RSS

በአዲስ አበባ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ዛሬም ተቃውአቸውን አሰሙ

02 Nov

ኢሳት ዜና:-ላለፉት 11 ወራት ድምጻችን ይሰማ በማለት የመብት ጥያቄዎችን ያነሱ ኢትዮጵያውያን ዛሬም ተቃውሞአቸውን አሰምተው ውለዋል።

ኢትዮጵያውያኑ ሙስሊሞች ተቃውሞአቸውን የገለጡት ነጭ ጨርቅ በማውለብለብና በዝምታ ሲሆን፣ የነጩ ጨርቅ ትርጉሙ በእስር ላይ የሚገኙት መሪዎቻቸው አሸባሪዎች ሳይሆኑ የሰላም ምልክቶች መሆናቸውን ለመግልጽ  መሆኑ ታውቋል። ተቃውሞዓቸውን በዝምታ ያደረጉትም መሪዎቻቸው ህገመንግስታዊ መብታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ የታሰሩ ይህሊና እስረኞች መሆናቸውን ለመግልጽ ነው ሲሉ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ለኢሳት ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ አንዋር መስጊድ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች የተሳተፉበት የዛሬው ተቃውሞ በሰላም ተጠናቋል። መንግስት ባለፈው ሳምንት 29 የሙስሊም መሪዎችን በአሸባሪዎች እና አክራሪነትን በማስፋፋት ወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል። አብዛኛው ሙስሊሞች ግን በመንግስት በኩል የቀረበውን ክስ አይቀበሉትም።

በሌላ በኩል በወልድያ ከተማ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሙስሊሞች ከጁመአ ስግደት በሁዋላ ተይዘው መታሰራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሀይማኖት መሪዎቻችንን በነጻነት እንምረጥ፣ መንግስት አህባሽ የተባለውን እስልምና ለማስፋፋት የሚያደርገውን የተቀነባበረ ዘመቻ ያቁም እንዲሁም መሪዎቻችን ይፈቱ  የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳታቸው ይታወሳል።

 
Leave a comment

Posted by on November 2, 2012 in AMHARIC, NEWS

 

Tags: , , ,

Leave a comment