RSS

የእብዶቹ መንግስትና ሕገ-መንግስታቸው

18 Nov
ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)

Ethiopian Constitution - Amharic/English.

ያለፈው የወያኔ መሪ ባለቤት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ትግራይን የኢንዱስትሪ ማእከል ለማድረግ መለስ ዜናዊ አቅዶት የነበረውን፤ ጽፎ ጽፎ ያስቀመጠውን ህልሙን ተግባር ላይ ለማዋል መንቀሳቀስ እንደምትጀምር በቅርቡ በይፋ አውጃለች። ይህ ሰው የኢትዮጵያ መሪ ይባል የነበረ ነው። ለምንድነው ከኢትዮጵያ ህዝብ ደብቆ ለትግራይ ብቻ ያን ሁሉ ራዕይ አልሞ፤ አቅዶ፤ ነድፎ እንዲፈጸም አደራ ብሎ የነበረው? ለሚለው ጥያቄ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የራሱን መልስ ይስጥ።ወይዘሮዋ ይህንን ተልኮ የምትፈጽመው ኢፈርት የሚባለውን የንግድ ድርጅት በመምራት ነው።

ኢፈርት የኢትዮጵያን ሀብት በሙሉ ተቆጣጥሮ እንዲይዝ የተደረገው የወያኔ የኢኮሚ ክንፋቸው ነው። መልካም!..ትግራይ ከኢትዮጵያ ከተሞች ሁሉ ተመርጣ የኢንዱስትሪ ማእከል ትሁን።…ከዚያ በሗላስ?..መለስ ዜናዊ ምን አድርጉ ብሎ ጽፎላቸው ይሆን ? ኢትዮጵያውያን ሁሉ ግምታቸውን ቢጽፉ ለጥንቃቄ ይረዳናል። ትግራይን  በኢንዱስትሪ ካበለጸጋችሁ በሗላ… አንዲህ አድርጉ… ብሎ የጻፈው ለኔ እንደሚታየኝ……ትግራይን በኢንዱስትሪ አጥለቅልቁ። ክልላችን አስተማማኝ የኢንዱስትሪ ማእከል ከሆነች በሗላ ደረጃ በደረጃ ሌሎቹ ክልሎች የየራሳቸው ጦር እንዲያሰለጥኑ እንዲያደራጁ እርዷቸው። የጦር መሳሪያ በገፍ አቅርቡላቸው።ከአማሮቹ ክልል በስተቀር ሌሎቹን በሙሉ በሚገባ በጦር ካደራጃችሁ በሗላ በሀገሪቱ ያለውን መከላከያ ከአየር ሀይል እስከ እግረኛ የመከላከያውን ተቋም በሙሉ ቀስ በቀስ እያላችሁ ነገር ግን ብዙም ሳታዘገዩ በመላው ትግራይ ውስጥ አስፍሩት። አማሮቹ ላይ ልዩ ትኩረት አድርጉ።በጥንቃቄ ተቆጣጠሯቸው። አንድም የጦር መሳሪያ በክልላቸው እንዳይገኝ። የራሳቸው ጦርና ድርጅታዊ ጥንካሬም እንዳይኖራቸው አድርጉ።በኢኮኖሚውም ከተወሰነ ደረጃ በላይ ጠንክረው እንዳይሄዱ አድርጉ። በተቻለ መጠን ከፋፍላችሁ እያጋጫችሁ አዳክማችሁ ያዟቸው። ግጭት እየፈጠራችሁ በዙሪያቸው ካሉት ክልልሎች ጋር ሁሉ አጣሏቸው።

በተወሰነ ደረጃ በተለይም በአማራው ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንዲንቀሳቀስ ካደረጋችሁ፤ ሁከት እንዲፈጠር ካደረጋችሁ በሗላ የትግራይ ተወላጅ የሆነውን በሙሉ ወደትግራይ እንዲሰባሰብ አድርጉ።ከዚያ ብሄር ብሄረሰቦች የራሳቸውን እድል በራሳቸው መወሰን፤ ነጻነታቸውን ማወጅ እንደሚቻል ሀያ አራት ሰአት የማያቋርጥ የፕሮፓጋንዳ ስራ እንዲሰራ አድርጉ።የትግራይን ዙሪያ በጦር እጠሩ። ካጠራችሁ በሗላ የህገመንግስቱን አንቀጽ 39 መሰረት በማድረግ የታላቋን ትግራይ ነጻነት አውጁ።ሌሎቹም ክልልሎች ያንኑ አቅጣጫ እንዲከተሉ አበረታቷቸው።አንድነት ምናምን… ኢትዮጵያ ምናምን እያሉ አማሮች ለመነሳት ቢሞክሩ በፍጥነት ተረባረቡባቸው። በዙሪያቸው ያሉ ብሄር ብሄረሰቦች  ሁሉ እንዲነሱባቸው አድርጉ።በተለይ ከኦሮሞው ጋር በደንብ አድርጋችሁ አባሏቸው። ካሁን በፊት የተጠቀምነውን ዘዴ በበለጠ አጠናክራችሁ ተጠቀሙበት።አማራውን ኦሮሞው እጅ ለእጅ ከተያያዙ ሌሎቹን ሁሉ በቀላሉ ማስተባበርና ማቀፍ ስለሚችሉ ከፍተኛ ችግር ይፈጠርባችሗል። ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ። በተለይ ሁለቱ እንዳይስማሙ። አማሮቹን ከጀርባ በኩልም በሱዳኖች አስመቷቸው። የሰጠናችሁን መሬት ሊወስዱባችሁ ነው በሏቸው።አማራው ከተመታ… አማራው ከጠፋ ሁሉም ብሔረሰቦች ነፃነታቸውን አውጀው በሰላም ይኖራሉ።የታላቋ ትግራይ ኢንዱስትሪም ሰፊ ጥሬ ሀብትና ገበያ ያገኛል።ህዝቡም ይበለጽጋል።…የመለስ ዜናዊ ሕገ መንግስት አንቀጽ89፤ ንኡስ አንቀጽ 2፤ እንደሚለደው፤

መንግስት የኢትዮጵያውያንን የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ለማሻሻል እኩል እድል እንዲኖራቸው ለማድረግና ሀብት ፍትሀዊ በሆነ መንገድ የሚከፋፈልበትን ሁኔታ የማመቻቸት ግዴታ አለበት።

ይህን ህገ-መንግስታዊ ግዴታ የማስፈጸም ሀላፊነት የነበረበት ሰው ነው ትግራይን ብቻ የኢንዱስትሪ ማእከል ለማድረግ ሲሸርብና ሲጎነጉን የኖረው።

ውድ አንባብያን ወያኔ ሶስት ህግ አለው ይባላል።አንደኛው፤ መለስ ዜናዊ የጻፈው የራሱ የሆነውና ህገ-መንግስት ብሎ ህዝብ ላይ የጫነው ነው። ሁለተኛው ተቃወሙኝ ጠሉኝ የሚላቸውን ዜጎች ለማጥፋት በየጊዜው አዳዲስ ህግ እያወጣ ዜጎችን የሚያስጨንቅበት የሚያስርበት የሚገልበት ለምሳሌ የሽብርተኝነት ሕግ አይነቱ ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ የጫካ ህጉ በፈለገው ሰአት የፈለገውን የሚያደርግበት መሳሪያው ነው።ሶስቱንም ህጎች እንደየሆኔታው እየተጠቀመ የቡድኑንና የስልጣኑን ደህንነት እየጠበቀ አገዛዙን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እያጠናከረ የስልጣን ዘመኑን ቀጣይነት ያረጋግጥበታል።እስካሁን በሀያ አንድ አመታት ተሞክሮ ያሳየን ነገር ቢኖር ያለ ምንም የህዝብ ምክርና ይሁንታ በፈለገው ሰአት የፈለገውን ነገር እያደረገ በጫካ ህጉ እንደሚኖር ሲያረገግጥ ይህን ድርጊት የሚቃወሙ ዜጎችን የሚመታው አዳዲስ ህግ እየፈጠረ መሆኑን ነው።

ህገ መንግስቱ ከህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ነው። ተቀበሉት። ተገዙለት። ስገዱለት። እያለ እንደመለመኛ ቁና አስቀድሞ እየያዘ ከእርሱ ጋር ለመነጋገር ለመደራደር ለመከራከር የሚፈልጉትን ወገኖች ሁሉ፤ መጀመሪያ ተሳለሙ፤ ተቀበሉ፤ ብሎ የሚያቀርበውን ሰነድ፤ በሀያ አንድ አመታት ታሪክ ውስጥ አንድም ቀን አንዲቷን አንቀጽ አክብሮ ተገዝቶላት ህዝቡን ሲገዛ አልታየም።ድርጊታቸው በሙሉ ህገመንግስታቸውን የሚቃረን ከቶም ከቶ የማይገናኝ መሆኑን ለመረዳት አንድ ሁለት እያልን ጥቂቱን እንመልከት

ሕገመንግስት አንቀጽ 8 ፤ ንኡስ አንቀጽ 1

ሰብዓዊ መብቶችና ነጻነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ፤የማይጣሱና የማይገፈፉ ናቸው።

ንዑስ አንቀጽ 2

የዜጎች እና የህዝቦች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ይከበራሉ።

ባለፉት ሀያ አንድ አመታት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤና የአለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅቶችን ላንቃቸው እስኪነቃ ሲአስጮሀቸው የነበረውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት፤ አሁንም በዛሬዋ ጀንበር በኢትዮጵያ ውስጥ በሰብአዊ ፍጡር ላይ የሚፈጸመውን ግፍ፤ በዚህ ጽሁር ለመዘርዘር እንደማይቻል አንባብያን የሚያውቁት ጉዳይ ነው።ምርጫ 97 ላይ ወያኔዎች ክፉኛ ከደነገጡበት ጊዜ ጀምሮ እንደ እብደት አድርጎ ያመማቸው ነገር ብዙ አስገራሚ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ሰላስገደዳቸው፤ በሰብዓዊ መብት ድርጅቶችና በፖለቲካ ድርጅቶች ላይ በከፈቱት ከባድ ጥቃት ሰለባ የሆነው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ ቢሮዎቹም ሁሉ ተዘግተው ሰራተኞቹ ታስረውና ከሀገር ተሰደው ባለበት ሁኔታ ያአልበቃ ብሎ ከደጋፊችና አለም አቀፍ ለጋሾች ያገኘውን ስራ ማካሄጃ አስር ሚሊዮን ብር አካባቢ ወያኔ በቅርቡ ወረሰ። የኢትዮጵያ ሴቶች ህግ ባለሙያዎች ማህበርም እንደዚያው ተዘረፈ።ይህ እንግዲህ በጎቹን ለማጥቃት መጀመሪያ እረኛውን ማጥፋት የሚለው የሴጣን ብልሀት መሆኑ ነው።

ሕገመንግስት አንቀጽ 11 የመንግስትና የሀይማኖት መለያየት

ንኡስ አንቀጽ 3

መንግስት በሀይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም። ሀይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ  አይገባም።

ሙስሊም ወንድሞቻችን በመጠየቅ ላይ ያሉትና እየተገደሉበት ያለው ጉዳይ የሀይማኖት መሪዎቻችንን እኛው በየቤተ መስጊዳችን ተሰብስበን እንምረጥ፤ሕገመንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት የሀይማኖት ነጻነታችንን ተጠቅመን የውስጥ አስተዳደራችንን በዲሞክራሲያዊ አሰራር እናካሂድ፤መንግስት የራሱን ካድሬዎች እየመለመለ እራሱ በመረጠው አምልኮ እያሰለጠነ፤ሊጭንብን የሚሞክረውን ከልት ያቁም ነው። ወያኔ ደግሞ ህገመንግስት ብሎ ያቀረበውን ሰነድ ወደጎን ትቶ አሕባሸ የሚባል ተለጣፊ እስላም ከሊባኖስ አገር አስመጥቼላችሗለሁና ለሺዎች አመታት ስትከተሉት የነበረውን እስልምና ጥላችሁ እኔ ያመጣሁትን ያብዮታዊ ዲሞክራሲ እስልምና ተቀበሉ ነው። ሙስሊም ወንድሞቻችን አናም አጠቃላይ ህዝባችን ህገመንግስቱ ለምናችን ነው? ብለው ቢጠይቁ ተፈጥሮአዊ ነው።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ኖቬምበር 4 / 2012 ባወጣው ሪፖርቱ እንዳለው “..እየቀጠለ ላለው የሙስሊማን ተቃውሞ ምላሽ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የሰብአዊ መብት ጥሰት እየፈጸሙ ነው። በርካታ ቁጥር ያላቸው ሙስሊም ተቃዋሚዎች ታስረዋል። ፖሊስ ከልክ ያለፈ ሀይል እየተቀመ እንደሆነ የሚያመለክቱ በርካታ ሪፖርቶችም አሉ። የተቃውሞው ቁልፍ አንቀሳቃሾች በአሸባሪነት ወንጀል ተከሰዋል። ብዙዎቹ የታሰሩት የተከሰሱት የመንግስቱ የጥቃት ኢላማ የሆኑት ተቃውሞአቸውን በሰላም ለመግለጽ በመሳተፋቸው ነው..” ይህ ካምነስቲ ኢንተርናሽናል ዘገባ የተወሰደ ነው።

መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ አይገባም የሚለው የወያኔ ህገመንግስት እንደጠቅላላው ህጉ ለተረትነት የተቀመጠ በመሆኑ ከወያኔ ጋር መነጋገር የሚቻለው ሕግን እየጠቀሱ ሳይሆን ሲቦቀሱ እየቦቀሱ ሊሆን የተፈጥሮ ግዴታ መምጣቱ ነው። የህግና የሰላም አማራጭ

በኢትዮጵያ ውስጥ የማይሰራ መሆኑን ለማወቅ ሀያ አንድ አመታት መጓዝ አልነበረብንም።

ሕገ መንግስት አንቀጽ 12 የመንግስት አሰራርና ተጠያቂነት፤

ንኡስ አንቀጽ 1

የመንግስት አሰራር ለህዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን አለበት

የሞተው የወያኔ መሪ ሬሳው በሳጥን ተጭኖ እስከመጣበት ድረስ ምን እንደሆን፤፡ የት እንደነበረ ከኢትዮጵያ ህዝብ ይልቅ ሁኔታውን የሚያውቁት የሚስጥር ተካፋዮቻቸው ባእዳኑ ነበሩ።በየትም ሀገር መንግስት እንዲህ በከፋ መልኩ ለሚያስተዳድረው ህዝብ ባይተዋርና ድብቅ ሆኖ አያውቅም።

በልማት ስም የኢትዮጵያን ለም መሬት ለመሸጥ ዜጎችን በሀይል እያሳደደ እየገደለ ታሪካዊ አድባራትና ገዳማትን ክብርና ይዞታ እደፈረ እየናደ፤ መሬቱን ለባእዳን ሲያቀራምት፤ ወያኔ ምን ስምምነት እንዳደረገ፤ ምን እንደሚከፍሉ ገንዘቡ ለየትኛው ክፍል አንደሚገባ፤ የመሬት ተከራዮቹ ግዴታና መብት ምን አንደሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚነገረው ነገር አለ? አንድ ሺህ ስድስት መቶ ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን የኢትዮጵያ ግዛት ለሱዳን አሳልፈው ሲሰጡ መንግስት ነን ያሉት ወያኔዎች የሀገሪቱ ባለቤት ለሆነው ህዝብ ያማከሩት የነገሩት ነገር አለ? የኢትዮጵያን ጥቅምና ደህንነት ለመጠበቅ ሳይሆን የምእራባውያንን ተልኮ ለማስፈጸም ጦር ሰራዊቱን ድንበር እያሻገረ ወደ ሶማሊያ ሲያሰማራ የሞተው የቆሰለው ተነግሮ ያውቃል? ለአብነት ያህል ይህንን ካነሳሁ አንባቢ የቀረውን ይሙላ። የሚያስደነግጠው ነገር ሕግና ህገመንግስት አያስፈልገንም ወያኔ እያደረገ እንዳለው ማንም ዜጋ በያለበት የፈለገውን እያደረገ ይኑር ብሎ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳር እዳር ቢነሳ ምን ይሆን የሚፈጠረው?

ሕገመንግስት አንቀጽ 12፤ ንኡስ አንቀጽ 2

ማንኛውም ሀላፊና የሕዝብ ተመራጭ ሀላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂ ይሆናል።

ከማንኛውም ሀገር አንባገነን ገዢዎች በከፋ መልኩ ወያኔዎች በተያያዙት የሀገር ሀብት ዘረፋና ሙስና ባህር ማዶ ያሸሹት 11.7 ቢሊዮን ዶላር ሲዘረፍ ፤ አንድ የጦር አዛዥ ሀምሳ ሚሊዮን አርባ ሚሊዮን የሚያወጣ ህንጻ ሲገነባ፤ በነፃ ለህዝብ እንዲታደል በባእዳን በጎ አድራጊዎች የተለገሰ መድሀኒት በሀገር ውስጥና በኬንያ ሲቸበቸብ፤ ለዚህ ሁሉ ሀላፊነት መጓደል የተጠየቀ የመንግስት ባለስልጣን የለም።ባለፈው አመት አስርሺህ ቶን የሚመዝን ቡና ከተቀመጠበት ተሰወረ ሲባል፤አስራ ስድስት ሚሊዮን ዶላር ግምት ያለው የወርቅ ክምችት ከብሄራዊ ባንክ ተሰረቀ ሲባል፤ በራሳቸው አንደበት እጃቸው እንዳለበት ለህዝቡ በንቀት ሲነገረው አንድም የወያኔ ባለስልጣን በተጠያቂነት አልቀረበም። እነሱን ያልሆነ ይህን ወንጀል ፈጽሞ በኢትዮጵያ ምድር መሸሸጊያ ቦታ እንደማይኖረው ለኢትዮጵያ ህዝብ ግልጽ የሆነ ጉዳይ ነው።

ሕገመንግስት አንቀጽ 15፤ የህይወት መብት

ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብት አለው። ማንኛውም ሰው በሕግ በተደነገገ ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ሕይወቱን አያጣም።

ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ኦነግ ነህ፤ መላው አማራ ነህ፤ እንዲ ነህ እንዲያ ነህ እያሉ እየገደሉ በየጢሻው የጣሉትንና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ ሲጮህላቸው የነበሩ ዜጎች እንዳሉ ሁነው የጅምላ የጅምላውን ፍጅት አንድ ሁለቱን ብናነሳ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የአካዳሚክ ነጻነታውን ለመጠየቅ በሰላም ወተው ነው ተጨፍጭፈው በየእስር ቤቱ የታጎሩት። ሙስሊም ወንድሞቻችን በአርሲ አረካ፤ በወሎ እየተገደሉ ነው። ምርጫ 97 ሁለት መቶ ሰው አስገድሏል። 800 አቁስላል። ‘’ በህግ በተደነገገ ከባድ ወንጀል ካልሆነ ሰው ሕይወቱን አያጣም” ይላል ህጉ። ወያኔ አነዚህን ሁሉ ዜጎች ሲገድል የትኛው ፍርድ ቤት አቅርቦ አስፈርዶ ይሆን ? ለዛሬ በዚሁ ላብቃና ቀጣዩን ይዠ እስከምንገናኝ ቸር ያሰማን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

lkebede10@gmail.com

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on November 18, 2012 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: