RSS

“የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ማሸነፉ ጥርጥር የለውም”-ታጋይ ዘመነ ካሴ

16 Feb

የግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል በጀመረው የትጥቅ ትግል በስርአቱ አስከፊነትና በህዝቡ ለውጥ ፈላጊነት ሳቢያ
አሸናፊነቱን ቅንጣት ታህል እንደማይጠራጠር ወጣት ታጋይ ዘመነ ካሴ ገለፀ። ህዝባዊ ሀይሉን ከመሰረቱት
ወጣቶች አንዱ የሆነውና ቀድሞ በአማራ ክልል የወጣቶች ፕሬዘዳንት የነበረው ወጣት ዘመነ ኢትዮጵያ
እንደ አገር ኢትዮጵያውያን እንደ ህዝብ የገባበት የውርደት አዘቅትና ከዚህ አዘቅት መውጣት የሚቻለው
ስርአቱን በትጥቅ ትግል ማስወገድ ሲቻል ብቻ መሆኑን በማመኔ ወደዚህ ትግል ገባሁ ሲል ለምን ወደ
ትጥቅ ትግሉ እንደገባ ለቀረበለት ጥያቄ መልሷል።

ከኢሳት ጋር ባደረግው ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሟና ብሄራዊ ደህንነቷ እንደ ሻይ ቅጠል በሱቅ
ተንጠልጥሎ የተሸጠበት ዘመን ቢኖር ይህ ያለንበት የወያኔ ዘመን ብቻ መሆኑን የተናገረው ወጣት ዘመነ
በተለይ ከወያኔ ጋር በቅርበት መስራቱ ስርአቱን ይበልጥ እንዲረዳው ስለአስቻለውና የስርአቱ በአስቸኳይ
መወገድ አስፈላጊነት ለትግል እንዲሰለፍ ያስገደደው መሆኑን ተናግሯል።

ስለ ህዝባዊው ሀይሉ አላማና ራዕይ ተጠይቆም ሲመልስ፤ ህዝባዊ ሃይሉ በግልጽ አስቀምጧል፣ ትግላችን
በዴሞክራሲያዊ ስርአት የተመረጠ መንግስት ለስልጣን እስከሚበቃበት ጊዜ ድረስ ነው፤ ለዚህም ስርአት
እውን መሆን ሁኔታዎችን ማመቻቸትም ነው አላማችን ሲል በየትኛውም የአስተዳደር እርከን ላይ
ባለስልጣናት በህዝብ ውክልና የሚመረጡበት ዲሞክራሲያዊ ስርአት እስከሚፈጠር ድረስ መሆኑን ጨምሮ
ገልጿል።

ወጣት ዘመነ የብዙዎች ስጋት ስለሆነው አምባገነን አስወግዶ ሌላ አምባገነን የመተካቱን አዙሪትን በተመለከተም ለቀረበለት ጥያቄ ሁሉን ያሳተፈ
በዲሞክራሲያዊ ስርአት በህዝብ የተመረጠ መንግስት ወደ ስልጣን እንዲመጣ እስከ ማመቻቸት እንጂ ለስልጣን የሚደረግ ትግል ያለመሆኑን በአላማችን
ላይ በግልፅ የተቀመጠ መሆኑና የወቅቱ የአለም ፖለቲካ ሁኔታም ለእንዲህ ያለው ሁኔታ አመቺ ያለመሆኑ ማንም ስጋት ሊገባው አይገባም ብሏል።
ጨምሮም እያንዳንዱ ታጋይ ከወዲሁ የፖለቲካ ስልጠና እንዲያገኝና በግለፅ ዉይይቶች ላይ እንዲሳተፍ በማድረግ አስፈላጊውን የፖለቲካ ትጥቅ
በማስታጠቅ እና በማዘጋጀት ላይ ስለሆንን በዚህ በኩል ቅንጣት ታክል ስጋት የሌለኝና ሌላውም ቢሆን የአላማችንን ግልፅነት ተረድቶ ስጋቱን በማስወገድ
ከጎናችን ሊሰለፍ ይገባል በማለት ይመክራል።

በዚሁ ቃለ-ምልልስ ለድል ያበቁናል የሚላቸውን ሁኔታዎች ሲያስረዳ ሀገራችን ላይ ያለውን ችግር በደንብ በተገነዘቡና ወደፊትም ሊፈጠር የሚችለውን
አደጋ በቅጡ የተገነዘቡ የተለያየ የትምህርትና የህይወት ተመክሮ ባላቸው ከሀገር ውስጥና ከመላው አለም በተሰባሰቡ ወጣቶች የተመሰረተ ሀይል በመሆኑና
በተገነዘብነው ችግር ልክ ማስቀመጥ የሚገባንን መፍትሄና አቅጣጫ በውል እየተረዳን ያስቀመጥን በመሆኑ ለድል እንደሚበቁ አረጋግጦ ቀደም ሲል
የትጥቅ ትግሉን ከጀመሩ ሀይሎች ጋር ያላቸውን በጋራ የመስራት ሁኔታም ጨምሮ ገልጿል።
በመጨረሻም የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል በጀመረው ወያኔን በትጥቅ የማስወገድ ትግል እንደሚያሸንፉ ምንም ጥርጥር እንደሌለው በሙሉ ልብና በሙሉ
ስሜት ተናግሯል።

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on February 16, 2013 in AMHARIC, NEWS

 

Tags: , , , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: