RSS

ቴረሪስቱ ማነው ?

15 Jan

መሰረት ቀለመወረቅ
አውሰትራሊያ

አባቶቻችን ነገርን በምሳሌ ሲያስረዱ “ይች ወፍ ገልብጣ ነፋች ይላሉ ” ምሳሌዊ አነጋገሩን ያለምክንያት አላመጣሁትም። ከአቶ መለስ ሞት ወዲሕ በኢሕአዴግ ስም ወያኔ ያጠለቆው ጭንብል እየወለቀ ሲመጣ ትክክለኛ ማንነቱን ለመደበቅ በማይችልበት መልኩ መከሰቱ ወያኔዊ ተግባሩን ብቻ ሳይሆን በማጭበረበር ተወልዶ በማጭበርበር ያረጀና የበሰበሰ የነፍሰ ገዳዮች ቡድን መሆኑ የተረጋገጠበት ሀቅ በመሆኑ ነው። ባለፉት 21 ዓመታት ውስጥ
በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊያን ላይ ላደረሰው ጠቅላላ ውድመት በአቶ መለስ ዜናዊ የሚመራው ወያኔ የተባለው የሺፍቶች አሸባሪ ቡድን ለመሆኑ የማያወቅ ኢትዮጵያዊ አለ ብየም አልገምትም።ዛሬም የመለስን የጥፋት እራእይ አንግቦ የሚውተረተረው ወያኔ ሐይለማርያም ደሳለኝን እና መሰሎቻቸውን ባሻንገለትንት አስቀምጦ የፖለቲካ ሺምጥ ለመጋለብ ቢሞክርም አሸባሪው ሕወሐት ከቴረሪሰቶች መዝገብ ውስጥ የተመዘገበበትን የታሪክ አጋጣሚ ለመደበቅ ከቶውንም አይችልም። ከሚገርመው ነገር ወያኔ ዛሬ ለነጣነቱ የሚዋጋውን አረበኛ፤የእምነት ነጣነቱን ለማስከበር ሰላም ፍቅረነና አንድነትን በመጠየቅ ላይ የሚገኘውን ክረሰቲያንና ሞሰሊም፤በኢተዮጵያ ውስጥ ሉዓላዊነት የሕግ የበላይነት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እኩልነትና ወንድም አማችነት እንዲሰፍን የጠየቁ ምሁራን፤ ጋዜጠኞች፤ አዛውንት አባቶችና እናቶችን፤ ወጣቶችንና ተማሪወችን በቴረሪስት ቅባት እየቀባ በመግደልና በማሰር ሕዝባችን
ማሸበሩን ከቀጠለበት 21 ዓመታት ተቆጥረዋል። ይች ወፍ ገልብጣ ነፋች ማለት ይኸ ነው። አሸባሪው ንጡሐኑን አሸባሪ የሚልበት አሸባሪው ሕግ አውጭ ሆኖ ሰላማዊ ዜጎችን የሚቀጣበት የተገላበጠ ዘመን።

ነገርን ነገር ያነሳዋልና አለማቀፍ ምሁራን ቴረሪሰት የሚለውን ቃል ትረጉም ሲያስቀምጡ ሰላማዊ ሕዝብን በመኖረያ ስፈሩ በስራገበታው በመዝናኛ ማዘውተሪያው በቤተጰሎት ማድረሻው ባልታሰበና ባልተጠረጠረ ስዓት አሸምቆ የጦር መሳሪያ በማፈንዳትና በመተኮስ ሲቢሊያንን የሚገደል ነው፤በተጨማሪም የሰውልጅ ለእለታዊ ኖሮና ለማሕበራዊ እድገቱ የሚጠቀምባቸውን የቴክኖሎጅ ውጤቶች መዝረፍ ማቃጠልና ማውደም ሌላው ተገባሩ
እንደሆነ ያስረዳሉ።ታዲያ ለቃሉ ከተሰጠው አለም አቀፍ ትርጉም አነጣር በሐገራችን ውስጥ ተግባር የማንነት መግለጫ ነውና አሸባሪው ወያኔ ከዘመነ ሺፍትነቱ አሁን እስካለበት የቤተመንግሰት ስልጣኑ ድረስ የተጉዘባቸውን የታሪክ አጋጣሚወችና የፈጠማቸውን ድርጊቶች ኢትዮጵያዊነትን በተላበሰ ጨዋነትና በቅን ዓዕምሮ ለተመለከተ ሰው ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ቴረሪስቱ ማነው? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ከባድ መስሎ አይታየኝም ወያኔ በዓለም አቀፉ መንግስታት የቴረሪስት ድረጅቶች ምዝገባ ውሰጥ ባሸባሪነት ለመመዝገብ የበቃው ቅድመ ምዝገባ መመዘኛውን በሚገባ አሟልቶ እንጅ እንዲያው ባጋጣሚም አይደለም። ሺብርተኛው ወያኔ በጫካ ዘመኑ በትግራይ፤በጎንደርና በወሎ በአፋር ሕዝባችን ላይ በፈጠማቸው ከፍተኛ ወንጀሎች ምክነያት በአለም አቀፍ ደረጃ ከተመዘገቡት ቴረሪስት ግሩፖች ውስጥ አንዱ ወያኔ መሆኑን እረስቶት ከሆነ ልናስታውሰው ይገባል።

አሸባሪው ወያኔ ገና ከአፈጣጠሩ በደደቢት በኩል ሺፍትነቱን ሲጀምር ትግራይ ውስጥ የገበሬውን ቤት ከነቤተሰቡ ዘግቶ በማቃጠል፤ ወጣቱንና አዛውነቱን በጨለማና በጠራራ ጠሐይ በማፈን እየገደለ ጉልበቱን እንዳሳበጠ የትናት ትዘታችን ነው። በከተሞችም ቢሆን በመቀሌ ከተማ በአውራጃና በወረዳ ከተሞች ዘራፊ ነፍሰገዳይና አፋኝ ስኩዶችን በማሰማራት ይቃወሙኛል የሚላቸውን ንጡሐን ወገኖች ይገድል ያሸብር ስለነበር በሺህ የሚቆጠሩ ህጣናት ያለ አሳዳጊ አባትና እናት መቅረታቸውን እናስታውሳለን። በተመሳሳይ ሁኔታ የግለሰቦችን ሐብት ከመዝረፍ አንስቶ ያልተሰበረ ድልድይ ያልተመዘብረ ባንክ ያልተሰረቀ ሕክምና መስጫ ተቁም ያልተቃጠል ትምሕረትቤት አልነበረም እንዲያውም በወቀቱ ድርቅ ያስከተለውን ሰባዊ ቀውስ ወያኔ ለሺብር ተግባሩ በመጠቀም እራሐብተኛ ወገናችን 20 ሰው በአንድ ጉድጉድ እየቀበረ የመጣላቸውን ነፍስ አድን አለማቀፍ እርዳታ ከአፋቸው እየነጠቀ ሲሸጥ ነበር። ስለዚሕ ጨካኝ ቡድን በዙ የተባለበት ስለሁነ መድገም አያስፈልገኝም።

ነፍሰ በላው ወያኔ የሺብር ድረጊቱን ወደመሐል አገር በማስፋፋት በ 21 ዓመታቱ የግድያና የዝርፊያ የሺበርና የአፈና ግዛቱ በጎንደር በወሎና በአፋር በሐረር በወለጋ በሲደሞ በሸዋ  ገጠሮችና ከተሞች ውስጥ በሰው ሕይወትና በንብረት የፈጠመውን ወንጀል ታሪክና ትውልድ የመዘገበውና ሕዝባችንም በጠጠት የሚያስታውሰው ስለሆነ በዚች አጭር ማስታወሻ መዘርዘር ከቶውንም አይቻልም። ይሁንና በትንሹም ቢሆን ለማስታወስ በአዋሳ በጎንደር በሐረር በደሴ
በደበረማረቆስ በጋንቤላ በአምቦ በአሰላ በደብረብርሓን በባሌ በአዲስአበባና በሌሎቹም ከተሞች እየገደለና ቤትንብረቶን እየዘረፈ የፈጀው ሕዝብ ቁጥር እንዲህ ቀላል እንዳልሆነ ማንም ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን አለም አቀፍ ታዛቢወችም ያረጋገጡት ጉዳይ ነው።በአውቶቢሰ በባቡር በታክሲ በገበያ ቦታና በመሰብሰቢያ አዳራሾች ቦንብ በማፈንዳት የሰላማዊ ሰወችን ህይወት በመቅጠፍ በወጡበት አስቀርቶል። ይቃወሙኛል ያላቸውን ስላመዊ ሰለፈኞች በጠራራ ጠሐይ እረሺኖል። በቀያቸው የሚጫወቱ ሕጣናትን ገድሎል። በገጠሩ ነዋሪ ሕዝባችን ላይም በመኖሪያ መንደሮቹ አልሞ ተኩሾችና ነፍሰ ገዳይ ጉጅሌወችን በማሰማራት ጫካው ወንዙ ሳርቅጠሉ ዋሻው በሬሳ ክምር ተሞልቶ ዘመድ አልቅሶ ሳይቀብረው አሞራ ቁራ የበላውና የዱር አራዊት የተጫወተበት ስንቱን እንደሆነ የሚታወቅ ነው። ወያኔ ባሰማራቸው ጀሮጠቢወች አማካኝነት ሰላማዊው ሕዝባችን በደስታውም ሆነ በመከራው ያካበተውን አብሮ የመኖር አኩሪ ባህል በማፍረስና በማሸማቀቅ የግዞት የሺብር ሕይወት እንዲገፋ ከመገደዱም በላይ በስርቤት የሚማቅቀው በኤሌክትሪክ የተጠበሰው በዱላ የተቀጠቀተውና አካለ ስንኩል የሆነው ቤት ይቁጠረው። እንዲያውም በየትኛውም አለም ታይቶም ተሰምቶም በማየታወቅ ዘግናኝ ሁናታ ባልና ሚስት እራቁታቸውን በሕዝብ ፊት ቆመው ሚስት የባሏን ብልት ባደባባይ እንድትጎትት የተደረገበት አገር ቢኖር የዛሬዋ የወያኔው ኢትዮጵያ ናት። መከራ የወረደበት ሕዝባችን ከእንዲሕ አይነቱ ስቃይ ለመዳን ስደትን እንደአማራጭ ቢጠቀምም በተሰደደባቸው አጎራበች ሐገራት ካሸባሪው ወያኔ ግድያና
እስራት ለመዳን አልቻለም። ወገን ሆይ ታዲያ በዓለማችን ላይ ከዚህ በላይ አሸባሪነትና የሺብር ተግባር ምን አለ ?

የሐገርሕ የወገንሕ መከራ ለሚሰማሕ ወገን ሆይ !!ዛሬ ሁላችንም እንደምነረዳውና ከላይ በግርድፉ ለማመላከት እንደሞከርኩት ኢትዮጵያና ኢተዮጵያውያን በአሸባሪው ወያኔ የሚሰቃዩበትና የሚታመሱበት ወቅት ነው። በአንጣሩ ደግሞ ይሕ የወያኔው የሺብር ድርጊት እንዲቆም የብሶትና የመከራ ድምጥ ገንፍሎ ከየትኛውም የሐገራችን አቀጣጫ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰተጋባ መጥቶል። ጥያቄው አሸባሪው ወያኔ የሚፈጥመውን ወንጀል የቡድኑን መሰረታዊ አፈጣጠርና ባህርይ ለሺብር ተግባሩ የሚጠቀምባቸውን ተቁማት ለይቶ በመረዳት ሕዝባችን ከሺብርተኛው ወያኔ ነጣ በማውጣት ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም በሐገራችን ለመትከል በተቃዋሚነት ጎራ የተሰለፈው ወገን ተመጣጠኝ የትግልና የአሰላለፍ ስልት አውጥቶ የጉዳቱ ሰለባ የሆነውን ሕዝብ ለማስተባበር ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተንቀሳቀሰ ነው ወይ ? የሚለው ጉዳይ በኔ እምነት የወቅቱ ጥያቄ ይመስለኛል። ነገር ግን ከዚህ ላይ መታወቅ ያለበት በተቃዋሚው ጎራ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጠመ ያለውን የሺብር ተግባር በቀጥታ ከሚደግፉትና የወንጀሉ ተባባሪ ከሆኑት ተቃዋሚ መሰል ድርጅቶች ሌላ በወያኔ ተቃዋሚነታችን እንከን አይወጣልንም በሚሉ ተቃዋሚወች በኩል በወያኔ የሚደርሰውን ጥፋት በየጊዜው በአይናቸው እየተመለከቱ በጀሮቸው እየሰሙ እነሱ ራሳቸው የችግሩ ሰለባ ሆነው እያለ ነገር ግን ድፍረቱ ኖሮቸው አሸባሪው ወያኔ የመፈጥመውን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን የማጥፈት እረምጃ ለማስቆም የሚያስችሉትን የትግል እረምጃወች አቁሞችና ክንዋኔወችን በተገባር ለይቶ በማውጣት ከሕዝባቸው ፊትለፈት ቆመው ወቅቱ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት በፖለቲካ ድርጅት ደረጃ ሲከፍሉ አይታዩም እንዲያውም ችግሩ የዲሞክራሲ ጥያቄ ችግሩ የስልጣን ክፍፍል ችግር ችገሩ የወያኔው መንግሰት የስራ አፈጣጠም ችገር ………. ወዘተ እንደሆነ አስመስሎ በማቅረብ ወያኔው ለሚፈጥመው የሺብር ተግባር ሺፋን ሆነው የሚያገለግሉ አሉ። በእርግጥ ከመካከላቸው አንዳንድ ወገኖች የከፈሉትና በመክፈል ላይ ያሉት መሰዋትነት ታረክና ትወልድ የማይረሰው ቢሆንም ትግላቸው ቀጣይነት ባለው መንገድ በድርጅት ደረጃ የተጠናከረ ባለመሆኑ የሕዝባችን የመከራ ዘመን ለማሳጥር አልተቻለም።

ከዚሕ ላይ ብዙ ዙሪያ ገባ ሳንመለከት አሸባሪወች በዓለማችን ላይ የሚያደርሱት ሰባዊና ቁሳዊ ቀውሰ ምን ያህል በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ አስከፊ እንደሆነ የምንረዳው ጎዳይ ነው። ለዚሕም ነው መላው አሜሪካኖች፤ ምዕራባውያን፤ ምስራቃዊያንና ጠቅላላው ዓለምችን አለማቀፍ ሺብርን ለመግታት በመደራደር ሳይሆን ያለየሌላቸውን ወታደርና የጦር መሳሪያቸውን አሰልፈው በቢለዮን የሚቀጠር በጀት መድበው ዓለማቀፍ የመረጃና የዲፕሎመሲ ስራቸውን አጠናክረው መተኪያ የሌለውን የዜጎቻቸውን ሕይወት በመገበር ሺብርተኝነትን እያንበረከኩት ነው ከፍተኛ አለም አቀፍ ውጤትም አግኝተውበታል እኛም በተገኘው አንጣራዊ ሶላም ተጠቃሚወች ነንና ልናመሰግን ይገባል ብየ አምናለሁ። ነገር ግን እኛ አትዮጵያዊያን በሕዝባችንና በሐገራችን ሕልውና ላይ የሚፈጠመውን ሺብር እያየንና እየሰማን የፖለቲካችን ጭብት ወሬ አሳባቂና ቃላት ሰንታቂ ሆነን ጥርስ የሌለው ውሻ በመሆን ከቴረሪስቱ ወያኔ
የጥፋት በትር በማያድን ጉንጭ አልፋ ንትርክ ስንደናበርና ስንላፋ 21 አመታትን አስቆጥረናል። እንዲያውም አሸባሪውን ወያኔ ከማሸበር ተግባሩ ውጫ ያለተፈጥሮው የሌለውን መልክና ቅርጥ እየሰጠን ብሔራዊ እርቅ ድርድር ምርጫ ሰላማዊ ትግል እያልን አሸባሪው ወያኔ በተቆጣጠራት ሐገር የማናገኘውን ስልጣን በመመኘት የሕልም ጉዞ አላሚወች ሆነናል። ይሕ አስተዛዛቢ ሁናታ ከአሁኑ ወቅታዊ ሁኔታ የበለጠ አጋጣሚ ተገኝቶ መቸይሆን የሚታረመው በሚል እንደ ኢትዮጵያዊነቴ ያደረብኝን በርቱ ስጋት በተለይም በውጭ ለሚኖረው ኢተዮጵያዊ ወገኔ ምንም እንኩን አቅሜም ሆነ ችሎታየ ትንሺ ቢሆንም
የተሰማኝን ስሜት በከፍተኛ ሐዘን መግለጥን መርጫለሁ።

ከደስታየ ጥቂቶቹ ደገሞ አርበኞቻችን ወያኔን በሚገባው ቁንቁዋ እያናገሩት መሆኑን በራሱ በወያኔው አንድበት ምሰክርነቱን ወዶ ሳይሆን ተገዶ በመስጠት ላይ እንደሆነ ስረዳ ደግሞ በጀግኖች ወገኖቸ ከፍተኛ ኩራትና ተስፋ ይሰማኛል እንዲያውም ወያኔ በጦር ሚዳው ውሎው በየትኛውም አቅጣጫ እየደረሰበት ያለውን ሺንፈት ጭንቀትና ፍርሐት በወለደው አንደበቱ እያስተጋባ ነው ። ተፋላሚወቸ ብሎ ከሚመስክርላቸው ውስጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ አረበኞች
ግንባር የትግራይ ዲሞከራሲያዊ ንቅናቄን የጋቤላ ነጣነት ንቅናቄ የተባሉ ኢተዮጵያውያን ድርጅቶች ዋናወቹ እንደሆኑ ተናግሮል።

በዚሕ አጋጣሚ ወያኔ ያፈረሳትን ሐገር፤ወያኔ የረገጣትን ሰንደቅ አላማ፤ወያኔ የዘረፈውን የሕዝብ ሐብት፤ ወያኔ የበተነውን ሕዘብ ፤ወያኔ ያረከሰውን እምነቶች፤ወያኔ የበከለውን አኩሪ ባሕል፤ ወያኔ ያነገሰውን ሕግ አልባነት ግድያ አፈና ሺብር ስደትና የግዞት ስርዓት ለማስወገድ መተኪያ የሌላትን ውድ ሕይወታቸውን በመገበር በዚህ ወቅት በየትኛውም የፍልሚያ ጎራ ተሰልፈው የወያኔን እብሪት ለማስተንፈስና ለኢትዮጵያዊያን ነጣነት፤ አንድነት፤ለጋራ እድገት ፤ፍቅርና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ነጣነት ያለመስዋእትነት አይገኝምና የታሪክና የትውልድ አደራቸውን ከሕዝባቸው ጎን ሆነው ግዳጃቸውን በመወጣት ላይ ለሚገኙት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና በቅርቡ ከግንባሩ ጋር ሕብረት በመፍጠር የአሸባሪውን ወያኔውን ጎራ በማንቀጥቀጥ ላይ ለሚገኙት ስድስት ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች ለሚፈጥሙት የላቀ ጀግንነት ምሰጋናየ ይድረሳቸው እላለሁ ይንን የተቀደሰ ሐገርና ሕዝብን የማዳን ተግባር ለዲሰፖራው ወገን እግዚአብሔር ቅን ልቦና ስጥቶት አርበኞቹን እንዲቀላቀል ጥሪየን እያቀረብኩ ፈጣሚው እሱ ነውና ለሐያሉ ጌታም ልመናየን አቀርባለሁ…….//..

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on January 15, 2013 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: