RSS

እኛ እንድንሰለፍ ካልተፈቀደልን እናንተ በጠራችሁት ሰልፍ ላይ እየተገኘን እንቃወማችሗለን

07 Sep

ይኸነው አንተሁነኝ

መስከረም 7 2013

ታላላቅ ሰልፎችን መጥራት ብቻውን ግብ እንዳልሆነ ማወቅ ብቻም ሳይሆን ሌሎች የጠሩትን ሰልፍ ገልብጦ ለራስ ዓላማ ማራመጃነት መጠቀም እንደሚቻልም ጭምር ተማርን። እኔ በጠራሁት ሰልፍ ላይ ብዙ ሰው አይገኝልኝም ብሎ የሰጋው ፋሽስት ወያኔ በተመሳሳይ ቀንና በተመሳሳይ ቦታ ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ሕገ ወጥ ብሎ ፈረጀ። በዚህም አላቆመም አመራሩንና ጥቂት ደጋፊዎችን አፍኖ በማጋዝና በመደብደብ እንዲሁም ለሰልፉ አስፈላጊ የነበሩ መሳሪያዎችን በመዝረፍና የሰማየዊ ፓርቲን ቢሮ በመቆጣጠር ሁኔታዎችን ለሱ በሚመች መልኩ ለመለወጥ ቢጥርም የሰልፉን ድባብ ግን ፋሽስት ወያኔ እንዳሰበው ከተቃዋሚነት ወደ ደጋፊነት ሳይመልሰው ቀረ።

ከዚህ በፊት በተለያዩ ጊዜያት የተካሄዱትን የታላቁ ሩጫ ዝግጅቶች ሁሉንም ለማለት በሚቻል መልኩ የህዝብን ብሶት ማንጸባረቂዎች ሲያደርጋቸው እንደነበረው ሁሉ፤ መገናኘትን መሰባሰብንና መወያየትን ወያኔን ለመቃወም እንደአጋጣሚ ሲጠቀም የኖረው የአዲስ አበባ ሕዝብ እሁድ ዕለት በተካሄደው ሰልፍም ያንኑ በመድገም ተሳክቶለታል።

እኔ ሁሌም የሚደንቀኝ ነገር ቢኖር በተቃዋሚ ፓረቲዎች ለሚጠሩት ሰላማዊ ሰልፎች ጥበቃ ለማድረግ አሻፈረኝ የሚለው ፋሽስት ወያኔ ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎችን ለመጨፍለቅ ሲሆን ግን ከልክ በላይ የሆነ አጋዚ ጦር ማሰለፉ ነው። ነው ወይስ ሰልፍን ለመጠበቅና ለመጨፍለቅ የሚሰማራው የአጋዚ ጦር የተለያየ ስልጠና ያለው ነው። እኛን እስከደገፍክና ለኛ እስከተሰለፍክ ድረስ አንድ እርምጃ ወደ ፊት ተራምደን እንጠብቃለን ከተቃወምከን ግን እግርህን እንቆርጣለን አይነቱ የፋሽስት ወያኔ አካሄድስ እስከምን ድረስ ያዛልቃል? ለመሆኑ ሰላማዊ ሰልፈኞችን ወይም የዴሞክራሲ ሃይሎችን በማገትና በማሳደድ፣ በመግረፍና በመግደልስ ነጻነት የጠማውን ሕዝብ ካሰበው የነፃነት መንገድ ማቆም ይችላል እንዴ? ነፃነትኮ ተለዋጭ ወይም ተመሳሳይ የለውም። ከዚህ በፊት ባንድ ወቅት በዚሁ የግንቦት 7 ራዲዮ የቀረበች አንድ ግጥም ትዝ አለች የግጥሟ ርእስ ነፃነቱ ብቻ ትላለች፦

ነፃነቱ ብቻ

                                       የነፃነት ጥሙ ቅጥል እርር አርጎት

የፍትህ ፍላጎት እርቦት ሆድ አስብሶት

ከፍ ዝቅ መደረግ ኮስኩሶት ጎርብጦት

መናቅ መጎሳቆል ቆርጦት አንገብግቦት

ከባድማ ቅየው መገፋቱ መሮት

ከስራ ከንግዱ መፈናቀል አሞት

ባገሩ በወንዙ ባይተዋር የሆነን የተገፋን ዜጋ

ከእንግዲህስ በቃኝ  ሁሉም መረን ወጣ በቃ ብሎ ከተንጋጋ

ያው ነፃነቱ እንጅ ማን ይመልሰዋል ማንስ ያቆመዋል ይህንን ፍለጋ

እውነት ነው ነፃነት የፈለገ ሕዝብ እያደረገ ካለው እንቅስቃሴ ሊገታ የሚችለው ሆዱን ስለሞሉለት ሳይሆን የተመኘውን ነጻነት ሲያስረክቡት ነው። በተዛነፈና ባልተማከለ ልማት ተብየ ልማት ሲደልሉት ሳይሆን እንዲሰራና እንዲንቀሳቀስ ነፃ አድርገው ሲለቁት ነው። ካንተ ይልቅ እኛ የሚያስፈልግህን ቀድመንና በትክክል እናውቅልሃለን ሲሉት ሳይሆን የመናገር የመጻፍና እንደፈለገ የጠመጠየቅ ተፈጥሯዊ ነፃነቱን ሲመልሱለት ነው። እኔን ደግፈህ ሰልፍ ውጣ የእተባለ እንደሚገደደው ሁሉ ራሱ ለራሱ በፈለገው ጉዳይ ላይ ፋሽስት ወያኔን በመቃወም ሰልፍ ሲወጣ መብቱ ተከብሮ ያለ ምንም ችግር ሰልፉን አጠናቆ መመለስ ሲችል ነው። ፋሽስት ወያኔ ግን ይህንን የህዝብ ፍላጎት ሊጠብቅ አልቻለም። ምክንያቱም የህዝብን መብት የማክበር አቅምም ሆነ ዴሞክራሲን የማስፈን ባህልም ሆነ ችሎታ የለውምና ነው።

በመጀመሪያዎቹ የወያኔ የአገዛዝ አመታት ወቅት ጠንካራ ተቃዋሚ እንደሌለና ለሀገር የሚያስብ ብቸኛውና ሃያሉ ፓርቲ ወያኔ እንደነበር ሲለፈፍ ከረመ። በሗላ ግን ምድርን ያነቀጠቀጠ፣ ፋሽስት ወያኔን ያርበተበተ፣ ዓለምን ያስደመመው ቅንጅት ሲመጣ ደግሞ በምን አይነት አኳሗን ከጫወታ ውጭ እንዳደረጉት ሁላችንም የምናስታውሰው ነው። አሁን በቅርቦቹ ዓመታትም በድጋሚ እኛ ብቸኛ ነን፣ ጠንካሮች ነን መባል ተጀምሮ ነበር። ይኸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ፋሽስት ወያኔ የሚፈጽምባቸውን አፈና ተቋቁመውና የተዘጋውን በር በርግደው ሲወጡ ደግሞ  የለመደውን አፈናና ጭፍለቃ ያለምንም ፍርሃት በፊት ለፊት እንደገና ደገመው።

ፋሽስት ወያኔ ጠንካራ ተቃዋሚ የለም ካለ ለምንድን ነው በተቃዋሚዎች የሚዘጋጁ ሰልፎችን የሚፈራውና የሚጨፈልቀው? ለሰልፍ የሚወጣውን ሕዝብ ይፈራል እንዳንል 99.6 በመቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ የመረጠኝ፣ የተማመነብኝ፣ ልማታዊ ያለኝ፣ ዴሞክራሲያዊ ያለኝ ወዘተ ወዘተ ይቀባጥራል። ከሗላ ያለው ያፈጠጠው እውነት ግን ፋሽስት ወያኔ ተቃዋሚዎችን ደብን አርጎ ይፈራል ምክንያቱም ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ከተቃዋሚዎች ጋር ነውና ያለው።  ይህን ለማረጋገጥ ማስረጃ ፍለጋ እሩቅ መሄድ ሳያስፈልገን ባለፈው እሁድ ራሱ ወያኔ የጠራውን ሰልፍና ውጤቱን ብቻ መመልከት በቂ ይሆናል። ፋሽስት ወያኔ ባለፈው እሁድ ባዘጋጀው ሰልፍ የንግድ ቦታ ላለማጣት ፣ ከስራ ላለመባረር፣ እንዲሁም የሚያገኙትን እዚህ ግቡ የማይባሉ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን ለማስጠበቅና መጪውን ዘመን ለራስ የተስተካከለ አድርጎ ለማመቻቸት ተገደው ሰልፍ የወጡ ሁሉ በቦታው ግን ፋሽስት ወያኔን አውግዘው መመለሳቸው ገሃድ ሆኗል። ወያኔንም አስደንግጧል። ይህ እንግዲህ የሚያሳየው ፋሽስት ወያኔ መሰረት የሌለው በአየር ላይ የተንሳፈፈ አጥፊና ዘረኛ ቡድን መሆኑን ነው። ኢትዮጵያዊያን ግን ገዥዎች የጠሩትን ሰልፎች ሳይቀር በቦታው ተገኝተው ለተቃውሞ የማዋልን አዲስ ዘዴ ለዓለም በማሳየትም ሊደነቁ ይገባቸዋል።

ለዲሞክራሲ ግንባታ ገና ልጆች ነን እያለ ሕዝብን የሚደልለው ፋሽስት ወያኔ ዛሬም ከስንት የአገዛዝ ዘመን በሗላ እንኳ ሰላማዊ ሰልፎችን በመጨፍለቅ አድሮ ጥጃነቱን በዓለም ፊት አስመስክሯል። ይሁን እንጅ የትላንትናው የኢትዮጵያ ሕዝብና የዛሬው አንድ አይደለም። ፋሽስት ወያኔ ዛሬም ልክ እንደትላንቱ መቀጠል ከማይችልበት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በግልጽ ታይቷል። ስለሆነም ፋሽስት ወያኔ የነጻነት ጥማችንን፣ መብታችንን የማስከበር ጉዟችንን ልክ እንደትላንቱ በማስፈራራት፣ በማፈን፣ በማሰርና በማጋዝ፣ በመግረፍና በመግደል ሊገታው አይችልም። ይህን ነጻነት ፈላጊ ሕዝብ ሊያቆመው የሚችለው አንድና አንድ ነገር ብዙ መስዋትነት የከፈለለትን ነፃነቱን ሲቀዳጅ ብቻ ነው። ስለሆነም የሽ ኪሎ ሜትር ጉዞ በአንድ እርምጃ ይጀመራል ነውና በሁላችንም የተቀናጀ እርምጃ መሰረት አጥቶ እዚህ የደረሰውን ፋሽስት ወያኔ ፈጽሞ ለማስወገድ ትብብራችንን አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል።

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on September 7, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: