RSS

ቅዱስ ጋብቻ ወይስ ጅምላ ጋብቻ?

09 Oct
ቅዱስ ጋብቻ ወይስ ጅምላ ጋብቻ?

ጋብቻን በተመለከተ፣ ሦስት አሳሳቢ አዝማሚያዎች ይታያሉ። የመጀመሪያው፣ የክርስቲያንና የእስላም ጋብቻ ሲሆን። ቀጥሎ፣ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ። በመጨረሻም፣ የጅምላ ጋብቻ ነው። አንድ ሙስሊም፣ ክርስቲያን ሚስት ማግባት ይችላል ይላል ቁራን። አንዲት ሙስሊም ሴት ግን ክርስቲያን ባል ማግባት አትችልም። ሙስሊም ባል ያገባችዋ ሴትና የምትወልዳቸው ልጆች ደግሞ በክርስቶስ እምነት ውስጥ መሆናቸውን ይከለክላል። በአሁኑ ወቅት ክርስቲያን ነን በሚሉ በአንዳንዶች ዘንድ ከኑሮ ውድነትና እምነትን ካለመረዳት የተነሳ ከሙስሊሞች ጋር የሚጋቡ ቁጥራቸው እየጨመረ መጥቷል። እምነቱን እንደሚገባ የማያውቅ ምእመን እንግዲህ የተጋለጠ ለመሆኑ ይህ አንድ ማስረጃ ነው። “የሰላምና የመቻቻል” አራማጆች የሚሰብኩንን መስማት ትተን የክርስቶስን ወንጌል እንደሚገባ ማስተማር የሚኖርብን ለዚሁ ነው። “[ክርስቶስን] ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድአትጠመዱ፤ … ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?” [2ኛ ቆሮንቶስ 6፡14-15]። በሌላ አነጋገር፣ ክርስቶስን ላመኑ፣ እግዚአብሔርን መታዘዝ ሰውን ከመታዘዝ ሊቀድምባቸው ይገባል [የሐዋርያት ሥራ 4፡19]። እንደዚሁም፣ የክርስቶስን ትምህርት የማይገነዘቡ ያፈቀዳቸውን ያደርጋሉ ማለት፣ ክርስቶስን ለሚከተሉት መመሪያ ይደነግጉላቸዋል ማለት እንዳይደለ ሊታወቅ ይገባል።

ሌላኛው፣ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ጉዳይ ነው። ግብረሰዶማዊነት ሰብዓዊ መብት ነው በሚል ሳቢያ ሕጋዊ እውቅናና ድጋፍ ለማሠጠት ሕዳር ወር 2004 ዓ.ም. በአፍሪካ አዳራሽ የተደረገውን ሙከራ አንዘነጋም። መንግሥት ይህን ተግባራዊ ካላደረገ እርዳታ እንደሚያጣ አሜሪካና አውሮጳ አስታውቀዋል። የፖለቲካና የቤተክርስቲያን መሪዎችም የተባበረ፣ ግልጽና ጠንካራ አቋም እንደመውሰድ በተናጠል ሲቆሙ፣ ሲያመነቱና ሲያፈገፍጉ ታይተዋል። ዛሬ የመብት ጥያቄ ነው፤ ነገ ግን ጥያቄው የጋብቻ ጥያቄ እንደሚሆን ቤተክርስቲያን መርሣት የለባትም። ቤተሰብ የአገር ህልውና መሠረት እንደመሆኑ፣ በዚህ አፍራሽ በሆነ ጉዳይ ላይ ተቻችሎ መኖር የሚባል ነገር ሊኖር እንደማይችል ግልጽ ይመስለናል።

ሦስተኛው፣ ሰሞኑን እየተወራ ያለው የጅምላ ጋብቻ ወይም “የሺህ ጋብቻ” ጉዳይ ነው። በዚህ መሠረት፣ አንድ ሺህ ተጋቢዎች ከየክልሉ መስተዳደሮች ለየብሔሩ በወጣው መመሪያና ኮታ መሠረት እንደሚመለመሉና ጋብቻቸውን በሕዳር ወር በስፖርት ሜዳ ላይ እንደሚፈጽሙ፣ ይህም በዜና አውታሮች እንደሚሠራጭ አዘጋጆቹ ገልጸዋል። ዓላማው፣ ሀ/ ሠርግ እያስከተለ ያለውን ከፍተኛ ወጪ ለመቀነስ ነው ተብሏል። ሪፖርተር ጋዜጣ፣ በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ድህነት ስላለ፣ ማግባት እየፈለጉ የተሳናቸው እንዳሉ ጠቅሶ፣ የናጠጠ ሠርግ የሚሠርጉትን ወርፏቸዋል፤ ለ/ የመቻቻልን ባህል ለማዳበር መ/ የአዲስ አበባን መቆርቆር 125ኛ ዓመት ለመዘከር ሠ/ “ሺህ ጋብቻን” ዓመታዊ ክብረ በዓል ለማድረግ ረ/ የአገራችንን መልካም ገጽታ ለዓለም ለማስታወቅና በ“ጊነስ” የዓለም ሪኮርድ ለማስመዝገብ ነው ብለዋል። ተጋቢዎች ማመልከቻ ይሞሉና፣ለዚሁ የተቋቋመው ኮሚቴ መዝኖ የሚቀበለውን ተቀብሎ ሌላውን  ውድቅ ያደርጋል፤የተመረጡት ተጋቢዎች ወደየመጡበት ክልል ተመልሰው ይህንኑ አዲስ ባህል ያስተዋውቃሉ ማለት ነው።

ዝግጅቱ በንግድ ለተሠማሩ ገቢ ያስገኛል እንበል። በአገር ደረጃ ግን አደገኛ አዝማሚያ መፍጠር ብቻ ሳይሆን ያልታቀዱ ቆይተው የሚከሰቱ የቀውስ ጽንሶችን እንደቋጠረ ማሰብም ይበጃል። መነሻ አሳቡ፣ ማሕበረሰብን በፈለግነው ሁኔታ እንደ አውራ ጎዳና መቀየስ እንችላለን ከሚል ከ19ኝኛው መቶ ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ የተቆነጠረ ይመስላል። ሰው፣ በአምላክ መልክ የተፈጠረ ክቡር ፍጡር ሳይሆን በፍጥረት ሂደት የተገኘ ጅምላ አካል ነው ይላል። ባለፈው ትውልድ፣ እግዚአብሔር የሌለበትን ሶሻሊስታዊ ማሕበረሰብ ለመመሥረት፣ የነበረውን እንዳለ መጣልና ማፍረስ እንደ ተጀመረ እናስታውሳለን። በዚያን ወቅት የአገሬውን ባሕልና የሰውን ተፈጥሮ ካለመረዳት የተነሳ የጠፋውን ሕይወትና የወደመውን ንብረት መጠን እንደማስታወስ፣ ያንኑ ስሕተት በሌላ መልኩ ስንደግም እንዳንገኝ ያሠጋል። ሁለተኛ፣

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on October 9, 2012 in ARTICLE

 

Tags: , ,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: