RSS

አቶ ኃይለማርያም እና ኤርትራ – መልስ ለአቶ ግርማ ካሳ

22 Oct

ውድ አቶ ግርማ ካሳ አቶ ኃይለማርምና ኤርትራ በሚል ፅሑፍ አዘጋጅና አቅራቢ በመሆን ያለዎትን ሃሳብ ስላካፈሉን በቅድሚያ ያለኝን ምስጋናዬ ላቅርብ፡፡ በፅሑፎ ላይ ስለሰጡት የዘር መተንትን ከእርሶ ጋር የምጋራው ነጥብ ቢኖረኝ እንጂ የምቃወምዎት ሃሳብ የለኝም፡፡ ምክንያቱም ዘር የእድል ጉዳይ እንጂ የጥረት ውጤት አይደልምና፡፡ ማንኛውም ሰው መመዘን ካለበት በጥረቱ በሚሰራው ስራና በሚያመጣ ውጤት እንጂ በዘር መሆኑ በጣሙን የተሳሳተ አመለካከት በመሆኑ በዚህ ላይ ሰፊ ትንታኔ መስጠት ቢቻልም በግዜው ስለፃፉት ስለ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሳብ ላይ ያለኝን አስቴየት ለመሰንዘር ነው፡፡ ከዚህም አኳያ በፃፉት ፅሑፍ ላይ ከእርሶ ጋር የምጋራው ነጥብ እንዳለኝ ሁሉ የማለልስማማበትም  ዓቢይ ነጥብ አለኝ፡፡  እርሱም የአገራችንን አንድ አባባል በቅድሚያ በመጥቀስ ወደ ዋናው ነጥብ እገባለሁ፡፡ አለባበሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ እነደሚባለው ሁሉ እርስዎም በማወቅም ይሁን እሳቸውን ላለማሳጣት ከሚመስል አስተሳሰብ ለመደገፍ የሚያደርጉት የፅሑፎት ይዘት ትንሽ ጎልቶ ይታያል፡፡ በመሆኑም አስተያየት ፅፌ የማለቀውን ሰው አስተያየቴን እንድሰጥ ውስጤን ኮረኮሩት፡፡

አስተያየቴ አቶ ልበላቸው ወይስ ጠቅላይ ሚኒስትር ግልፅ ያለ አቋም ባይኖረኝም የሀገሪቱ ፓርላማ፤ ይህም ፓርላማ መሆኑ ቢያጠራጥርም፤ ማለትም በኔ አስተያየት የመንደራችንን የነትዬ አለሚቱን በዳኝነት የሚመሩትን የሴቶች አድር ያክል እንኳን ጠንካራ ያልሆነና እርባና የሌለው ፊደል የቆጠሩና ያላቆጠሩ የኢሐድግ የሆድ አደሮች ስብስብ በመሆኑ ነው፡፡ በነገራችን ላይ  የሴቶችን እድር ያልኩት የመጠንንና የጥንቅሩን የምጠና ትንሽነት ለማሳየት እንጂ ምንም አይነት አሉታዊ አስተያየት በእድሩም ሆነ በፆታ ላይ እንደሌለኝ ታዳሚውን ለመስረዳት እወዳሉ፡፡

ይሁንና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹመት ስንል ፓርላማ እንበለው፡፡ ከዚህም ነጥብ በመነሳት አስተያየት እንስጥ ከተባለ አርስዎ በመጀመሪያ ስለ ስም ትርጉምና ስለ ቀዳማዊት እመቤት የዘር ምንጭ እማኛነትዎን ዋቢ በማስደገፍ ስለልጃቸው ስም የተሰጠውን የመፅሐፍ ቅዱስ ትንታኔ በሚገባ አንብቤያለሁ፡፡ በዚህ ላይ እውቀት ኖረኝም አልኖረኝም መተቸት አልፈልግም ቢያንስ ግን የርስዎ ሃሳብ እጋራለሁ፡፡

ሌላው ነጥቦት ኃይለማርያምን አስመልክቶ ሕዝብ አክባሪ ናቸው ብልው ሀሳቦትን  ያሰፈሩበት ፅሑፎትን መልሰው ቢያነቡት እጅግ የሚያሳዝን ነው፡፡ ምክንያቴም ሕዝብን የሚከብርና የሚወድ ባለስልጣን ወይንም የያዝኩት ስልጣን ምንጩ የሕዝብ ነው የሚል አንድ መሪ የሚያደርግውን ድርጊት እያደረጉ ባለመሆናቸው ነው፡፡ አንዱን እርሶ ከገለፁት ልጥቀስ፤ ስለነ እስክንድር ነጋ ስለ ተቃወሚ መሪዎች እስር ጋር አያይዘው የተናገሩትን አንዱ ነው፡፡ እርስዎም በነግዜ እንስጣቸው አባባል ደጋፊዎች ጋር ተሰላፊ ሆነው በትችቶት ዳር ዳሩን የነኩትን አስተያየት በመጀመር የሀገራቸን ሰው በሚያዘወትረው አንድ ብሂል ልለጥቅ፡፡ እሱም አንድ ነገር ከራሱ ቤተሰብ ውጪ መልክ ሲኖረወ ቁርጥ የኛንቤት ሰው ይላል እናት ከሌላ ያመጣችውን ልጅ ልክ ከባለቤቷ እንዳመጣችው ለማስመሰል፡፡ እናም ሰዉ ግራ የተጋባውና የዘረኝነት ምሳሩን ያነሳው  የሀገሪቱን መፃሂ እድል ለማቃናት የተሰለፉትን ማለትም ብዙዎችና እራሳቸውም የፓረቲውን አመራሮች ጨምሮ ተቃዋሚ የሚባሉት በኔ አመለካከት ግን ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሆኑ ኢትዮጵያውንን ሁሌም ለመደራረር ዝግጁ ያልነበሩት ያለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ያንፀባርቁ የነበረው ሃሳብ እኝህም ሰው ሲደግሙት ምናልባት እሳቸው ባይሆኑም ባለቤታቸው እንደቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የሁለት አገር ሰው ከሆኑ ብልው ነው፤ ምክንያቱም ጠርጥር ከገንፎ ውስጥ አይጣፋም ስንጥር ነውና፡፡

ሌላው ሕዝብ ያከብራሉ ህዝቡን ላለማንገላታት ከሌሊቱ 11፡00 ሰዓት ተነስተው ስራ ይገባሉ ሲወጡም አምሽተው ይወጣሉ ብለውናል፡፡ እስቲ ይህችን አስተያቶትን በጥቂቱ እንያት የሚፈሩት ሕዝብን ነው? ወይስ የሟቹን ጠቅላይ ሚኒስትር ሚስት? እርስዎ ይመልሱት? ወይስ እኔ? በቅን ልቦና የሚያስቡ ከሆነ እሳቸው የሚፈሩት ህዝቡን ሳይሆን በቀድሞ አስተያየቶት በፓርላማ የተናገሩትንና ለጋዜጠኛ የሰጡትን መልስ በመንተራስ እንደሰጡት አስተያየት ትክክል አለመሆነቸውን ነቅሰው ተችተዋል:: ከዚህም መንደርደሪያ በመነሳት ትክክል አለመሆነቸውን በጽሑፎት ገልፀዋል፡፡ ስለዚህም እርሳቸውን መናገር ካላስፈራዎት በስተቀር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዝቡን የሚንቁና ለአንዲት ግለሰብ ትልቅ ፍራቻ እራሳቸው ላይ በመጫን ሕዝብ የጣለባቸውን ትልቅ አላፊነት በትጋት ከመወጣት ይልቅ ጊዜያቸውን ባላባሌ ቧልት የሚያሳልፉ ሆነው ነው የተሰሙኝ፡፡ ሕዝብን የሚያከብር ወዳጄ ሕዝብ የሰጠውን ስልጣን በተገቢው ይጠቀማል እንጂ በነሚሚ ስብአቱ ሬዲዮ ጣቢያ ቧልት በመመራት ለሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚስት ሀዘናችው ይወጡ የሚል ሃሳባ አያመነጩም፡፡

አነድ ነገር ትዝ አለኝና ይህችን አስተሳሰብስ ቢመለከቱት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሕዝብ ቁጥር ከ85 ሚሊዮን አይተናነስም፤ ከዚህም አኳያ ይህ ሕዝብ በመንግስት አመሰራረት ላይ የራሱ የሆነ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ምናልባት ከላይ እንደጠቀስኩት ስልጣን የህዝብ ነው የሚባል ከሆነ፡፡ ይሁንና ይህ ሕዝብ ደግሞ እንደሚወለድበት ብሔርና አካባቢ የራሱ የሆነ ማንነት፣ ባሕልና እምነት አለው፡፡ ከዚህም በመነሳት እርስዎ በገሃድ ባይገልፁትም በአግድሞሽ እንደነገሩን እና ሌሎች እንደሚሉት ለሴትየዋ 80 ቀን ነው፤ ሌላም ይሁን የሃዘን ግዜ እንስጣቸው ብንል ማዘን ካለባቸውም በግላቸው እምነት ነው ማዘን ያለባቸው እንጂ ለአንድ ግለሰብ ሲባል የ85 ሚሊዮን ሕዝብ መብትና ምርጫ ሊረገጥበትና ሊጨፈለቅ አይገባም፡፡ ከዚያም አለፍ ሲል ደግሞ እሳቸው የሚሉትን የ80 ቀን የሐዘን ግዜ ሁሉንም ኢትዮጵያ ሀይምኖቶችና ባሕሎች አይደግፉትም አይቀበሉትም፡፡ ስለዚህም አቶ ኃይለማርያም ማክበር የነበረባቸው የትኛውን ነው? ሕዝቡን ወይስ የአንዲት ግለሰብን ለቅሶ? መቼም ወዳጄ የጠቅላይ ሚኒስትር ለቅሶ ነውና ለምን እንዳይሉኝ?  ምክንያቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅላይ የሆኑት ጠቅልለው እንዲያስተዳድሩት ስልጣኑን የሰጣቸው በማጭበርበር በተገኘ ምርጫም ይሁን በትክክለኛ ይህ ሕዝብ በመሆኑ፡፡

በእርግጥ ያለፉት ጠቅላይ ሚኒስትርም ሆኑ የአሁኑ አንድ ተመሳሳይ ፈሊጥ አላቸው ሕገመንግስቱ ይከበር ይላሉ፡፡ ሕገመንግስቱን መክበር ያለባቸው እንሱ ናቸው፡፡ መክነያቱም እያንዳንዱ ግለሰብ መንግስትን በሚያቋቁምበት ግዜ መንግስት በምን ዓይንት መልኩ ማስተዳደር እንደለበት መንግስት ለመቆጣጠርና ለመጠየቅ እንዲችል ከሕግና ስርአት ውጪ ሲሆን ከስልጣን የሚወርድበት ከዚያም በተጨማሪ ሃላፊነት የተሰጠው ባለስልጣንም በዚሁ ህግ መሰረት ማሕበረሰቡን የሚመራበት መንገድ ነው እንጂ ሌላ ምንም አይደልም፡፡ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር አፈሩን… ያድርግለቸው፡፡ የተከበረውን ባንዲራ … ብለውት የለ፡፡ እንግዲያው ሕገመነግስቱም ሕዝብ የሚፈልገውን የመንግስት ሥልጣን የሚገድብብበት መሳሪያ ሆኖ ካላገለገለው ለኔ ለማ እና ዘመዶቹ ወይም ተረትና ምሣሌ የሚባለው ፅሑፍ ነው፡፡

ሌላው ጥያቄዬን ላስከትል ከሳቸው ጋር አሜሪካ ጂ ምንድን ነው የሚሉት ስብሰባ ላይ መጥተው ከጠቅላይ  ሚኒስትራችን በኋላ ሞተው መርዶአቸውን ቀድምን የሰማነውን የጋናውን ፕሬዚዳንት ብንመለከት ብቁ ማስረጃ ነው፡፡ በርግጥ እሳቸው በአቢዮታዊ ዲሞክራሲ አይመሩም፡፡ የጋናው ፕሬዚዳንት የጆናታናሚልስ ሚስት እስከ አሁን ቤተመንግስት ናቸው? ጥያቄውን ይመልሱ ስለዚህም ኃይልማርያም የሚያከብሩት አዜብን ወይስ የኢትዮጵየን ሕዝብ መልሱ ግልፅና አጭር ነው፡፡ የሚያከብሩትም የሚፈሩትም አዜብንና ሕውሃት ነው እንጂ የኢትዮጵያን ህዝብ አይደለም፡፡ ኃይለማርም ግዜ የሚሰጣቸው በደንብ ወታረደሩን ማዘዝ ችልው እንደቀድሞው መሪያችን መፍጀት እስኪጀምሩና የተሰጣቸውን ሃላፊነት ሕዝብ ማፈኛ እስኪያደርጉት ድረስ ከሆነ እስማማላሁ፡፡ ካለበለዚያ ግን የግብፁን ሬዚዳንት መሃመድ ሙርሲ የወሰዱትን እርምጃ መለስ ብሎ መመልከት ከተቻለ ለኃይለማርም ግዜ እንስጣቸው ማለት ለኔ ቀልድና ሹፈት ነው፡፡ ምክንያቱም በፓቲው ውስጥ ብዙ ግዜ ሰርተዋል በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ሰርተዋል፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርም ሆነው ሰርትዋል ስለዚህም ግዜ በዝቶባቸው የሚሰሩት ጠፍቶባቸው ካልሆነ በስተቀር ግዜ አላነሳቸውም ወዳጄ፡፡

መሐመድ ሙርሲ ከአሜሪካ ተጉዘው የሰሩትን አርሳቸው ከተራ ፓርቲ አባልነት የክልል ፕሬዚዳነትነት ብሎም የጠቅላይ ሚኒስተሩ አመካሪነት ካዛም በመቀጠል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትረና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትረ ሆነው የሰሩበትን አብሮ አደግ ጥርስ አስነቃይ የፓርቲ ስልጣናቸውና ቤታቸውን አያውቁም ብሎ ማለት ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ነው፡፡ ለማንናውም ወዳጄ ቸር እንሰንብት

አቡጊዳ ቀይሶ ከኮልፌ

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on October 22, 2012 in AMHARIC, ARTICLE

 

Tags: , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: