RSS

የህዳሴዉ ግድብ ግንባታ የመቋረጥ አደጋ አንዣቦበታል

10 Oct

Posted by 

Image

የተለያዩ ታማኝ ምንጮች እንደጠቆሙት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በአባይ ወንዝ ላይ የተጀመረዉና ለማጠናቀቅ ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚጠይቅ የተገመተዉ የህዳሴዉ ግድብ ግንባታ የመቋረጥ አደጋ አንዣቦበታል፡፡

ምንጮቹ “የግብፅና የሱዳን መንግስታት በግድቡ ላይ ያላቸዉን ተቃዉሞ ያለዝባሉ ተብለዉ ሲጠበቁ የነበረ ቢሆንም እነርሱ ግን ያን አላደረጉም” ያሉ ሲሆን ፤ “የግድቡን አጠቃላይ ሁኔታ ለማጥናት እና ዉጥረቱን ለማርገብ የተቋቋመዉ ቴክኒካል ኮሚቴ በአዲስ አበባ እያደረገ ባለዉ ዝግ ስብሰባ ላይ ተቃዉሟቸዉን ይበልጥ አጠናክረዉ በተወካዮቻቸዉ አማካኝነት ግልፅ አድርገዋል” በማለት ተናግረዋል፡፡ አይይዘዉም “ይህ የሁለቱ አገሮች የከረረ ተቃዉሞ እንደ አይ ኤም ኤፍ(IMF) ያሉ ተቋማት እያደረጉ ካለዉ ዉትወታ ጋር ተዳምሮ በስልጣን ላይ ያለዉ መንግስት ግንባታዉን እንዲያቆም ሊያስገድደዉ ይችላል” ብለዋል፡፡

ምንጮቹ እንዳብራሩት የግብፅ መንግስት ግድቡ ከኢትዮጵያ ወደ ግብፅ የሚፈሰዉን የዉሃ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንስ ነዉ ያለ ሲሆን ፤ ይህም ደግሞ አጠቃላይ ህልዉናዋን በአባይ ወንዝ ላይ በመሰረተችዉ ግብፅ ላይ በቀጥታ ትልቅ ችግር የሚፈጥር በመሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት በፕሮጀክቱ መግፋቱን አቁሞ ሊያስብበት ይገባል ብሏል፡፡

የሱዳን መንግስት በበኩሉ ግብፆች ባነሱት መከራከርያ ነጥብ ላይ ለዘብተኛ አቋም ቢኖረዉም ግድቡ ግዙፍ በመሆኑ ነገ ከነገ ወዲያ አንድ ችግር ቢደርስበት በሱዳን ምድር ላይ መጠነ ሰፊ ጥፍት ሊያደርስ የሚችል ነዉ ሲሉ ከግድቡ መልካ-ምድራዊ አቀማመጥ ጋር በተያያዘ ተቃዉሟቸዉን ከረር አድርጎ አሰምቷል፡፡

በኮሚቴዉ ስብሰባ ላይ ጠንከር ያለ ተቃዉሞ የገጠመዉ አንባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት የከፋ ተቃዉሞ እንዳልገጠመዉ በተለያዩ የመንግስት ሚዲያወች እየገለፀ ሲሆን ፤ “ቀላል” ሲል ለገለፀዉ የሁለቱ አገሮች ተቃዉሞ  ፕሮጀክቱ ከመጀመሩ በፊት የተደረጉ ጥናቶችን መሰረት በማድረግ አጥጋቢ መልስ ሰጥተንበታል ብሏል፡፡

እየጠነከረ ከመጣዉ የግብፅና የሱዳን ተቃዉሞ ባሻገር የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ከግድቡ ጋር በተያያዘ የተለያየ ስጋታቸዉን እየገለፁ ሲሆን ፤ ከእነዚህም መካከል በዋነኝነት የሚጠቀሰዉ በቅርብ “የኢትዮጵያ መንግስት ደጋግሞ ሊያስብበት ይገባል” ሲል በጥብቅ ያሳሰበዉ አይ ኤም ኤፍ ነዉ፡፡

በኢትዮጵያ የአይ ኤም ኤፍ ተወካይ የሆኑት ጃን ሚክልሰን ለጋዜጠኖች እንደተናገሩት መንግስትን ለአንድ የግድቡ ግንባታ ሀገሪቱ ያላት አጠቃላይ ገንዘብ እንድታፈስ እያደረገ ነዉ ያለ ሲሆን ፤ ይህም በሀገሪቱ ያለዉን አጠቃላይ የንግድ እንቅስቃሴ ክፉኛ በመጉዳት ሀገሪቱን ለባሰ የኢኮኖሚ ችግር ይዳርጋታል ብለዋል፡፡

እንደሚታወሰዉ በአረቡ አለም የተቀሰቀሰዉን ህዝባዊ አቢዮት ተከትሎ መንግስት የግድቡን ፕሮጀክት ለህዝብ ይፋ ሲያደርግ ብዙ የሰሉ ትችቶች ከተለያዩ ምሁራን እና የፖለቲካ ተንታኞች ገጥሞት ነበር፡፡ ከትችቶቹም ዋናዉና ተጠቃሹ ፕሮጀክቱ በጥናት ላይ ያልተመሰረተ እና ከተፋሰሱ ሀገራት ጋር የሚፈጥረዉን የፖለቲካ ችግር ከግምት ዉስጥ ያላስገባ እንዲሁም የአገሪቱን ኢኮኖሚያዊ አቅም ያላገናዘበ  ፤ ይልቁንም ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች በመዛመት ላይ የነበረዉን የአረቡን ዓለም አቢዮት በመፍራት ብቻ በኑሮ ዉድነት ፣ በፍትህ እና በመልካም አስተዳደር እጦት የተማረረዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ለማባበል ሲባል እንዲሁ በችኮላ የተደረገ ነዉ የሚል ነበር፡፡ ሆኖም ግን አንባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት ለትችቱ ጀሮ ዳባ ልበስ በማለት ህብረተሰቡን በዉዴታም በግዴታም ለፕሮጀክቱ የገንዘብ መዋጮ እንዲያደርግ እንዲሁም ቦንድ እንዲገዛ በማድረግ በቀጥታ ወደ ፕሮጀክቱ ትግበራ ሊገባ ችሏል፡፡

በአሁኑ ሰዓትም ህብረተሰቡን በማስገደድና የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ከፍተኛ መጠን ያለዉ ገንዘብ መሰብሰቡን የቀጠለ ሲሆን ፤ ይህ ተግባሩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመንግስት ሰራኞች እና  በከፍተኛ የኑሮ ዉድነት እየተሰቃዩ ባሉ መሰል የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን እየፈጠረ ይገኛል፡፡ በንግዱ ህብረተሰብ  አካባቢም እንዲሁ የተቃዉሞ ጉርምርምታ እየተሰማ ነዉ፡፡

Share this:

Advertisements
 
1 Comment

Posted by on October 10, 2012 in AMHARIC, ARTICLE, POLITICS

 

Tags: ,

One response to “የህዳሴዉ ግድብ ግንባታ የመቋረጥ አደጋ አንዣቦበታል

  1. bayru

    November 2, 2012 at 11:51

    look how you are anti Ethiopia and Ethiopians ,you are the servant of Eritrea and other countries so we are more than 85 million , we can do by our selves by organizing together for one aim to build the dam. even we are ready to pay our blood for development of Ethiopia if necessary . today is another day we are united to pass the dark era and to handle the bright future. b/c it is the basic issue for all Ethiopian people

     

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: