RSS

በመከላከያ የጀኔራሎች ፍጥጫ

03 Nov

(እየሩሳሌም አርአያ)


በመከላከያ ያለው ሽኩቻ እየበረታ ሄዶዋል። በጄ/ል ሳሞራ ትዕዛዝ የአየር ሓይል አዛዥ የነበሩት
ጄ/ል ሞላ ሃ/ማሪያም ከሃላፊነት እንዲነሱ ተደርጎዋል። በምትካቸው ደግሞ ጄ/ል መሃሪ ዘውዴ
እንደሚቀመጡ ታውቓል። በቅርቡ የሜ/ጄኔራልነት ሹመት ያገኙት እና ወዲ ዘውዴ በሚል
የሚጠሩት ጄ/ል መሃሪ ዘውዴ ከበረሃ አንስቶ ከሳሞራ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት እንዳላቸው ከዚህ
ቀደም ጠቁሜ ነበር። የሹመታቸው ምስጢሩ ሳሞራ ናቸው። ካኤርትራ የሚወለዱት ወዲ ዘውዴ
ከሳሞራ ባለፈ ለመለስ ታማኝ አገልጋይ የነበሩ ናችው። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት « ፈሪ» ተብለው
እንደተገመገሙ ታማኝ ምንጮች አስታውሰዋል።
በአንጻሩ ጄ/ል ሞላ ወደ አየር ሃይል አዛዥነት ከመምጣታቸው በፊት የላቀ ጀብዱ እንደፈጸሙ
ምንጮች ጠቁመዋል። በሻእቢያ ጦርነት ወቅት ኰ/ል ማእረግ የነበራቸው ሞላ በባድመ፡ አስመራ፡
ተሰኔ….በመሳሰሉ ከባድ ውጊያዎች ላይ የጦር ጄቶችን በማብረር ሻእቢያን ድባቅ የመቱ ኢትዮጵያዊ
ጀግና ናቸው።
ጄ/ል ሞላ ለአቶ መለስና ለሳሞራ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደነበራቸው ሲታወቅ በተለይ በጦርነቱ
የተፈጥጸመው ሴራ፡ አሰብ ወደብን ለመያዝ የተነደፈው ፕላን መኮላሽትን ጨምሮ ባድመን እንስጥ የሚለውን ባለ 5 ነጥብ የክህደት
አጀንዳና ሌሎች የነመለስ – ሳሞራ ሕገ ወጥ አካሔዶችን አጥብቀው ያወግዙ እንደነበረ ተጠቁሞል። « በራሱ እምነት የሚጉዝ ጠንካራ
ሰው» ተብለው በባልደረቦቻቸው የሚሞካሹት ጄ/ል ሞላ ያራምዱት በነበረው አቁዋም በነመለስ- በረከት ጥርስ ተነክሶባቸው ቆይቶዋል።
ከዚያም ባለፈ « የአንጃ ደጋፊ» በሚል ተገምግመዋል። ቢሆንም ግን ከአቖማቸው ዝንፍ ሳይሉ ቖይተዋል።
ከጄ/ል ሞላ ጋር የቅርብ ወዳጅ የነበሩትና የአየር ሃይል ባልደረባ የነበሩት ኰ/ል ክብሮም በ1996ዓ.ም የመለስን – ባድመን አሳልፎ
የመስጠት አጀንዳ በመቃወም ሰራዊቱን ሰብስበው እንዲያወግዝ የማነሳሳት ጥሪ በማድረጋቸው አንዲባረሩ ተደርጎዋል። በ1999 ዓ.ም
ማእረጋቸው ተገፎ እንዲባረሩ የተደረጉት የቀድሞ የአየር ሃይል አዛዥ ጄ/ል አለምሽት ደግፌ ፡ መጀመሪያ ያራምዱት የነበረውን – መለስን
የመደገፍ አቁዋም በመተው መቃወም በመጀመራቸው ውሳኔው ሊተላለፍባቸው ችሎዋል። ጄ/ል አለምሽት ከስልጣን ከመነሳታቸው
በፊት አንድ አስገራሚ ነገር ሰርተዋል፤ በ1993 ዓ.ም የአቶ መለስን ተሃድሶ በማውገዝ ጥለው የወጡት ጄ/ል ታደሰ በርሄ (ጋውና) እና
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ « መታሰር አለባቸው » ሲሉ በወቅቱ የተከራከሩት ጄ/ል አለምሽት ከጊዜ በሁዋላ ለሁለቱም የቀድሞ ባለስልጣናት ስልክ
ደውለው ይቅርታ መጠየቃቸው ነበር። « በናንተ ላይ ሳራምድ የነበረው ተግባር አሳዝኖኛል፤ የመለስን አካሄድ ያወቅኩት ዘግይቶ ነው።
ይቅርታ አድርጉልኝ።» እንዳሉዋቸው ታማኝ ምንጮች አረጋግጠዋል። በነገራችን ላይ አለምሽት ቦሌ አካባቢ በየእለቱ መጠጥ ሲጎነጩና
ሲበሳጩ ይታያሉ።
በአለምሽት ቦታ የተተኩት ጄ/ል ሞላ ለ4 አመት አየር ሃይልን ሲመሩ ከቆዩ በሁላ መነሳታቸው ከጀርባ ያለውን ከባድ የፖለቲካ ሽኩቻ
ወደከፋ ጫፍ እንደሚያሽጋግረው የቅርብ ምንጮች ስጋታቸውን አስቀምጠዋል። ጄ/ል ሞላ በአየር ሃይልና በመከላከያ በርካታ ደጋፊዎች
እንዳላቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል። በሌላም በኩል ጄ/ል መሃሪ ዘውዴ በአንድ የአየር ሃይል አንጋፋ መኮንን ላይ የፈጸሙት አሳዛኝ ድርጊት ይገኛል። መ/አ ለማ ይባላሉ፤ የኦሮሞ ተወላጅ ናቸው። ለ25 አመታት በአየር ሃይል አገልግለዋል። በኢትዮጵያ በግራውንድ ስኩል እንዲሁም በሩሲያ ከፍተኛ ስልጠና
ወስደዋል። ኤል-39 የመለማመጃ አውሮፕላን ሴፍቲ ሃላፊ ነበሩ። ከተግባርድ ጀርባ ኪራይ ቤቶች በሰጣቸው መኖሪያ ተከራይተው ይኖሩ
ነበር። በ1996ዓ.ም ለውሽማቸው ቤቱን መስጠት የፈለጉት ጄ/ል መሃሪ መ/አ ለማን ቤቱን ይጠይቃቸዋል፤ « ለምን እለቃለው?»
በማለት እምቢ ይላሉ። ጄ/ል ወዲ ዘውዴ ለማስፈራራት ይሞክራሉ። ለማ ግን አልተበገሩም። ጄኔራሉ የአየር ሃይል ኤር-ፖሊሶችን
በማሰማራት መ/አ ለማ በመኖሪያ ቤታቸው በምሽት ያስደበድባሉ። በአጋጣሚ ፓትሮል የሚዞሩ ፌደራል ፖሊሶች ደርሰው
ያስጥሉኣቸዋል።
መ/አ ለማ ለደታ ፍ/ቤት ይከሳሉ፤ ደብዳቢዎቹ ፍ/ቤት ቀርበው ሲጠየቁ « ወዲ ዘውዴ ነው የላከን » ይላሉ። ከዚያም ጄ/ሉ ተከሰሱ፤
በአስገራሚ ሁኔታ ፍ/ቤቱ ክሱን በማቓረጥ «ጉዳዪ በወታደራዊ ፍ/ቤት ነው መታየት ያለበት» አለ። መ/አ ለማ በደረሰባቸው ከባድ
ድብደባ አንድ ጆሮቸው አይሰማም፤ኩላሊታቸውና እግራቸው ክፉኛ ተጎድቶ ስለነበረ፤ የሃኪሞች ቦርድ « መስራት እንደማይችሉ
በመግለጽ ቦርድ እንዲወጡ ወሰነ።  ይህን ተከትሎ ጄ/ል ወዲ ዘውዴ ባሳለፉት ቀጭን ትእዛዝ መ/አ ለማ እስር ቤት ተወረወሩ፤በየቀኑ ከፍተኛ ድብደባ ይፈጸምባቸው ነበር። ክእስር ቤት በተደጋጋሚ ደብዳቤ ጽፈዋል፤ በወቅቱ የመከላከያ ሚ/ር ለነበሩት አባዱላ ገመዳ ጭምር የአቤቱታ ጥሪ አሰምተዋል። ሰሚ ግን አላገኙም። መጀመሪያ በአየር ሃይል ከዛም በታጠቅና ናዝሬት እስርቤቶች የታሰሩትና ከፍተኛ ግፍና ሰቆቃ የተፈራረቀባቸው መ/አ ለማ መጨረሻቸው ምን እንደሆነ አይታወቅም።
ኢትዮሚድያ – Ethiomedia.com
November 2, 2012

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on November 3, 2012 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , , , , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: