱን ዋነኛ የገንዘብ ምንጭ የሆነውን የንግድ መስመር ለመቆጣጠር ሲያደርጉት እንደነበረው ደም ያቃባ ፍልሚያ፤ አሁን በሀገራችን እየተከወነ ያለውን ዐይን ያወጣ ሙስናና  ከፍተኛ የገንዘብ ምንጭ የሆነውን ኤፈርትን ለመቆጣጠር ብዙ ትርምሶችንና መጠፋፋቶችን አይተናል አሁንም እያየን ነው።

ሆኖም ግን ኤፈርት የሕዝባችንና የኢትዮጵያ ታሪክ ጠላት ከሆነው ጠባቡ ወያኔ ስብሃት ነጋ ወደ ሙስናዋ እናት የፋሽስት መለስ ባለቤት አዜብ ጎላ፤ አሁን ደግሞ እንደገና ተመልሶ በተዘዋዋሪ ወደ ሽማግሌው ስብሃት ነጋ በተዟዟረባቸው ያለፉት የወያኔ የአገዛዝ ዓመታት፤ ብዙ ሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎችን ቢፈጽምም ባለቆቹ ጥበቃ ማንም ሳይነካው እስካሁን የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ተቆጣጥሮ ቀጥሏል። በምናውቃቸው የማሕበረሰብ ልማዳዊ የአኗናር ዘይቤዎችም ሆነ ሃይማኖታዊ አስተምሮቶች ተመሳሳይ ድርጊት ወይም ሙስና የፈጸሙ ሲደርስባቸውና እየደረሰባቸው ካለው ቅጣት በተለየ የኤፈርት ሀገር ገዳይ የሙስና እንቅስቃሴ እውቅና አግኝቶ ጥበቃ እየተደረገለት ይገኛል። ይህም የሆነበት ምክንያት ሁሉም የወያኔ ባለስልጣናት ለማለት በሚያስደፍር መልኩ በዚህ ሙስና ድር የተጠለፉና ከሚገኘውም ዝርፊያ ተቋዳሽ በመሆናቸው ነው።

በዚህም የተነሳ ለይስሙላም ቢሆን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲል ፋሽስት ወያኔ የጀመረው ሙሰኞችን እያጋለጥኩ ነው የሚለው ዘመቻ ጥቂት የበታች ሙሰኞችን ተጠያቂ ያደረገ ቢሆንም፤ ላለፉት የፋሽስት ወያኔ የአገዛዝ ዓመታት ሲጠላለፍና ሲወሳሰብ በነበረው የሙስና ሰንሰለት የተነሳ የትኛውንም የሙስና ሰንሰለት አካል መንካት ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሶ ስለነበር፤ ያሁኑ የይስሙላ እርምጃ እንኳ ”የገደለው ባልሽ የሞተው ወንድምሽ ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ” ይሉት አይነት ሆኖበታል ለወያኔ። በዚህ የተነሳም የሙስናዋ እናት አዜብ ጎላና ተንኮለኛው የኢትዮጵያ ጠላት ስብሃት ነጋ እንዲሁም ተባባሪዎቻቸው እያደርጉት ያለው ትርምስ የግል ቂም መወጫ እንጅ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምንም የሚያመጣው ፋይዳ የለውም።

ኤፈርትና በስሩ የተኮለኮሉት ወያኔዎች ያለቁም ሆነ ጥሬ እቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባቱ ሂደት ሀገራችን ታገኝ የነበረውን ቀረጥ በማስቀረትና ሌሎች ተወዳዳሪ ሀቀኛ ነጋዴዎችን ከሕጋዊ የንግድ ሂደት ውጭ ከንግድ ስራቸው በማስወገድ ከፍተኛ ወንጀል ፈጽመዋል። ጊዜያቸው ያለፈባቸውና ላገልግሎት ብቁ ያልሆኑ የግንባታ እቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባትና ጥቅም ላይ በማዋል ለብዙ ሕንጻዎች፣ መንገዶች፣ ድልድዮችና ግድቦች ጥራት መጓደልና ያለጊዜያቸው የማርጀት ችግር ተጠያቂዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃብት የነበሩ ድርጅቶችንና የአገልግሎት ተቋማትን ወደ ግል ይዞታ በማስተላለፉ ሂደት ለፖለቲካ መስመርተኛና ደጋፊ ማስረከብን ጨምሮ ሲደረግ በነበረው የተዛባና አድሏዊ የዋጋ ቅነሳ ሙስና የመጀመሪያ ተጠያቂዎች ናቸው።

ምንም እንኳ አሁን ባለው የእከክልኝ ልከክልህ ጥቅም ተጋሪነት በተፈጠረ መተባበርና መተጋገዝ ዋና ዋናዎቹ የኤፈርት አንቀሳቃሽ ሙሰኛ የወያኔ ቁንጮዎችና ባጠቃላይ የሚበዛው ሙሰኛ ያልተነካ ቢሆንም፤ በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች የሚገኙ ምርጥ ምርጥ ቦታዎችን ለድርጅቶችና ለባለሃብቶች በማስረከቡ ሂደት በነበረው ከፍተኛ የሙስና ወንጀል ግንባር ቀደም ተጠያቂዎች መሆናቸውንና ወደ ፊት ለሀገርና ለሕዝብ የሚቆም መንግስት ሲመጣ ለፍርድ የሚጠሩ ስለመሆናቸው ምንም ጥርጥር የለኝም። አሁን ፋሽስት ወያኔ እያካሄድኩት ነው የሚለውን ሀገር አቀፍ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት፤ ይህን ተከትሎም እጅግ በጣም ሰፋፊ የእርሻ ቦታዎችን ለባለሃብቶች በማስረከቡ ሂደት በነበረው ሀገር የመሸጥ ሙስና ተጠያቂዮች እንደሚሆኑ ጥርጥር የለኝም።  ለሀገራችን እጅግ ትልልቅ የሆኑ የግንባታ ጨረታዎችን ላሸናፊዎች በማስረከቡ ሂደትና በዚሁ ሳቢያ ከቀረጥ ነጻ እድል እየተባሉ ከሚገቡ ብዙ ተያያዥ ግብአቶች ጋር በተያያዘ ለተሰሩ ከፍተኛ የሙስና ወንጀሎች ተጠያቂዎች እንደሚሆኑ እርግጠኛ ነኝ።

ይህን ሁሉ እጅግ የገዘፈ የሙስና ወንጀል ለማስፈጸም እንዲረዳ በማሰብ አስፈጻሚ የወያኔ ቢሮዎችን በዘመድ ወይም በጥቅም ተጋሪ ወያኔ በማስያዝ በተደረገው የስልጣን እደላ፤ ሙስና የፈጸሙ የወያኔ ቁንጮዎች፣  የኤፈርት ዘዋሪ ሙሰኞችም ሆኑ ተባባሪዎቻቸው ነገ በፍትህ ፊት ፍርድ እንደሚያገኙ በእርግጠኝነት ባለሙሉ ተስፋ ነኝ። እኛ ስለ ወገኖቻችን እየታገልን ነው የምንል ኢትዮጵያዊያን ግን ሕዝባችንን ለርሃብ ለእንግልትና ለስደት፣ ሀገራችንን ለውርደት የዳረጉ ወያኔዎች እየሰሩት ያለውን ሁሉ እየተከታተልን መመዝገብና ማጋለጥ ይጠበቅብናል።

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on September 28, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , , , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: