RSS

ወያኔን ያሳበደው የሰሞኑ ፖለቲካ

05 Jul

 

ይኸነው አንተሁነኝ

ሐምሌ 5 2013

የሀገራችን የፖለቲካ ኳስ አብዳለች። የምት ጥንካሬዋና ፍጥነቷ ጭምር ጨምሯል። የምታካልለው ቦታና የማሕበራዊ ክፍልም እንዲሁ ስፋትና ጥልቀቱ ጨምሯል። የተጨዋቾች አቅምና ችሎታ፣ ድፍረትና ቁርጠኛነት፣ ዓላማና የዓላማ ጽናትም እንዲሁ ከፍ ብሏል። ይህን ተከትሎም ወያኔም እንዲሁ አብዳለች። ከተቃዋሚው እንቅስቃሴ ጋር በጽኑ የተቆራኘው የወያኔ የልብ ምትም የተቃዋሚው እንውስቃሴ በጨመረ ቁጥር ፍጥነቱን ጨምሯል። የወያኔን የልብ ምት የሚያስጨምሩት ጉዳዮች ስፋትና ጥልቀታቸው፣ ብዛትና አይነታቸው ጨምሯል። እነዚህን ጉደዮች የሚያነሷቸው ሰዎችና እየተነሱ ያሉበት ቦታና አካባቢም በሚገርም ሁኔታ ብዛት አለው። ይህን ሁሉ እየተመለከተች ያለችው ወያኔ ምንም እንኳ ከእሷ የሚጠበቅ ባይሆንም በሆደ ሰፊነት ችግሮችን በማስተናገድ ፋንታ አሉታዊ እርምጃ በመውሰድና የበለጠ አፍራሽ እርምጃ ለመከወን በዝግጅት ላይ እንደሆነች ይሰማል።

ሀገራችንን የለውጥ ማዕበል ሊንጣት ከጫፍ የደረሰ ይመስላል። አስካሁንም ድረስ ሳያባራ የተቃውሞ አካባቢ አድማሱን እያሰፋና ጥያቄዎቹን እየጠናከረ የመጣው የሙስሊም ወገኖቻችን ሰላማዊ እንቅስቃሴ በሀገራችን አራቱም ማእዘናት ተስፋፍቶ ወያኔን አላፈናፍን ብሎ ቀስፎ ይዟታል። ወያኔም ምንም አይነት መለሳለስ አላሳየችም። በሙሉ ኢትዮጵያ በሚገኙ ሙስሊም ወገኖቻችን ላይ አሰቃቂ ግፍ እየፈጸመችባቸው ትገኛለች። ያም ቢሆን ግን የሙስሊሙ እንቅስቀሴ ተጠናክሮ ቀጠለ እንጅ ላፍታ እንኳ አላባራም። ይህም ለወያኔ ከትልቅ ራስ ምታት በላይ እየሆነ እንደመጣ እየታየ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ በሃይል ወያኔን ለመጣል የሚደረገው ትግል አካል የሆኑ የተለያዩ ሃይሎች አቅማቸውን እያጎለበቱ ከመምጣታቸውም በላይ በተለያዩ አካባቢዎች ከወያኔ ጋር በተደረጉ ውጊያዎች የአቅም ፍተሻ ማድረጋቸውና ሕዝባችንንም ወያኔን ለመጣል ለሚደረገው ትግል የተቀላቀሉ ጥሪ ማስተላለፋቸው መሰማቱ ወያኔንን ጭንቅ ውስጥ ከቶታል። በተለይም የግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ሃይል ከተመሰረተ ባጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነትና እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ መሰማቱ ወያኔን ካስጨነቋት ጉዳዮች ወናው ሆኗል።

ሌላው በከፍተኛ ሁኔታ ወያኔን ካስጨነቃትና የፖለቲካውን ኳስ በፍጥነት ካጦዘው ጉዳይ አንዱ የሰማያዊ ፓርቲ እንቅስቃሴ ነው። ወጣቱ ሰማያዊ ፓርቲ ወያኔን ያስደነገጠና ለሌሎችም በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀስን ነው ለሚሉ ፓርቲዎች ፋና ወጊ የሚሆውን ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዱና እጅግ ከፍተኛ ተቀባይነትም ማግኘቱ ወያኔን አንዘፍዝፏታል። ይህ ሁሉ ሲሆን የፖለቲካዋ ኳስ ከወያኔ መንደር ወጥታ ወያኔን በሰላማዊ እና በነፍጥ በሚታገሉ ድርጅቶች መሃል በፍጥነት ስትንከባለል መመልከት ለወያኔ አልተዋጠላትም። ስለሆነም ይህን የተሰናኘ እንቅስቃሴ ለማምከን ሰሞኑን ተንኮል እየሸረበች መሆኑ ይሰማል።

ከሁሉም ባልተናነሰ መልኩ ወያኔን የበጠበጣት ጉዳይ ደግሞ በአንድነት ፓርቲ ቀስቃሽነት ጎንደር ላይ ሊደረግ የታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ ነው። የሰልፍ ጥሪ እንቅስቀሴው እንደ ፌስ ቡክ እና ትዊተር ባሉ ማህበራዊ መገናኛ መዲያዎች የሚሳተፉ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ የጎንደርን አካባቢ ማሕበረሰብ በደስታ እየናጠ መሆኑ ታውቋል። በዚህ የተነሳም በዚህ በኩልም ብልጫ የተወሰደባት ወያኔ ሰልፉን ለማጨናገፍ እንቅስቃሴ መጀመሯ ታውቋል። በዚህ መሰረትም የጎንደር ሕዝብ ለሰልፉ በነቂስ እንዲወጣና ተቃውሞውን እንዲገልጽ ሲቀሰቅሱ የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባላትን የወያኔ ፖሊሶች ይዘው ማሰራቸው ተሰምቷል።

በያቅጣጫው እየተለበለበች ያለችው ወያኔ ”በስንቱ ልቃጠል አለች ጀመና” ን እየተረተች መሆኑ እየተሰማ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ በወያኔው የጸረ ሙስና ኮሞሽን አማካኝነት የተጀመረው ሙሰኞችን የማጋለጡና የማሳሰሩ እንቅስቃሴ በራሱ ወያኔን አጣብቂኝ ውስጥ እንደከተታት ታውቋል። ይህ ሁኔታ በወያኔ ውስጥ ሳይቀር ከፍተኛ ተቃውሞ እያስነሳ መሆኑ ሲታወቅ እንደ የመርዝ ብልቃጡ ስብሃት ነጋ አይነቶች ሁኔታውን አፈንድተው ትልልቆቹ ሙሰኞች አልተነኩም እያሉ መሆኑ ብዙ ታዛቢዎች ሁኔታው በወያኔ መንደር ስላለው ክፍፍል አይነተኛ ጠቋሚ ነው እያሉ ይገኛሉ። በመሆኑም የፖለቲካዋ ኳስ ጭራሹኑ ክያኔ ሰፈር እንዳትጠፋ ሕወሃትን ስጋት ወጥሮ ይዟታል።

የጎጠኛው መለስ ዜናዊ የሙት መንፈስ የሆነው ሃይለማሪያም ደሳለኝ የተቃዋሚዎችን አሰላለፍ በመተቸት የሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫም ወያኔ ሁልጊዜ ቡጢ ከቀመሰች በሗላ የምታሰማው አይነት የተለመደ ጩከት ነበር። ስለሆነም ከጨዋታ ሜዳው የተገፋች የመሰላት ወያኔ ተመልሳ ወደ ጨዋታ ለመመለስ በተለመደው ደካማ ዘዴዋ የሰላማዊ ፓርቲ አባላትን በማሰርና ሌሎችንም ድርጅቶችና ንቅናቄዎች በመውቀስና በመሳደብ ትኩረት ለመሳብ እየጣረች ነው። አይጋ ፎረም እና ትግራይ ኦን ላይን በመሳሰሉት የወያኔ ድረ ገጾችም ላይ ወያኔዎች ከወትሮው በተለየ ሁኔታና በተጠናከረ መልኩ በተቃዋሚዎች ላይ የከፋ ጩኸትና ስም ማጥፋት መጀመራቸው በእርግጥም ወያኔ እያበደች መሆኑን አመላካች ነው።  ከዚህ በተጨማሪም ወያኔ የቅርብ ጊዜ የሀገር ውስጥ ስጋቴ ያለችውን ሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ከግንቦት 7 ለፍትህ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ጋር በማያያዝ ለመክሰስ ዝግጅቷን እያጧጧፈች መሆኑ ታውቋል። ይህ እብደት ካልሆነ ምን ሊሆን ይችላል?

ሌላው ወያኔን ያስደነገጠና የፖለቲካውን ኳስ የሳበደው ጨዋታ ደግሞ በዚሁ ሰሞን የሆነውና የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የተባለው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ተቋም ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ኦባንግ ሜቶ በአሜሪካ ኮንግረስ ፊት ቀርበው ኢትዮጵያ ከመለስ በሗላ በሚል ርእስ የሰጡት ምስክርነትና ያስመዘገቡት ትልቅ ነጥበ ነበር። ይህንን ምስክርነት ተከትሎ ምስክርነቱን የመሩት ኮንግረስ ማን ሚስተር ስሚዝ የኢትዮጵአን ሰብአዊ መብት አያያዝ በተመለከተ ህግ እንዲረቀቅ ለአሜሪካ ምክር ቤት ሕግ አውጭ አካል ጥያቄ ይቀርባል ማለታቸውን ተከትሎ ወያኔም ሆነች ደጋፊዎቿ ጭንቅ ጥብ ውስጥ መግባታቸውና አብደው መክረማቸው ተሰምቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በወያኔ ጀነራሎች መንደር ማውጣት ማውረዱ እንዳለ እንደቀጠለ ሲታወቅ የነበሩት ሲሻሩ የተሻሩት እንደገና ሲመለሱ እየተስተዋለ ነው። ይህን በማድረግም ወያኔ በውስጧ በተፈጠረው ክፍተትና መከፋፈል ምክንያት እየተፈጠሩ ያሉ የውስጥ ቡድኖች የየራሳቸውን ቡድን ለማጠናከር የሚያደርጉት መሳሳብ እንደሆነ ተገምቷል። ወጣም ወረደ ሰሞኑ የፖለቲካው ኳስ በተለይ በተቃዋሚው መካከል እንዳበደ በዚህ የተነሳም ወያኔ ሁሉ ነገር  ከድጡ ወደ ማጡ ሆኖባት አብራ እንዳበደች መክረሟን የወያኔ መንደር ክራሞት ያሳያል።

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on July 5, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: