RSS

በኢትዮጵያ በ2003 ዓም ብቻ 100 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ተዘርፎ ወደ ውጭ ባንኮች መግባቱ ታወቀ

13 Dec

ኢሳት ዜና:-ጥናቱን ይፋ ያደረገው አለማቀፍ እውቅና ያለው ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ የተባለው ተቋም ሲሆን በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2010 ወይም በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2003 ዓም ብቻ ከኢትዮጵያ በተለያዩ መንገዶች ተዘርፎ ወደ ውጭ አገር ባንኮች የተላከው ገንዘብ 5 ቢሊዮን 600 ሚሊዮን 400 ሺ ዶላር ወይም በጊዜው በነበረው ምንዛሬ ወደ  100 ቢሊዮን  ብር ነው።

ገንዘቡ የተዘረፈው በአብዛኛው በሙስ እና  በታክስ ማጭበርበር ነው። ገንዘብ በከፍተኛ ደረጃ እየተዘረፈ ወደ ውጭ ባንኮች ከሚላክባቸው አለም አገሮች መካከል ኢትዮጵያ የ15ኛ ደረጃን ይዛለች።  በተጠቀሰው አመት ከቻይና 420 ቢሊዮን፣ ከማሌዢያ 64 ቢሊዮን፣ ከሜክሲኮ51 ቢሊዮን፣ ከሩሲያ 43 ቢሊዮን፣ ከሳውዲ አረቢያ 38 ቢሊዮን፣ ከኢራቅ 22 ቢሊዮን፣ ከናይጀሪያ 19 ቢሊዮን፣ ከኮስታሪካ 17 ቢሊየን፣ ከፊሊፒንስ 16 ቢሊዮን፣ ከታይላንድ 12 ቢሊዮን፣ ከካታር 12 ቢሊየን ፣ ከፖላንድ 10 ቢሊየን፣ ከሱዳን 8 ቢሊየን ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ 7 ቢሊየን እና ከኢትዮጵያ በ ቢሊየን 6 መቶ ሚሊዮን ዶላር ተዘርፏል።

በ2003 ከኢትዮጵያ የተዘረፈው ገንዘብመንግስት በተመሳሳይ አመት ከበጀተው ብሄራዊ በጀት ጋር ተመሳሳይ ነው። አገሪቱ ከውጭ አገር በእርዳታና በብድር ካገኘቸው ገንዘብ ጋር ሲነጻጸር  የተዘረፈው ገንዘብ በ2 ቢሊየን ዶላር ይበልጣል።  ገንዘቡ ተመልሶ ወደ ኢትዮጵያ ካዝና ቢገባ ኖሮ የአባይን ግድብ ያለምንም መዋጮና ቦንድ ግዢ ለማስጨረስ ያሰችላል።

ይህ ተቋም ከአንድ አመት በፊት በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ1993 እስከ 2002 ዓም 8 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ከኢትዮጵያ ተዘርፎ በውጭ ባንኮች መቀመጡን ይፋ አድርጎ ነበር። ባለፉት 10 አመታት ከኢትዮጵያ በአጠቃላይ የተዘረፈው ገንዘብ መጠን ከ13 ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው።

አቶ ኤፍሬም ማደቦ 8 ቢሊየን ዶላር ከኢትዮጵያ ተዘርፎ መውጣቱ ሪፖርት በተደረገበት ወቅት ባወጡት አንድ ጥናታዊ ጽሁፍ ላይ ገንዘቡ 90 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ 18 ዩኒቨርስቲዎች፣ 27 ኮሌጆች፣ 36 ሆስፒታሎች፣ 180 ጤና ኬላዎ፣ 6 የዘይት ፋብሪካዎች፣ 4 ሲሚንቶ ፋብሪካዎች፣ 1 አባይ ግድብ፣ አራት የግብርና ኢንዱስትሪዎች ሊያሰራ እንደሚችል መግለጻቸው ይታወሳል።

በጥናቱ ውስጥ እነማን የአገሪቱን ገንዘብ እየዘረፉ ወደ ውጭ አገራት እንደላኩ አልተጠቀሰም። ይሁን እንጅ በኢትዮጵያ ውስጥ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነውን ንግድ የተቆጣጠሩትና በአለማቀፍ ንግድ ተዋናይ የሆኑት የህዝባዊ ወያን ሐርነት ትግራይ ኩባንያ ንብረት የሆነው የትግራይ መልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ በእንግሊዝኛው  አጠራር ኢፈርት እና የሼክ ሙሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ንብረት የሆነው ሚድሮክ ኢትዮጵያ መሆናቸው ይታወቃል።

ከአመት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት መርሀግብር በቱርክ በተካሄደበት ወቅት፣ የድርጅቱ ባለስልጣናት በጉባኤው ለተሳተፉት አቶ መለስ ዜናዊ የችግሩን አሳሳቢነት ገልጸውላቸው እንደነበር ይታወሳል።

 
Leave a comment

Posted by on December 13, 2012 in ENGLISH, NEWS, POLITICS

 

Tags: , , , ,

Leave a comment