RSS

ሕወሃቶች የምትሉት አይሰማም!!! አንሰማምም!!!

16 Jul

 

ከይኸነው አንተሁነኝ

ሐምሌ 16 2013

የሰው ልጅ በዚህ ዓለም ሀ ብሎ እንዴት መኖር እንደጀመረና ማህበራዊ ሂዎቱንም እንዴት ማካሄድ እንደቀጠለ የሚያስረዱ ወጥ የሆኑ የተጻፉ ማረጋገጫዎች ባይኖሩም፤ የሰው ልጅ አጠቃላይ እንቅስቃሴ መጻፍ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ያለውን ብንመለከት እንኳ፤ በተለይ እንደማሕበራዊ ሳይንስ ተመራማሪዎች አባባልና አተናተን ብዙ የሚባሉ ነገሮች አልታጡም።

እንደነዚህ የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪዎች አባባል የሰው ልጅ አብሮ ወይም በጉርብትና በመኖር የሚጋራቸው የኑሮ ዘይቤዎች አሉ። ከራሱ ለሌሎች የሚሰጣቸው እንዳሉ ሁሉ ከሌሎች አጎራባች ሕዝቦችም የሚቀበላቸው ልማዶች አይነትና ብዛትም እንዲሁ በቀላሉ የሚገመቱ አይደሉም። እንደዚህ ባለው የቅብብሎሽ ሂደትም በተወሰነ መልኩ ከሚከሰት የማንነት መደበላለቅ ጀምሮ መቶ በመቶ እራስን እስከ ማጣትና ሌሎችን ሆኖና መስሎ እስከ መቀጠል የሚደርስ ለውጥ ሊከሰት እንደሚችል ሁሉ ልዩነታቸው ይጎላና ምናልባትም ከቀድሞው በዛ ያለ ማንነትን ይዘው ብዙ ሆነው ሊቀጥሉ ይችላሉ። አሁን ያለው የዓለም ማሕበረሰብ እውነታም የዚሁ ነጸብራቅ ነው። ይህ ማለት ግን ቀደም ባለው የዓለም ታሪክ በተጽዕኖ የተፈጠሩ ማንነቶች አልነበሩም ማለት አይደለም። በጊዜው ከነበረው አስተሳሰብ አመለካከትና ጥቅም አኳያ የተቃኙ በጉልበት የተፈጠሩ ማንነቶች እዚህም እዚያም መታየታቸው የዓለም ሃቅ ነበር። እጅግ ቢያንስ ያኔ።  

ተመራማሪዎቹ ስለ እንደዚህ አይነቱ ኩነት ማስረጃቸውን ሲጠቅሱ ባሁኑ ሰአት ያለው የዓለም ሕዝብና እየተከተለው ያለው እጅግ ብዙ የተለያየ የቋንቋ የሃይማኖት የቀለም የአለባበስ የአመጋገብ በጥቅሉ የአኗኗር ማንነት ባንድ ጊዜ የተገኘ እንዳልሆነ ያሰምሩበታል። ዘፈኑ የለቅሶ ስርአቱ ሁሉም ማሕበረሰብ እራሱን የሚገልጽበት መንገድ ሁሉም ማለት በሚቻል መልኩ በተጽእኖ  ወይም በቅብብሎሽ በተራዘመ ዘገምተኛ የለውጥ ሂደት አማካኝነት የተፈጠረና ወደፊትም በዚሁ መልክ እየተለወጠ የሚቀጥል እንደሆነ ይስማሙበታል። በአሁኑ ሰአት ዓለም በደረሰበት የእድገት የትምህርት የአስተሳሰብና የአመለካከት ደረጃ ከፍተኛነትና በተጎናጸፈው የዲሞክረሲ ስርአትና የሰብአዊ መብት ጥበቃ ደረጃ ምክንያት በሂደት  እንጅ  በተጽእኖ የሚከሰቱ የማሕበራዊ ማንነት ለውጦች ልክ እንደ ቀደመው ዘመን እምብዛም የሚጠበቁ አይደሉም።

ሀገራችን ኢትዮጵያም ከዚህ ሀቅ የጸዳች አይደለችም አልነበረችምም። በሕዝባችን ላይም በዓለም ከታየው የማሕበራዊ የለውጥ ሂደት በተለየ መልኩ የተከሰተ ማንነት የለም አልነበረምም። አብሮ በመኖር ማንነታቸውን ያበዙ እንዳሉ ሁሉ የነበራቸው ማንነትም ጠፍቶ ወደ ሌሎች የተቀላቀሉ ጥቂቶች አይደሉም። በተለይም ከሌሎች ሀገሮች ጋር በምንዋሰንባቸው የድንበር አካባቢ እና በሀገር ውስጥም የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩ ሕዝቦችን በሚያዋስኑ አካባቢዎች ይህ ሀቅ የበዛ ነው። ስለዚህም በማንነት መስፋት ወይም መጥፋት በተለይም አሁን በምናውቃት ኢትዮጵያ አብሮ የመኖር ሂደት የሚፈጥረው እንጅ ጉልበት ቦታ የለውም። በሀገራችን የታየውን የማህበረሰብ የአኗኗር ለውጥ እንደ ወያኔ ያሉ ጎጠኛ ጉጅሌዎች ሕዝብን ለመከፋፈልና ለመበታተን ዓላማቸው እየተጠቀሙበት ቢሆንም ሀቁን ግን ሊሸፍኑት አልቻሉም።

ሀቁ ይህ ሆኖ እያለ  ከ1968 ዓ/ም ጀምሮ ቀጣይ የሆነውና አማራውን የማጥፋት የሕወሃት ዋና ዓለማ  እንደፈለጉ መፈንጫቸው በሆነው ትግራይ ኦን ላይን ሰሞኑን ተንጸባርቋል። ትግራይ ኦን ላይን Unfinished Amharization process in Ethiopia and Kemants’ Quest for Dignity and Self-Rule በሚል ርእስ ሰሞኑን ባስነበበን ጎጠኛ መጣጥፍ የዘረኝነት ልክፍቱን በመርጨት አማራው ሕዝብ እያስገደደ ማንነትን እያስካደ ነው በማለት ”ጩኸቴን ቀሙኝ” አይነት እሪታ እያሰማ ይገኛል። በዚህ ድርጊቱም  እንደ መርህ እየተከተለው ያለውን ሕዝብን ከሕዝብ የማጋጨት ድርጊቱን በመቀጠል አማራውን ከቅማንት ሕዝብ ጋር ለማጋጨት ከመሞከሩም በተጨማሪ ወያኔ ሕወሃት ራሱን በራሱ በመቃወም ወያኔ ’የአማራው ክልል’ ብሎ የሚጠራው አካባቢ የወያኔ ቁንጮዎች የተወሰነውን የቅማንት ህዝብ ከአማራው ሕዝብ ጋር ቀላቅለው በመቁጠር ቁጥራቸውን ከፍ አድርገዋል እያሉን ነው ሕወሃቶች በትግራይ ኦን ላይን። ይህም የሚያሳየው በተጠናና በተደራጀ መልኩ በሕጋዊ ሽፋን ሲሰራው የነበረው የአማራውን ቁጥር የማሳነስ እኩይ ስራው  እንደፈለገ በሚያዘው የይስሙላ ፓርላማ ሳይቀር  ሰሞኑን የተጋለጠበትና ዓላማው የተደናቀፈበት ወያኔ ድርጊቱን በሌላ መንገድ እየከወነው መሆኑን ነው።

ሕወሃቶች ”ያቦን መገበሪያ የበላች ፍየል ያስለፈልፋታል” አይነት ሆኖባቸው ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የማይገጣጠሙ ነገሮችን ይለፈልፋሉ እንጅ በእርግጥ ባሁኑ ሰአት ባለው የዓለም ነባራዊ ሁኔታ ባልተለመደ መልኩ ሕዝብን በማስገደድ ማንነትን እያስካደ የራሱንም ቁጥር እያሰፋ ያለው ማነው? ራሳቸው የአማራው ክልል እያሉ የሚጠሩት አካባቢ ገዥዎች የቅማንትን ሕዝብ ጨፍልቀው ከራሳቸው ጋር ለመቁጠር የሚያስችል ጉልበትና ነጻነትስ አላቸው ወይ? አደረጉ ቢባል እንኳ ለጊዮንን በለጊዮን ከሚባል በቀር ጥፋቱ የማን ሊሆን ይችላል? ስለሆነም ሁሉም መልኩን ቀይሮ የተከሰተው አማራውን የማጥፋት ወያኔያዊ እንቅስቃሴ እንጅ መሰረታዊ ሃቅ የለውም።

በሀገራችን መሬት ላይ ያለው የሚያበራው እውነት የሚያረጋግጠው ግን ለሙን የአማራ ክልል መሬት ለዘላለሙ ለትግሬ ለማድረግ የቋመጠው ሕወሃት ቅዠቱን እውን ለማድረግ የተከተለው መንገድ የአላማጣን የኮረምን የራያን ሕዝብ በማስገደድ ትግሬ ማድረግ ነበር። የወልቃይትን የጸገዴን የሁመራን ሕዝቦች ልጃገረዶች ደግሞ በማስገደድ በትግሬ ጎረምሶች እንዲደፈሩ በማድረግና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ሕዝቡ ዘሩን እንዳይተካ በማምከን አካባቢውን ወደ ትግሬ ሕዝብነት የመቀየር ጭካኔ የተሞላበት እንቅስቃሴ ነበር። ”ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል” እንዲሉ ወያኔ ሕወሃት መከራውን እየቆጠረ ያለውን የአማራ ሕዝብ የቅማንትን ሕዝብ በማስገደድ ወደ ራሱ ገለበጠው እያለን ያገኛል።

ወያኔ ሕወሃት ይህን በማድረጉ ”ባንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ” እንደሚባለው የራሱን ሕዝብ ቁጥር ከማብዛቱም በተጨማሪ የአማራውን ሕዝብ ቁጥር ያሳንስበታል። ይህን በመመርኮዝም በየዓመቱ በሚደረገው የበጀት ድልድል ለራሱ ከፍ አድርጎ ሲያስመድብ የአማራውን ክልል በጀት ድልድል በመጉመድ የክልሉን ሕዝብ ያሰቃይበታል።

ስለሆነም በእኛ እድሜ ባሁኑ ሰአት እያየን ያለው ጥርት ያለው እውነት አማሮችን በሃይል ገልብጦ ትግሬ የማድረግ ሂደት እንጅ ሕወሃቶች በትግራይ ኦን ላይን እንዳላዘኑት ቅማንቶችን አማራ የማድረግ ሂደት አይደለም።

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on July 16, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: