RSS

ዳዊት ከበደ ሚሚ ስብሀቱና የዘረ ፖለቲካ

25 Jan

በይመር ይማም ከኒዎርክ

የዳዊት ከበደና ሚሚ ስብሀቱ victimization card ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብዙ አስገራሚ ነገሮች እየሰማን ነው :: እንደአብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ለረጅም ጊዜ ዝምታን ከመረጡ ግለሰቦች ውስጥም አንዱ ነበርኩ ነገር ግን ዝምታቸን እንደአለማወቅና ሞኝነት እየተቆጠረ እየመጣ ስለመሰለኝና እንዲሁም ማፈርን የማያቁት ዘረጆች ይባስ በለውም እንደተበዳይ እየመሰሉ ሌላውን ሲሳደቡና ሲዘልፉ በመመልከቴ የበኩሌን ለማለት ወደድኩ ::ሰሞኑን እውነትን ለምን
ለህዝብ ተናገራቹ በሚል ምክንያት ከሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ጀምሮ እስክ ዩንቨርስቲ ምሁራን ድረስ በአገር ውስጥ ና ውጪ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ መጀመሩን ካስተዋልኩ ቆየሁ ::ነገሩ አዲስ ባይሆንም ጉዳዩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገር ውስጥ በነሚሚ ስብሀቱ እንዲሁሉም በውጭ ሀገር ደግሞ በዳዊት ከበደ የተጀመረው ዘመቻ አጋጣሚ ሳይሆን ሆን ተብሎ የሚደረግ መሆኑን ማንም ሊስተው ሚችል አይመስለኝም ::

አቶ ዳዊት ከበደ በቅርቡ የሰጠውን ቃለ መጠይቅ በመገርም በመናደድ በማዘንና ግራ በመጋባት መንፈስ ነበር የሰማሁት:: የዳዊት መልስና እንዲሁም የሱን ምላሽ ተከትሎ ከቤቱ የተሰጡት አስተሳየየቶች ያዘሉት እንድምታ በጣም አሳዛኝ ሆኖ አግኝቼዋለሁ :: የዳዊት አስተያየት በአጭሩ ኢትዮጵያውያን እያሰቃየ ያለውን መንግስት በመረጃ የሚያጋልጡም ሆኑ እውነቱን ሚናገሩ ግለሰቦች ፖለቲከኞች ሚዲያዎች ድህረ ገጾች በሙሉ የትግራይ ህዝብ ጠላቶች ናቸው
የሚል አይነት ነው ::

ዳዊት ከበደ ና ሚሚ ስብሀቱ በአገር ውስጥና ውጪ አገር በሚዲያዎቻቸው አማካኝነት ሊያስተላልፉ የፈለጉት መልእክት ተመሳሳይ ነው :: የትግራይን ህዝብ ተበዳይ አድርጎ በማሳየት የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ የሚፈጽመውን ወንጀል ለመሸፈን ና ይህንን ስርአት የሚያጋልጡ ወገኖችን ዝም ለማሰኘትና ሆን ተብሎ ስም በመለጠፍ አንገት ለማስደፋት የሚድረግ ዘመቻ ነው ::ፈረንጆች Blaming the victim ይሉታል:: የአማርኛ ተቀራራቢ ቃሉን ለማቅረብ ባለመቻሌ ይቅርታ እይጠይቃለሁ ::ይህንን Blaming the victim የሚለውን ቃለ ትንተና ለመጀመሪያ ጊዘ በሰፊው የተጠቀመበትና ያስተማረው ዊሊያም ራይን ይባላል:: Blaming the victim በሚለው መጸሀፉ ላይ “ victim blaming is a a way to preserve the
interest of the privileged group in power” ግፍ ፈጻሚዎች ጥቅማቸውን ለማስጠበቅና ለሚፈጽሙት በደል ላለመጠየቅ ተጠቂውን ሀጥያተኛ በማድረግና ለምን ጥቃቱ እንደሚገባው ትንተና ይጀምራሉ ::ይህም ሲደጋገም በሂደት ተጠቂዎችን ማህበርሰቡ እንደጥፋተኛ ማየት ይጀምራል ::ግፉን የሚያድረሱት ግለሰቦችም ይሁኑ ድርጅቶች መሀበረሰቡ ውስጥ ይህንን ትንተና በሚዲያን በሌሎች መንገዶች በማስረጽ በማበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ይሆናል በዚህም ከማንኛውም ሞራላዊም ሆነ ህጋዊ ተጠያቂነት ያመልጣሉ ::

ሴት ልጅ ስትደፈር መደፈርዋ ትክክል አይደለም ከማለትና ወንጀለኛውን በፍርድ ከማስቀጣት ይልቅ ::እሱዋ አጭር ቀሚስ ባታረግ ኖሮ በማታ ባትወጣ ኖሮ ከሱ ጋር ባታወራ ኖሮ ይህንን አትሆንም የሚል እሱዋን ተጠያቂ የሚያደርግ መሀበርሰብ ይፈጠራል ::በዚህም ደፋሪው ሌላዋን ለመድፈር ብርታትና ጥንካሬ ያገኛል::ይህም ሌሎች ሴቶች በማታ ካልወጡ ,አጭረ ቀሚስ ካላደረጉ እንደማይደፈሩ እንዲሰማቸው (false security ) ይፈጥራል:: ጠቂዎቹም በሂደት ለጥቃቱ ምክንያት እራሳቸው መሆናቸውን እያመኑ ይሄዳሉ::አጭር ቀሚስ ካላደረጉ ለጥቃት እንደማይጋለጡ ማመን ይጀመራሉ :: ይህ ከተሰራው ስህተት ይልቅ ተጠቂዎችን ወንጀለኛ የማድረግ ሂደት ችግሩን እያስፋፋው ከመሄድ በስተቀር አንዳች መፍትሄ አያመጣም ::ስህትን ማንም ይስራው ማንም ስህተት ነው ከማለት ይልቅና ስህተንን ከሞራላዊ , ከህጋዊም ሆነ ማህብረሰባዊ የህይወት ህግጋቶች አንጻር መፍትሄ ካልፈለግን ስህተቱ justify እየተደረገ ብዙ ተጠቂዎችን በሂደት ይፈጥራል ማለት ነው ::

በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ዘረኛው መንግስት ባስከተለው ቀውስ ወገኖቻችን እየተገደሉ እየታሰሩ እየተበድሉና እየተፈናቀሉ ባለበትና የእምነት መብታቸው ተከልክሎ የክርስትናውም የእስልምናውም ተከታይ ግራ እንዲጋባና መሄጃ እንዲያጣ የተደረገው በትትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር
እንደሆነ አገር የሚያቀው ሀቅ ሆኖ ሳለ ግፍ ፈጻሚውን ማን እንድንል ነው ሚፈለገው ? ናይጄሪያኖች ናቸው እንበል ወይስ ሞንጎሎች ? ስርአቱ ለራሱ በመረጠው ስም መጥራት ከጥላቻ ና ከዘር ማጥፋት ጋር ምን አገናኘው??? ህወሀት ከ 21 አመት መንግስት መሆን በሃላ እንኩዋን ሊቀይረው ያልፈለገውን ስም እኛ ምን ብለን እንድንጠራ ነው ሚፈለገው ::

ህዝቡ በደል ሲደርስበት ተበደልኩ ሲልና ሲጮህ ተበደልኩ ማለቱ እንደጥላቻ ወንጀለኛና እልቂት እንደሚያመጣ በማድረግ በውጪም ሆነ በአገር ውስጥ ሚነዛው ዘመቻ የአንድን ብሄር የበላይነትና ጥቅምን ለማቀጠል የሚደረግ ዘመቻ አካል ነው ::ከማህበረሰባችን ውስጥ የዚህን ነገር ተገቢ አለመሆንና አደጋ እንደሚያመጣ እንደአብዛኛው ኢትዮጵያዊ በቤት ውስጥ ሳይሆን በአደባባይ ስጋታቸውን የገለጹ ግለሰቦችን የፖለቲካ ድርጅቶችም ይሁን ጋዜጠኞችን
የዘር ጥላቻ አራማጆች በማለት በማሽማቀቅና በማዋረድ ዝም ለማሰኘት የሚደረገው ጥረት አይጠቅምም ባይ ነኝ::እነዚህ ሰዎች በአደባባይ ወጥተው እውነቱን በመናገራቸው ሊመሰገኑ ሲገባቸው ነገር ግን የስርአቱ አቀንቃኞች እውነቱ ለምን ወጣ በሚል ይመስላል እራሳቸውን victim በማድረግ ዘመቻቸውን ከጀመሩ ውለው አድረዋል::

ዳዊት ከበደ የዚህ ዘመቻ አካል ነው ::ዳዊት ethiomedia ድህረ ገጽ ላይ ስሙ ስለተነሳ ብቻ የዚሁ ስርአት አቀንቃኝ የሆነው ብርሀኑ ዳምጤ ጋር ሄዶ ተቃዋሚዎችን ሚዲዎችን ግለሰቦችን በአጠቃላይ ዲስያፖራውን ሲያዋራድ ነገር ግን በአንጻሩ ሌሎች የትግራይ ተወላጅ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን በሚያራምዱት አስተሳሰብ ብቻ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲገደሉ ቤታቸው ሲወረስ አገር ጠለው ሲጠፉ በደሉ የደረሰባቸው ከትግራይ ባለመሆናቸና አማራ ወይም ኦሮም ወይም ደቡብ በመሆናቸው ቢያስቡ ሀጢያቱ ምንድነው? እስከአሁን በሽብርተኝነት ሲከሰስ ያየነው ሌላው ኢትዮጵያዊ ማለትም አማራው ኦሮሞው ወይም ደቡቡ እንጂ አንድም የትግራይ ተውላጅ አላየንም :: የህዝቡን በደል ችላ ብለን ስለፎቅ ባለማውራታቸን የትግራይ ህዝብ ጠላት እንዴት ሊያስብለን ይችላል ? ዳዊት በዚህ ብቻ ሳያበቃ እራሱን በማግዘፍ ሌሎች አገር ጥለው ሲሰደዱ ነገር ግን እሱ ጋዜጣ ከፍቶ ሲሰራ እንደነበር በኩራት ሲግልጽ ነበር :: ከምርጫ 97 በሃላ ከታሰሩት ጋዘጠኞች ውስጥ እንዲሰራ የተፈቀደለት እሱ ብቻ ነበር :: ነገር ግን እነ እስክንድር ,ሲሳይ አጌና ,እና ሌሎችም ብዛት ያላቸው
ጋዜጠኞች በሙያቸው ቀርቶ በየትኛውም የግል ድርጅትም ሆነ የመንግስት መስሪያ እንዳይሰሩ ተደርገው ከነቤተሰባቸው ለችግርና ለመከራ ሲጋለጡ በአንጻሩ ዳዊት የመስራት መብቱ ተከብሮ አለም አቀፍ ሽልማት ለማግኘት ሁሉ በቅትዋል ::ጥያቄው ሚሆነው በምን መለኪያ ላሱ ተፈቀደለት ? በዘር ካልሆነ? መልሱን ይሰጠኛል ብዬ እገምታለሁ ::

እነበቀለ ገርባ ብዙ አመት እስር ሲፈረድባቸውና ያም ሳያንስ ባለቤታቸው ከስራ እንድትባረር ተደርጎ ልጆቻቸው መንገድ ላይ እንዲወድቁ የተደረጉት ኦሮሞ ስለሆኑ አይደልምን ? የእስክንድር ባለቤት አንዴ ባወጣችው ጽሁፍ ላይ ዝርዝሩን መግለጽ ባትፈልግም እስክንድር የብሄሩ ስም እየተጠራ ሲሰደብ እንደነበር ግልጻለች::ጄኔራል አሳምነውም እንዲሁ ተፈጽሞባቸዋል :: ህሊና ያለው ማንኛው ሰብአዊ ፍጥሩ ይህንን በህዝብ ላይ ሚፈጽምን የለየለትና አይን ያወጣ ዘረኝነትና ወንጀልን ይቃወማል እንጂ ይህንን አይን ያወጣ ግፍ በአቅማቸው ሚታገሉትን ግለሰቦች ከ 2 ሰአት ላለነሰ ጊዘ መዝለፍ ህሊና ቢስነትና ዘረኝነት እንጂ ሌላ ምን ሊባል ይችላል ::

ዳዊት በዚህ ቃለመጠይቅ ላይ አንተ አንድም ቦታ የህውሀትን ዘረኛ መንግስት አምርረህ ስትናገር አልተሰማም:: ሌላው ቢቀር እንክዋን በራስህ በባለቤትነት ስትመራው በነበረው አውራምባ ጋዜጣ ላይ አብሮ ሲሰራ የነበረውና በ ትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት ሽብርተኛ ተብሎ ውብሸት ታዬን እንከዋን አላነሳህም::ውብሸት የልጅ አባትና ኦሮሞ ነው ::ዛሬ ያለምንም ማስረጃ ጨለማ ቤት ውስጥ ተዘግቶበት ይሰቃያል:: አንተ ወደ አሜሪካ ስትገባ እሱ ግን እስር ቤት ገባ ?? ያም ሳያንስ ትግሬ በምሆንህ እንደምትግለል ለመግለጽ ሞክርሀል::አስቂኝ ነው::ወትሮም ጉዳይህ የህዝብ ሳይሆን እራስህና እራስህን የተመለከተ ነው ::ስምህመነሳቱ በትግሬቴ ነው አልክ ::ሌላውም ሚሞተው ና ሚሰቃየው ደግሞ ትግሬ ባለሆኑ ብለን ብናስብ ዘረኛ ና እልቂት አምጪ ሊያስብለን ይችላልን ?

አንድ ወቅት ላይ ስትናገር ወደ አሜሪካ የተሰደድከው ሊይዙህ እንደሆኑ የውስጥ መረጃ ስለደረሰህ ነበር እ አንተ የውስጥ መረጃ እንዲደርስህ እንዴት ሆነ ?? በትግሬነትህ አይደለምን? ወይስ ሌላ ምክንያት አለ ? ተስፋ አደርጋለሁ ለዚህ መልስ እነምትሰጠኝ

በዚህ ቃለ መጠይቅ ላይ ደጋግመህ ዲያስፖራውን ዘረኛ እንደሆን ገልጽሀል ነገር ግን ይህንን የጻፈብህ ኢትዮሚዲያ የትግራይ ተወላጅ እንደሆነ ግልጽ ስለሆነ :: አንተ ለምትለው በትግሬነት ተጽእኖ ዸረሰብኝ ድርሰትና ትረካ ሚመች ባለመሆኑ የግድ አብርሀን አማራ ማድረግ ነበረብህ ::አብረሀ አማራ ነኝ
ብልዋል ብለህ የለየለት የዘር ካርድህን ተጫወትክ ::ከዚህ በላይ ዘረኝነት ምን አለ ??? ከዚህ በላይ ህውሀትነት ምን አለ?እንደአስፈላጊነቱ የሰዎችን ማንነት መለዋወጥ ወይንም መስጠት ህውሀታዊ አካሄድ ነው :: ያንተስከዚህ ስትራቴጂ ከዚህ በምን ይለያል ?

በ 1967 ህወሀት ትግል ሲጀምር ከነበሩት ምክንያቶቹ ውስጥ አንዱ በትግሬነታቸን እንጠላለን እንገለላን ከሚል የመነጨ ነበር :በዚህም የብዙ ሺህ ሰው ህይወት በከንቱ እንዲያልፍ ሆነ :: ከመነሻውም አማራ ሚባል ብሄርን ጠላት በማድረግ ና የራስን ብሄር ተጠቂ በማድረግ የጀመረ ትግል ስለነበረ በኢትዮጵያ ውስጥ የተሻለ ስርአት ሊያመጣ አልቻለም ::ያንተም አዲሱ ዘመቻ እንድምታም አሁንም ትግሬ ከሆናቹ አትወደዱም ትገለላላቹ ስለዚህ ስልጣኑን አትልቀቁ ::የትግራይን የበላይነት ለማስጠበቅ ብትገድሉም ብታስሩም ተገቢ ነው :: እኔ ተቃዋሚ ሆኔ እንዲህ ካደረጉኝ እናንተንማ ይጨርሱዋችሃል አይነት ይመስላል መልእክቱ ::

ከኢትዮጵያ ለመባረርህ ዋነኛው ምክንያት ዲይሳፖአራው ያሉት ፖለቲከኖች ናቸው ሚልም ነገር አንስተሀል ::አቶ ዳዊት ሲጀመር መባረርን ምን አመጣው ?? በዲያስፖራው ምክንያት ተባረርኩ ብለህ ከምትናገር ለምን በአገሬ ላይ የፈለክቱን ማናገር አልችልም ? ለምን እባረራለሁ ብለህ ብትታገል ኖሮ ለኢትዮጵያ ሚጠቅም ነገር ይመጣ ነበር ::በዚህ ቃለ መጠይቅ ላይ ባንተ የተንጸባረቁት አስተያየቶች አጠቃላይ እንድምታ ለምን ኬክ አይበሉም ዳቦ ከሌለ እንዳለችው ፍረንሳዊት ልእልት አይነት ነው ::እየደጋገምክ ስለሞራሊቲና ነጻ ሚዳዎች ስትናገር ነበር:: ላንተ አይገባህም እንጂ አብዛኛው ኢትዮኦጵያዊ ከፍተኛ መከራ ላይ ነው ያለው ::አንተ ያለህበት ና ሌላው ኢትዮፕያዊ ያለበት ሁኔታ የተለያየ ነው :: በዘረኞች እጁና እግሩ ታስሮ እንዲሰቃይ እንዲሞትና እንዲራብ የተፈረደበት ማህበረሰብ አንተ ስለምትለው ግዳይ በዙም አይገባውም ::በዲያስፖራም ያሉት ፖለቲከኞች የዛ ብሶት ውጤት ናቸው :: አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ሌላው ቢቀር እምነት ቦታዎቹን ተነጥቅዋል:ሴት ልጆቹ ወደ አረብ አግሮች ለ ግርድና እየተሸጡ ነው :: መሬቱ ለቻይና እየተሽጠ ነው :: ልጆቹ
በየኮንቲነሩ ታፍነው እየሞቱ ነው ሌሎቹም በባህር እየሰመጡ ነው ::እኔ ራሴን ሪሌት ማድረርገው ከነዚህ ወገኖች ጋር ነው ::የነሱ ስቃይ ስቃዬ ነው ::ችግራቸው ችግሬ ነው ::ረሀባቸው ረሀቤ ነው :: እርግጥ ነው አንተ የኔ ምትላቸው ህዝቦችን ሌሎች ይሆናሉ ለዚህም ነው የነዚህ ወገኖች ስቃይ ሚናገሩ ግለሰቦች , ድርጅቶች ሚዲያዎች ላይ የዘመትከው :: ሰብአዊነትና የወግንተኝነት ስሜት በውስጥህ ቢኖር ኖሮ ከ 2 ሰአት በላይ ስትናገር ይህንን በጠቀስክ ነበር ::

የኢንተርሀምዌ ሌላው ገጽታ የነሚሚና ዳዊት ዘመቻ የህውሀት አክራሪ የዘር ድርጅት ቅንጅትን ኢንተርሀምወሜ ብሎ የጀመረው ድራማ ሌላው ገጽታ ነው ::ተቃውሞ ና ጥያቄ ሲያይል እኔ እዚህ ብሄር የመጣሁ ስለሆነ የሚለው አመለካከት በራሱ ከትንሽነትና , ለራስ ካለ የበተቻነትና የዝቅተኝነት ስሜት ሚመጣ ነው ::በራሱ ሚተማመን ግለሰብ እኔ እንዲህ ስላሰብኩ ይህ ድረሰብኝ ይላል እንጂ እኔ እኒህ ሰልሆንኩ ብሎ አብረው የሰሩትና የረዱትን ግለሰቦች ለማዋረድ አደባባይ አይወጣም ነበር :: የበታችነት ስሜትት በሽታ ነው ::እነሂትለርም ሆነ መለስ እንዲሁም ሌሎች አንባ ገነኖች ያን ወንጀል ለመፈጸም ያነሳሳቸው ለራሳቸው ካላቸው ትንሽነት ስሜት የሚመነጭ ነው::

በፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች እወነቱን ለማህበረሰቡ ከማሳወቅ መቆጠብ የለባቸውም::እንዲህ እባላለሁ በሚል ስሌት ከ 21 አመት በላይ ወገኖቻችን ሲሰደዱ ሲገደሉና ሲሰቃዩ አየተን እንዳላየን ሆነናል::ነገር ግን ግፉ ሚቆም አልሆነም ::አካፋን አካፋ ብለን ለችግሩ መፍትሄ እስካልፈለገን ድረስ አሁንም በደሉን ስቃዩ ይቀጥላል ::

ወያኔዎች የወገኖቻችን ስቃይ እንዳይታይ በተካተታይ እራሳቸው ተበዳይ በማድረግና ተበዳዮችን በዳይ በማስመሰል የሚጫወቱን ካርድ ነቄ ማለት አለብን ::ከወያኔ ጋር ያለን ልዩነት የዚህ አመት ባጀት ከፍ ይበል ,ዝቅ ይበል የመሳሰሉ የፖሊሲ ችግሮች አይደሉም:ወያኔ ወገኖቻችንን እየገደለ ,እያሰቃየ እያሰረ ና እያፈናቀለ ያለ ስርአት ነው ::ይህንን ስርአት በምንችለው መልኩ እንታገለዋለን :: የውጪ ያሉት ተቃዋሚዎች ድክመት በምንም ሁኔታ የትግራይ ነጻ አውጪን ድርጅትን ግፍና በደል ሊሸፈነው አይችለም ይህንን ዘረኛ ስርአት የጥቂቶችን ጥቅም እያስጠበቀ እንዲቀጥል ለማድረግና ይህንን እውነታ ፊት ለፊት ተጋፍጦ ከማስተካከል ይልቅ ዳዊትን ጨምሮ ሌሎችም ግለሰቦች የዲያስፖራውን ድክመት በማጉላትና በማጋነን የወያኔን ስርአት በደል justify ለማድረግ ይሞክራሉ::ዲያስፖራው ከ አገሩ በበዙ ሺህ ማይል ርቆ ከመገኘቱ አንጻር የራሱ ድክመት አለበት ::ስህተቶች አሉ ይህ ማንም ሚክደው አይደለም ነገር ግን
በየትኛውም መለኪያ ከወያኔ ሀላፊነት ከጎዳለው የዘር ስርአት በህዝብ ላይ እያድረሰ ካለው ግፍ ጋር ሚነጻጸር አይደለም:: እውነታውን መጋፈጥ ከባድ ስለሆነ ዲያስፖራው ላይ መዝመት እንደ ፋሽን ከተወሰደ ሰንብትዋል::ውጤት ግን አላመጣም አያመጣምም ::

ዘረኛው ስርአት እስከሚወገድ ድረስ ትግላችን ይቀጥላል !!!!!

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on January 25, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: